ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
------ነው የምሆነው

"በሰማዩ ፈረስ ተጓዥን አድርሼ
በተካንኩት ጥበብ ታማሚን ፈውሼ
ለሀገሬ ቆሜ ማስጠራት ነው ስሜ
መሀንዲስ መሆን ነው የወደፊት ህልሜ
ብዬ ነበር ያኔ በልጅነት ወዜ
ሳድግ ምሆነውን በተጠየቅሁ ጊዜ።
ጥብቅና በመቆም ፍትህ ለተጠማ
እውነት እሰብካለሁ በውሸት ከተማ።
ብልሃተኛ ሆኜ ችግርን መርማሪ
በነጋ በጠባ ሰላምን አብሳሪ
ጥበብን ከቀለም ለትውልድ ነጋሪ።
ብዬ ነበር ያኔ በልጅነት ወዜ
ወዳጆቼ ሁሉ በጠየቁኝ ጊዜ፡፡
ወጥቼ እያደርኩ ለሀገር እሰ'ዋለሁ
ባይኖረኝም በትር ህዝብ አሻግራለሁ
ፍጥረቴ ሰው አይደል ለሰው እኖራለሁ።
አቀነቅናለሁ ለምንዱብ ድምፅ ሆኜ
በጥበቡ አለም ገሀዱን ተውኜ
በሰፈርኩት ቁና 'ሰፍራለሁ መዝኜ፡፡
በፍ'ቅር ሮጣለሁ ለሰንደቅ ዓለማ
የእምዬን ክብር ለአለም እንዲሰማ"።
ብዬ ነበር ያኔ በተጠየቅሁ ጊዜ
የወደፊት ህልሜ በልጅነት ወዜ።
            
by Abuugida

@getem
@getem
@getem
👍3210🔥1🤩1

ካባ ጫንኩኝ ለሷ ብዬ፡
ዘውድ ገፋች ለኔ ብላ፥
የኋላዬን ኋሏ ትቼ
የተክሊሉን ምኞት ጥላ፤
አብረን ቆመን አስቀደስን
ተዋሃድን በኢየሱስ ደም፡
እሰይ አለፍን ተያይዘን
ያቃቃረን ወጥመድ ይውደም።

ሳያት ግና ደነገጥኩኝ
የናፍቆቴን  ትንሽ ዞሬ
ይህ እምባዋን አላየውም
አብረን ሆነን እስከዛሬ
ጠይም መልኳ ማጀት ሆኖ
የባዶነት ግጥም ፅፏል
ወትሮ ሚስቅ ትንሽ አይኗ
ትኩስ እምባን አቸፍችፏል፤
መሪር ሀዘን የጥቁር ቅብ
የእምባ ጅረት ግድብ ላይኔ
ሀ,ለ የሚል፡ ቃል የሌለው
ያልተፈታ ባዶ ቅኔ።

ተሸበረ አንጀት ልቤ
ተሸሽጎ የነበረው
ፀፀት ወቶ በሀይል ገፋው፤
መቅደስ መሃል እንደቆምኩኝ
ካለውበት አለም ጠፋው።
ከሰማያት ሰማይ በላይ
በደመና ሽቅብ ሄጄ
ቁልቁል ነፍሴን ወረወርኩት፤
ከርሷ ጋራ ለመሆን ስል
አንድ ህልሟን ነው የነጠኩት።
ምንአለበት ፍቅር አይደለ
ባልቋደስ የሰው መባ
እንደህልሟ እናቷ ፊት
ተክሊል ደፍታ ብታገባ?

ምናለበት ባላገኛት
ባይበዛብኝ የኔ በደል
ለርሷ ሚሆን ትጉህ ንፁህ
በከተማው ሞልቶ አይደል?

ምን ነበረ ባላገኛት
ምን ነበረ ባልመኛት
እንዲህ እንዲህ ባለ ምሬት
ምትዋከብ ልቤ ጋለች
የኔ አበባ እኔን ስታይ
የውሸቷን ፈገግ አለች።

ከሰምኩላት
ወደኩላት
ንፁህ ፍቅሯ
መቅደስ መሃል
ዳግመኛ ልቤን ገዛው ፤
እዩዋት ጭንቄን ስታበዛው።
እዩዋት ፍርዴን ስታበዛው።

የዘመናት አንድያ ህልሟ
ያጠለልኩት እንደ ወንፊት
በምጢረ ተክሊል ከብሮ
መዳር ነበር አባቷ ፊት።
ላስተማራት የጌታን ቃል
ሽፍን አርጎ  ካለም ስጋት
ለውለታው ምላሽ ነበር
አቅፎ ስሞ ላሳደጋት።
ጥሎሽ ድግስ ብልጭልጩ
አይፈልግም ለምን ጥቅም
ካህን አይደል ካንድ ልጁ
ከክብር ውጪ አይጠብቅም።

እሷም ብትሆን አልማለች
አንድ እያለች አመታቷን
እንደ ባሪያ ወርዳ ኖራ
ዛሬ ልትወስድ ሽልማቷን
ብትመጣም እምቢ አለች
እኔም ክፉ እጇን ያዝኩኝ
የተክሊሉ ