ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
የባከነ ሌሊት!!!!
(በእውቀቱ ስዩም)
ወይ ሮንድ አላደርኩ
ወይ ኮኮብ አልቆጠርኩ
ወይ ደልቶኝ አልጨፈርሁ
ወይ ውስኪ አልተዳፈርሁ
የባለጌ ወንበር :ኮርቻ አልተሳፈርሁ
ወይ ሰአታት ቁሜ
ቤተክስያን ስሜ
ሰይጣን አላሳፈርሁ::
ሌቦች ደብድበውት
አንዱን ምስኪን ላሥር
ባምቢስ ድልድዩ ሥር
ቆስሎ የወደቀ
ገላው በላዩ ላይ :እንደጨርቅ ያለቀ
ፊቱ ተሸፍኖ : በደምና አቧራ
"በኡራኤል ርዱኝ " ብሎ የሚጣራ
ምስኪን አባወራ
ብብት ሥር ገብቼ
አፋፍሼ አንስቼ
ተሸክሜ አድኜ
ስፈልግ አምቡላንስ :ሲሻኝ ዶክተር ሁኜ
ወይ ምግባር አልሠራሁ
ወይ ጀብድ አልፍፀምኩኝ : ወይ ፅድቅ አላፈራሁ::
አንድ በትረ-ሙሴ
ሁለት ስስ አሎሎ
ከጭኔ መሀከል ሲያመሽ ተንጠልጥሎ
ሲባክን ዝምብሎ
" እሸኝ የኔ ጀግና እንደሰነፍ ቆሎ"
የምትል መለሎ
ልቤን ሳትሰውረው
አልጋየን ሳትሰብረው::
ወግ ቢጤ ሞንጭሬ: ፌስቡክ ላይ ሳለጥፍ
" እናትዋን ጨረቃ" የሚል ግጥም ሳልጥፍ::
አንዲት ሴት- አዳሪ :ቺቺንያ ምንገድ ላይ
እድሉዋ ሰባራ :ሰውነቱዋ አማላይ
ካፍያውና እንባዋ : ተጋግዞ ሚያረጥባት
ደምበኛ ስትጠበቅ :ደመኛ ጥሎባት
አምስት ደፋሪዎች : ከበው ሲያዋክቧት
ሲገፉ ሲስቧት
" እረ በናታችሁ በወላድ ማህፀን
እህት የላችሁም?" ብላ ስትማፀን
ልመናዋ ስቦኝ
እንዳበጀ በለው : በደሏ አንገብግቦኝ
ከሁዋላ ደርሼ
ነበልባል ለብሼ: ነበልባል ጎርሼ
እንደብሩስሊ: እንዳየሩ ጋኔን
እግሬን ወንጨፍ ወንጨፍ
ወዝወዝ ወዝወዝ ጎኔን
በማረግ ቃኝቼ
ከሁዋላ ነው ሲሉኝ ከፊት ተገኝቼ
ካምስቱ መከከል አራቱን ነጥየ
ከቻልኩ በካራቲ ካልቻልኩ በሳቅ ጥየ::
ድል ሳላስመዘግብ
ውጥረት ሳለረግብ
ወይ ታሪክ ሳልሰራ -ወይ ታሪክ ሳልዘግብ
ያለምንም ጣጣ : ያለምንም ፀጋ
አለሰበብ መሽቶ አለሰበብ ነጋ::

By bewuketu seyoum

@getem
@getem
@paappii
78😁23🔥13👍6😢2
የአብስራ ሳሙኤል

ከቤትሽ በር ላይ
ትንሽ ዘምበል ብሎ ቅጠሉ የረገፈ
አንቺ ስትወጪ የተንዘፈዘፈ
በአራራይ ዜማ
ጎንበስ ቀና ብሎ ውዳሴ የሚያሰማ

ዛፍ ካየሽ.......እኔ ነኝ
ደሞ ጮራ ከቦሽ
የጸሀዪ ንዳድ ገላሽን አልቦሽ
ማረፊያ ፍለጋ የተቀመጥሽበት

ስራ የፈታ ድንጋይ የዱርዬ መንበር
የኔ ገላ ነበር
ወይም ባለፈው 'ለት
በዕለተ ሰንበት ልደታን ስትስሚ
የተሽኮረመምሽው ምርቃት ስትሰሚ
ምንም ሳትሰጪ ሳትመጸውቺ
ህይወት ህይወት ጸዳል ለምትሸቺው ላንቺ

