ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ሽር---ሸረሪቷ

አንጀቷን ---
የተቋጨውን ከእትብቷ
ወተቷን ---
የተሾመውን ከግቷ
ወለላዋን ---
የተሰራውን በደሟ
ቅርሷን ---
ያኖረችውን በስሟ
አወጣችው ! - እያማጠች
እንደ ፈትል - እያደራች
እንደ ጅማት - እየላገች
እሷ ---
ቤተሰሪዋ ...
ብቸኛዋ ...
ኗሪዋ ...
ድምፅ የላትም ---
አትሰማም
ኮቴዋ እንኳን ---
አይጣራም
ዝም - ሽው
ሽክርክርክር ...
አቅታዋን ገትታ
መዞር
በዝምታ በጸትታ ---
መሽከርከር
ያለ ተራዳ ---
ድንኳን ማቆም
ያለ ካስማ ---
ቱሻ ማገም
ትንፋሽ የለ ---
ወይ ኮሽታ
ጣሪያ ማድራት ---
በዝምታ በጸትታ
ወራጀ የለ ---
ባለ ማገር
በጸጥታ ---
ትንፋሽ መስበር ...
ጣሪያ ሠርታ ---
መሽከርከር
ግድግዳ ሠርታ ---
ሳትወጥር
ሽር - ሸረሪቷ ---
ኃያል ጥበቧን ሰጥታ
አጀብ ዘመኗን ፈጅታ ---
ሽር --- ሸረሪቷ
ላንዲት መዓልት ቆይታ
አዲስ ቤቷን ሰርታ
ሽር --- ሸረሪቷ ---
ሁሉን ነገር ረስታ ...

ሚያዚያ ---- 1977
የማለዳ ስንቅ
(አበራ ለማ)

@getem
@getem