#ለፍቅር_ከሆነ
።።።።።።።።።።።።።።።።
ለፍቅር ከሆነ ሺ ጊዜ ልገፋ
ቀጥረሽኝ አትምጪ ልተክዝ ልከፋ
መውደዴን ስነግርሽ እንዳሻሽ ሳቂብኝ
ሺ ጊዜ ስደውል ሺ ጊዜ ዝጊብኝ
ልሙት
የሚወድሽ ልቤን ላንቺ እንዳስገዛሁት
ልብ አ'ርጊልኝ ታዲያ ለ_ፍ_ቅ_ር ነው ያልኩት
አንቺማ አንቺ ነሽ ፍቅር የማይገባሽ መውደድ የማታውቂ
ባፈቀረሽ ሰው ላይ ያላንዳች ምክንያት ምታፌዥ ምትስቂ
አንቺማ አንቺ ነሽ ቀጥረሽ የምትቀሪ የሚወድሽን ሰው
ድንጋይ ልብ የተቸርሽ ፍቅር የማይገባ ፍቅር የማይሰርፀው
እንዳ'ንቺማ ቢሆን
እንዳ'ንቺማ ቢሆን ድሮ ከበፊቱ
ይለይልኝ ነበር ይቆርጥልኝ ነበር ገና በጠዋቱ
ግን ፍቅር ነውና ካንቺ ጋር ያሰረኝ
ስወድሽ እንደኖርኩ ስወድሽ ይቅበረኝ
✍ #መኖር ደጉ
@getem
@getem
@gebriel_19
።።።።።።።።።።።።።።።።
ለፍቅር ከሆነ ሺ ጊዜ ልገፋ
ቀጥረሽኝ አትምጪ ልተክዝ ልከፋ
መውደዴን ስነግርሽ እንዳሻሽ ሳቂብኝ
ሺ ጊዜ ስደውል ሺ ጊዜ ዝጊብኝ
ልሙት
የሚወድሽ ልቤን ላንቺ እንዳስገዛሁት
ልብ አ'ርጊልኝ ታዲያ ለ_ፍ_ቅ_ር ነው ያልኩት
አንቺማ አንቺ ነሽ ፍቅር የማይገባሽ መውደድ የማታውቂ
ባፈቀረሽ ሰው ላይ ያላንዳች ምክንያት ምታፌዥ ምትስቂ
አንቺማ አንቺ ነሽ ቀጥረሽ የምትቀሪ የሚወድሽን ሰው
ድንጋይ ልብ የተቸርሽ ፍቅር የማይገባ ፍቅር የማይሰርፀው
እንዳ'ንቺማ ቢሆን
እንዳ'ንቺማ ቢሆን ድሮ ከበፊቱ
ይለይልኝ ነበር ይቆርጥልኝ ነበር ገና በጠዋቱ
ግን ፍቅር ነውና ካንቺ ጋር ያሰረኝ
ስወድሽ እንደኖርኩ ስወድሽ ይቅበረኝ
✍ #መኖር ደጉ
@getem
@getem
@gebriel_19