አሜን ሳትይ እንኳ የመረቀሽ ለማኝ
እኔ ነኝ

እናልሽ መቅደሴ
ሴያሻሽ እንደ ታዛ ሲያሻሽ እንደ ወንበር
ደጀ ሰላም ወድቆ ሲመርቅ የነበር

ከጎጆሽ ባይመጥን ከልብሽ ባይሞላ
በሄድሽበት ሁሉ በአምሳል እያጠላ

እንደ ንፍቀ ክበብ ሲዞርሽ የሚገኝ
እኔ ነኝ

@getem
@getem
@paappii
46🔥5👍1
አንዲት ምስኪን ሀገር
.
.
.
ሙሾ እያወረደች ነጠላ አዘቅዝቃ፤
ኩርማን ስትለምን ከማጀቷ ርቃ፤

መኖር ታክታ ክንዷ ዝሎ፤
በእንባ ብዛት ፊቷ ከስሎ፤

ሰላምን ተርባ ተሰብሮ መንፈሷ፤
በላይዋ አለቀ የዝን ጥቁር ልብሷ፤

ቀኝ ጎኗ ሲድን ግራዉ ይታመማል፤

መዳንን ስትሻ ሀኪሙ ይጠፋል፤
መድሀኒት ቀማሚ በሀገሩ ጠፍቶ፤

ቁስሏ ሲያመረቅዝ ህመሟ በርትቶ፤
ከቤቷ እየመጡ ይማርሽ ይሏታል፤
መድሀኒቷን ነፍገዉ ፈዉስ
ይመኙላታል።

በዔደን ታደሰ
@ediwub

@getem
@getem
👍4830😢5🔥2
" በረከተ-መንግስት"
                   ( ግዮናይ ነኝ)!፧
ምስኪን ያገሬ ሰው...
ቀኑን ሲሮጥ ውሎ  ሌሊት ይሸሸጋል፣
ተፈጥሮ ነውና...
በወፎች ዝማሬ   አይቀርም ይነጋል።
ይኸው ደሞ ነጋ...
መስከረም ይመስል  መድፉ ተተኮሰ፣
ከምንሸሽበቱ...
እየተከተለን   ውጊያው ተለኮሰ።
* * *         * * *         * * *
ይኸውና ሞርተር...
አዲሱን ቆርቆሮ  ባንድ'ዜ ቀደደ፣
እናት ታለቅሳለች...
የዘመናት ወዟ    ቤቷ እየነደደ።
ሰብአዊነት ጠፋ...
እንደ ውሻ ሆነ  የህዝቤ ክቡር ደም፣
ለቀብራችን እንኳን...
በነጋሢ ቄሳር  ለቅሶ አልተፈቀደም።
* * *         * * *         * * *
እርሻ የሄደ ሰው...
ቀንበር ተሸክሞ   በወጣበት ሲቀር፣
ምን እናደርጋለን...
ለላይኛው ጌታ   ከማዳኘት በቀር።

@getem
@getem
@getem
😢3227😱1
ምን አጥፍተን ይሆን
.
.
ዳገቱን ስንወጣ ወድቀን ተነስተናል፤
ከተራራው አናት አብረን ተጉዘናል፤

የጠዋቷን ፀሐይ በደስታ ሞቀናል፤
በዉቧ ጨረቃ በፍቅር ደምቀናል።

ግና ናፍቆቴዋ................

በዛች የቀን ምራጭ ሰይጣን ሹክ ቢልህ፤
ፈጥነህ ተቀበልከዉ እሺታህን ሰጥተህ።

ከእግዜር ተጣልቼ ቀኒቱን ጠላኋት፤
ባትፈጠር ብዬ አምርሬ ረገምኳት።

እናም አካላቴ ምን ተሰምቶህ ይሆን?
አትፈልጊኝ ስትል ሀዘን ገብቶህ ይሆን?

እኔማ ናፍቆቴ.................

ምክንያቱን ሳላዉቀዉ፤
አንተም ሳትረዳዉ።

እንለያይ ብለህ ከጎኔ ስትርቀኝ፤
በላዬ ተንዶ ምድር ተደፋብኝ፤

የማደርገዉ አጣሁ ቀኑ ጨለመብኝ፤
ብልሀቴ ጠፍቶ ማጣፊያው ራቀኝ።

ትናንት የቀኑብን ዛሬ እያሸሞሩ፤
ተለያዩ ብለዉ እንዲሰማ ሀገሩ፤
በቡና ሸፋፍነዉ ለፍፈዉ ነገሩ።

ሙጫ ነች እያሉ ፍርድ ይበይናሉ፤
ህመሜን ሳያዉቁ እንዲህ ነች ይላሉ።

ካንተ ጋ አብሮ ሄዷል ፈገግታና ስቄ፤
ዘወትር የምኖር ብሶቴን አምቄ።

ምን አጥፍተን ይሆን ?
እንዲህ የተቀጣን ?

እንደዉ በደፈናዉ በቃችሁ የተባልን፤
በናፍቆት ችንካራት የተቸነከርን።

መንገድህን መርጠህ ከእኔ ብትሸሽም፤
ተስቶህ ነው እንጂ በደልከኝ አልልም።

ዔደን ታደሰ
@topazionnn

@getem
@getem
43🔥4👍2
የአብስራ ሳሙኤል

፩.
ከቀጠራት ካፌ 
የአባቧዋን ገላ እየቀነጠሰች 
ጥሏት ከሄደበት 
በሀሳብ ተከትላው በሀሳብ ተመለሰች 
ያልጠጣውን ቡና እንፋሎት ታየለች 
ጠረኑን ቀላቅሎ ብን'ብሎ ሲጠፋ

እንደ ጠዋት ጤዛ እንደ ቀቢጸ ተስፋ 
የመሄዱን ዳና እያመሳሰለ 
ከመኖር ጎደለ
―✦―
፪.
እንባ አቅርሯል አይኑ 
ዞር ብሎም ለማየት አልቀናም ልቡናው 
ያውቀዋል ህሊናው 
ሰው አልመጠናትም 
ያቀፈችው ሁሉ ትከሻው አልሞቃትም 
አትገባም ለሱ 
ሰው አልሆነም እሱ 
ቢጽፍላት ቢቀኝላት 
እልፍ ግጥም እልፍ ቅኔ 
መልኳን ተሳልሞ መመለስ ነው 
ቃል አያቅም የ'ሱ ወኔ
―✦―
፫.
እናም እሷም ካለችበት እሱም ከሄደበት 
በቀስተ ደመና አድማስ የሚያጣምር 
የማይኖሩት ፍቅር 
ለምትኖረው ህይወት እስትንፋሱን ቸረ 
ሄደ ያለችው ገላ ሲመራት ነበረ
―☾―

@getem
@getem
@getem
40👍5🔥1
( ከእምነቴ እኩል )
==============

እኔ ብኩኑ ሀሳበ ብዙ
ድንጉጥ ጭንቀታም
እምነት ሸክፌ በጽናት መንገድ
ግን አልበረታም ....

ባርያው ነኝ እያልኩ የታጋሹ አምላክ
ሁሌ የምቸኩል
እንደ ፈቃድህ ብዬ እየጠየኩ
ምላሽ ምጠብቅ በራሴ በኩል
ለካ ፍርሀቴ
ገዝፎ አድጎብኝ ነው ከእምነቴ እኩል !!

By @kiyorna

@getem
@getem
@paappii
48👍12🔥5
#ፀጉር_ክብር_አያውቅም

ቅሉ በርሃ ነው
የጠጉር ዳና የለው ብለሽ አጣጣለሽኝ
አጃይብ አንችዬ እጅግ አስገረምሽኝ
እንደኔ ዓይነቱ
እርግጥ አልሞላለት ፈፅሞ አልታደለ
ክብር አያውቅ ፀጉር
የኔን እራስ ጥሎ ቂጥ ስር ነው የበቀለ

ወድጄ አይምሰልሽ
.
.
[ ጥሩቤል ]
@ebuhbhr

@getem
@getem
@getem
😁5023👎5🔥1

    የአብስራ ሳሙኤል
         ⁂

ለነፍስህ ቅሪት ምን አለህ
ማለፊያ ምግባር ምን ሰራህ
በኖርክባት ስንዝር እድሜ
ምን'ን ዘርተህ ምን አፈራህ

እንዴያው ሲያስበው ይጨንቀኛል
ነፍሴን እንዳል'ጥላት እፈራለሁ
ፈራሽ ገላ ተጫምቼ
ስንት ዘመን እኖራለሁ

የእንባ ብዕር ከሚጠቀስበት
መዝገብ እንዳላሰፍር
መሾ ከሚወርድበት
ክብሬን እንዳላሳፍር

ለመንግስትህ እጨኝ ባልልም
ከመከራው ጠብቀኝ
የኔ እውቀት አያድነኝም
መልካሙን አንተ አሳውቀኝ

ለማትሞላ ጎደሎ ምድር
ህልም ነው ወዳልከው ስትለፋ
ተስፋ ነው ወዳልከው ስትገፋ
ማረፍ አይቀርምና ታርፋለህ
መሞት አይቀርምና ትሞታለህ

ማለፊያ ምግባር የሚሆን
ለነፍስህ ቅሪት ምን አለህ

የበገና ክር መወጠር
ለዜማው መጣም ነው'ና
ምስገና መባ እንዲሆን
የህይወትህ ጥኡም ቃና

ለመንግስትህ እጨን ባንልም
ከመከራው አንተ ጠብቀን
የ'ኛ እውቀት አያድነንም
መልካሙን አንተ አሳውቀን

        ⁂
ለነፍስህ ቅሪት ምን አለህ ?


@getem
@getem
@getem
51🔥3🤩1
"ባሏን በሞት ያጣች ሴት ደብዳቤ"
.
ከገነት ላለኸዉ
.
የ'ግር እሳት ሆኖ ቢገርፈኝ መለየት ፍም እሳቱ፤
ልቤን አቀጣጠላት የናፍቆትህ ስር ግለቱ፤

በዛች የቀን ጎዶሎ ጥቁር ሞት አንተን ሲጠራ፤
እኔንም ጠርቶኝ በነበር ብጓዝ ከፍቅሬ ጋራ፤

ካንተ መራቅ አይሆንልኝ፤
ሌጣ ሆኜ አያምርብኝ፤

ዘወትር..መቃብርህን አቅፌ ስስም 'ዉላለሁ፤
ነጋ ጠባ..ስምህን ስደጋግም አድራለሁ፤

ያዩኝ በሙሉ.........

አበደች እያሉ ሲያሸሙሩብኝ፤
ከመቃብር አድራ ተለከፈች ሲሉኝ፤

መች ጆሮ ሰጠሁኝ መች አዳመጥኳቸዉ፤
ሞቷል እርሽዉ ሲሉኝ ላይኔ ጠላኋቸዉ፤

አይገባቸዉማ..........

በድኔን አስቀርታኝ መከረኚት ልቤ፤
አብራህ እንደሄደች አያዉቁም አሳቤ፤

ነፍሴ ከነፍስህ ጋር እንደተሳሰረች፤
ዳግም ላትነጠል እንደተጋመደች፤

ከጎኔ ባለገኝህም አይዞሽ ባትለኝ አንዴ፤
ጠረንህ ቢናፍቀኝም ባታባብለኝ ዉዴ፤

መቼም ላይጠፋ ከእኔነቴ፤
ዛሬም ህያዉ ነው ፍቅርህ ናፍቆቴ።

በዔደን ታደሰ እንደተፃፈ
@topazionnn

@getem
@getem
23😢9🤩2👎1
መኖሬ ከሆነ


እግሬ እንዳይራመድ
ልቤ ሲያጠምድ ወጥመድ

ልርቅ ስል ከሁሉ
ሲቀርቡኝ በሙሉ
አሉልኝ ያልኩኝ ለት
ብትንትን ሲሉ

በቅፅበት ደስታ
ስረሳው ሀዘኔን
ትንሽ ፈገግ አልኩኝ
ላነባው ዘመኔን

ወይ አለምን ንቄ
አልመነንኩ ከደብሩ
ወይ አልተሳካልኝ
አልተመቸኝ ምድሩ

መኖሬ ከሆነ ይቅርብኝ
ግድየለም ውሰደኝ እግዜሩ ።

By ኢዮብ_ዮሚን

@getem
@getem
@paappii
51😢7🤩1
ጥራታቸውን የጠበቁ የአውሮፓ ቦንዳ አልባሳት እና ጫማዎች መሸጫ 👌👏

አድራሻ 24 ሲድራ ሆቴል ጀርባ ወደ 40/60 መግቢያ 20 ሜትር

🤳 0913803516
7🔥3👍1
" አሜን"
          ( ግዮናይ ነኝ)!፧
አንቺ ጋር ለመኖር...
ሺ ቁልቁል ወርጄ  ብዙ ዳገት ወጣሁ፣
ዳኛ ሳይፈርድብኝ...
እንደ ወንጀለኛ    በኑሮ ተቀጣሁ፣
ያ'ርባ ቀን ዕድሌን  እጣ ፈንቴን አጣሁ።
  *                  *                  *
ህይወትን ተራብኩኝ...
እንጃ ስለ ፍቅር   ጥላቻን ተጠማሁ፣
ይኸው ደሞ ዛሬ...
እንለያይ የሚል   ካ'ንደበትሽ ሰማሁ።
አሜን ያደርግልኝ...
እዛ ማዶ ልጓዝ   ፍቅርሽን አልፌ፣
(አልጋዬ የት ነበር?)...
እስኪ ጋደም ልበል  ናፍቆኛል እንቅልፌ።
   *                  *                  *
ሰውነቴ ሁሉ...
እንደ ብሉይ ኃጢያት  ለምጻም ሰው መሰለ፣
ፈጣሪ ያውቀኛል...
ህይወቴ ላ'ንቺነት   ብዙ እንደ ቆሰለ።
ልሽሽ ካለሽበት...
ምድር እስከምታልቅ  በሌትና ቀትር፣
ባህር እንኳን ባገኝ...
ሙሴ ይሰጠኛል   የመክፈያ በትር።

@getem
@getem
@paappii
33👍2🔥2🤩2
ድክም ብል በሂወት መንገድ
እግሬ ቢዝል ብሰናከል
ቆፈን ብለብስ ለገላዬ 
ቁራሽ ዳቦ ብከለከል
ቀን ቢገፋኝ ካለሁበት
ከከፍታ ብወረወር
"አትመጥንም" ብባል በአፍ
ከአመት አመት በቀን በወር
አይኔ ደምን ሰርክ ቢያነባ
እቅድ ግቤ ቢፋለስም
ዳና ትግሌን አደብዝዘው
ያለ ስሜ ቢሰጡኝ ስም

አትጨናነቂ
ዝምብለሽ ሳቂ!

አታውቂምና ነው!
ቀን የገፋውን ሰው ቀን እንደሚያነሳው
ፈጣሪ ላልከዳው እሱ እንደማይረሳው

አታውቂምና ነው!
ዝቅ ያለ ሰው ሁሉ ከፍታ እንደሚያገኝ
ማርያም
ማርያም ላለ ፈጣሪ እንደሚገኝ

አታውቂምና ነው!

ሞን ያስለቅስሻል ለምን ትጨነቂ
ሁሉ በርሱ ይሆናል ዝም ብለሽ ሳቂ
ቀን ሳይገፋ አያልፍም ቀን
አልፈጠረብሽም ምንድነው ሰቀቀን

ለኔ ብለሽ አትድከሚ
አይብረድሽ ፍርሃት ቁር
ጊዜ አይፈጅም ለመልስማ
ካምላክ ሄጄ ብቆረቁር

አትጨናነቂ
ዝም ብለሽ ሳቂ!

ተስፋ መቁረጥ አይነበብ ካካል ገፅሽ ከመልክሽ ላይ
ሀይል ብርታቴ ይጨምራል የፊትሽን ፈገግታ ሳይ።
አንዲት ቅንጣት እንባ እንዳላይ ተደርድሮ ከጉንጭሽ ስር
ቀን እንደሆን አመሏ ነው ልታነሳ ምትሰረስር።

አትጨናነቂ
ዝም ብለሽ ሳቂ!


ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
38👍5🔥1🎉1
የሚጠቅመኝን ፥ አልወደድኩትም
አልጠቀመኝም ፥ የወደድኩትም ።

ከማን ጋር ልሁን ?
ከምወደው ? ወይስ ... ከሚጠቅመኝ ጋር ?
ተንገዳገድኩኝ ፥ በጭንቀት ስካር !

የቱን ላስቀድም ? የቱ ይበልጣል ?
የቱ ያከስራል ? የቱ ያወጣል ?
እንዴት የሰው ልጅ
ምርጫ ተሰጥቶት ፥ ነጻነት ያጣል ?

ፈጣሪ ራሱ
ከዚህም ከዚያም እያማረጠኝ
መሐል መንገድ ላይ ከሚያፋጥጠኝ
ምናል ከሁሉም ፥ ሁሉን ቢሰጠኝ ?!

