ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ከተጣሉ_ገፆች_መሃል

ፅኑ ቃል

          ቀኑ ቢተራመስ
በጠራራ ፀሃይ ጨረቃ ብትወርስ

በውድቅት ለሊት ላይ ፀሀይ ብትወጣ
ምሽቱና ቀኑ ሁሉም ቅጡን ቢያጣ
ጊዜው ተገልብጦ ጎልያድ ቢረታ
አልታዘዝ ብሎ ሙሴም ቢያመነታ
መልካም ሚያበጅ ሰው ውርደት ቢከናነብ
አንዱ ላንዱ ተንኮል ቢቀላለብ
ሺህ ዘመን ቢለወጥ
ሺህ ቀኑም ቢቀየጥ
ትላንት ያልኩሽ አለ ዛሬም እንደዚያው ነው
ድሮም እና አሁን ሁሌም 'ወድሻለው

ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
24👍13👎2🔥1😱1
#ከተጣሉ_ገፆች_መሃል

ምንም የለም
ምንም የለም
ሁሌ ከተባለ
በምንም የለም ውስጥ
አንድ ነገር አለ።

ዮኒ
     ኣታን  @yonatoz

@getem
@getem
@getem
👍6417🎉2
#ከተጣሉ_ገፆች_መሃል

ሚስቴን ዳርኳት

ዕፁብ ነው...
የሷ አፍቃሪያን አጃኢብ ያስብላል
መልኳ ተንኮለኛ ያየውን ይጥላል

ቀን ለኔ ወቶልኝ በሚስትነት ያዝኳት
ምዬ ተገዝቼ በወጉ አገባሇት
የሷ ማለት የኔ
የኔ ማለት የሷ
ሁኗል ከዚ ወዲህ
አፍቃሪዋ ሳይሆን
አፍቃሪያችን በዙ ሊባል ነው ከንግዲ።

ይህም ቢሆን እንኳን
አንዱ የሷ አፍቃሪ ቅናት የወረሰው
እሷን ሚጠጓትን ወንዱን የጨረሰው
ወደኔ ተጠግቶ
ሳይጥለኝ አንክቶ
እህቴ ናት ብዬ ማስወራቱን ጀመርኩ
መቼም ከመወጋት ወንድምነት መረጥኩ

አዬ...
አካል ቡጢን ፈርቶ በምላሴ ሸጥኳት
እህቴ ናት ብዬ እኔው ሚስቴን ዳርኳት

ዮኒ
      ኣታን
                  @yonatoz
@getem
@getem
@getem
😁4923👍20😱17😢5🤩3🎉2👎1
#ከተጣሉ_ገፆች_መሃል

የፊቱን እያየ የኋላውን ትቶ
ማንነቱ ጠፍቶት እልህ ጋ ተጋብቶ
          ጎጆውን ቀልሶ
ማን እንደነበረ ረስቶት ጨርሶ
የገዛ እልሁ ደፋው ከፊት ደርሶ።

ብላችሁ ንገሩ
ላገር ለመንደሩ
በምን ጠፋ ቢሉ!

ንሸጣ: ጋሽ ደበበ ሰይፉ (በምን ሞተ ቢሉ)


ዮኒ
     ኣታን   @yonatoz

@getem
@getem
@getem
👍148