By Hab HD

@getem
@getem
@paappii
65👍13😁6🔥3🤩2😱1
የአብስራ ሳሙኤል

እስቲ ትንሽ እንፋለስ
እስቲ እግዜ'ርን እንሞግተው።
ህሊና ያለው ፍጡር መቼም
መልስ ቢያጣም ጥያቄ አይተው።

ስለምን ሰው እንደ ቅጠል
በየመስኩ እረገፈ?
ባለቤት አልባ ይመስል
በ"እኔ ነኝ" ባይ ተቀጠፈ?



ይቆረቁራል ጎዳናው
ደምና አጥንት መሰለኝ...
እንዴት አድርጌ ዝም ልበል?
ውስጤ "ጩኽ! ጩኽ!" እያለኝ!



ስለምን ጡት ያልጠባ ህጻን
ከእናቱ እቅፍ ተነጠቀ?
ለነፍሱ አጽናኝ ሳይኖረው
"በረብ! በቁር!" ማቀቀ...
ወደቀ...ወደቀ...ወደቀ...



ስለምን ምስኪን እናቱን
በኑሮ አካልበህ ደፋሀት?
የልጇን ጠረን ሳጠግበው
ከመቀመቅ ገፋሀት?



ህመም ሲቃ ጩኸት ነው
ንፋስ የሚንሾካሹከው...
እንደምን ይመጣል ብዬ
ምእመንህን ልስበከው?



"ያልፈል" ብሎ ቢጽናና
ቀን �ይዞት እያለፈ፤
ስለምን አማኝ ከእምነቱ
መፈተንን አተረፈ?



ዝምታው ተሰማኝ
አሁን ነገዬን ማሰብ ከበደኝ።
በየመስኩ በጎዳናው
የቁስል ጠረን እያወደኝ...



ከታሪክ አመሳክረናል
ወንጌል ላይ ነው ተአምርህ?
በዘመን ገጽ ስንቱን እንዳለፈ
እየነበርክ ምኑን ልንገርህ?



ስለምን ቸልታህ በዛ?
የስምህ ትርጉም ቀለለ?
በረሀብ ይሞታል ህዝብህ 
ስለ እግዘብሔር እያለ! 

— 

ይቆረቁራል ጎዳናው 
ደምና አጥንት መሰለኝ... 
እንዴት አድርጌ ዝም ልበል? 
ነፍሴ "ጩኽ! ጩኽ!" እያለኝ
. . . . . . . . . . . . .


@getem
@getem
@paappii
34🔥5😢3👍2
በምድር ፍትህ የለም
      .........................
ለእውነት የሚቆም ራሱን የካደ
ከራሱ አስበልጦ አምሳሉን የወደደ
የአዳም ዘር ሆኖ በምድር ስለሌለ
ፍትህ በቃል ብቻ ተመዝግቦ ዋለ::
              ፠፠፠፠
ባለንባት አለም የኔም ያንተም ጠባይ
ለምድር ይቅርና ያስፈራል ለሰማይ::
እናም!... . 
      ፍትህ ለእገሊት!
ፍትህ ለእገሌ!
     ፍትህ.......ፍትህ......!
ፍትህ........!
እያሉ መጮህ አንዳችም አይሰራም
እንኳንስ ለሰው ልጅ
ምንኖርባት ምድር ለንጉስ አትራራም፡፡

By @Abuugida

@getem
@getem
@paappii
46😢14👍4🔥4
የአብስራ ሳሙኤል

ቀኑስ ከዳኝ እንዳላቅፍሽ 
እንግዲህ ህልሜን ልለመነው 
ወይ ወድጄሽ ላይሞላልኝ 
ያገናኘን ለምንድነው 

— 

ኪዳን አለኝ ከለሊትሽ 
ምስኪን ልቤን ሊያስተሳስር 
በሰመመን ያደርሰኛል 
ከመዳፍሽ ከእግሮችሽ ስር 

— 

ወብ ፈገግታሽ ተስረቅርቆ 
እንደ ንፋስ ሊዳብሰኝ 
ከጽናትሽ ተስፋን ሰርቆ 
ለንጋት ጀንበር ሊያውሰኝ 

— 

ከልካ ይ የለው አጋጅ የለው 
ወይ አይመሩት ወይ አይገሩት 
ተኝቶም ቢሆን ይሄዳል.... 
ልብ እንደው ወዳ 'አፈቀሩት 

— 

አይዞሽ እዛ ትግል የለም 
አረፍ በይ ከታዛው ስር 
ህቡእ ፍቅሬን ታገኛለሽ 
ህልሙን ከአንቺ ሲያስተሳስር 
የእንቅልፉን በር ሲሰረስር።

— 

አይዞሽ እዛ መራዝ የለም 
የተራበ ሁሉ ይጠግባል 
በህይወት የጠወለገው 
አንቺን አይቶ ልቤ ያብባል 
ተስፋ ምኞት ይቀለባል።

— 

**ኪዳን አለኝ ከለሊትሽ 
ምስኪን ልቤን ሊያስተሳስር 
በሰመመን ያደርሰኛል 
ከመዳፍሽ ከእግሮችሽ ስር 

— 

ቀኑስ ከዳኝ እንዳላቅፍሽ
እንግዲ'፣ ህልሜን ልለመነው
ወይ ወድጄሽ ላይሞላልኝ
ያገናኘን ለምንድነው.......


.    .    .    .    .    .    .    .    .    .    .     .   .

@getem
@getem
@getem
32🔥5👍1😱1
ጨዋታዉ ፈረሰ
.
.
ልጅነቴ ልጅነትህን፤
       ለጋነትህ ጮርቃነቴን፤
በትዝታ እየቃኘሁ፤
        ሳቃችንን እየሰማሁ፤
በትዉስታ ምልሰት፤
       በጥሞና ስመለከት።
በድንጋይ ከታትፈን፤
           ማባያ ጨምረን፤
መረቁን ከልሰን፤
          የሰራነዉ ጎመን።
ለሚመጣዉ ዘመን፤
          የእቃቃ ሰርጋችን፤
ሚዜ ስናዘጋጅ ፤
         መኖርን ስንዋጅ፤
ወረቀት ቀዳደን፤
            ቦጭቀን፤ 
ቦጫጭቀን፤
           እየጎዘጎዝን፤
ሰፈር ስናበላሽ፤
       መንደር ስናቆሽሽ፤
ቡና አፍልተን፤
        ቁርሱን በልተን፤
ደግሞ ስንጣላ፤
        ይጠፋናል መላ፤
ኩርኩም ስንቃመስ፤
          ጮኸን ስንዋቀስ፤
መተቃቀፍ በማግስቱ፤
         መንከባለል በክረምቱ፤
ስንቱ አለፈ በጊዜያቱ።
              የእቃቃ ቤታችን፤
ያለምነዉ ኑሯችን፤
          ጨዋታዉ ፈረሰ፤
ዳቦዉ ተቆረሰ።

በዔደን
ታደሰ
@topazionnn

@getem
@getem
55🔥4👍3
የአብስራ ሳሙኤል

እንዲያው እንደ'ድንገት፣ እንዲሁ እንደ'ሁኑ፣
ደርሰን ስንገናኝ አይንሽን ብፈራ፣
"እረስቶኝ ነው" ብለሽ እንዳት'ጨነቂ፣
"ይጠላኛል" ብለሽ እንዳትጠብቂ።

* * *

አይን የማያይው፣ ጆሮ የማይሰማው፤
የልቤን ትርታ አፍኜ በልቤ፣
ወንድነት ቢያንሰኝ ነው፦
አይኔን መሰብሰቤ፣ ፊቴን መሸበቤ...

* * *

እንዲያው እንደ'ድንገት፣
እንዲያው እንደ'ነገው፣
ብዙ አመታት አልፎ፣ ቀን እና ቀን ተጠላልፎ፣
አዲስ ታሪክ ጽፎ፣ አዲስ ህይወት ነድፎ፣
መልክሽ እንደ አደይ፣ እንደ ጤዛ እረግፎ፣
የልጅነት ጊዜ ጭዋታና ፍቅሩን ስናፍቂ...

"ይጠላኛል" ብለሽ፣ "ይረሳኛል" ብለሽ እንዳትጠብቂ!

* * *

የዕድሜ መሰላሉን ብወጣ፣ ብሄድም፣
ህይወትን ብጓዘው፣
አለም ካጣበቡ እልፍ ሴቶች መሀል፦
ያንቺ ሳቅ ብቻ ነው፣ ቀልቤን የሚይዘው።


@getem
@getem
@paappii
35🔥5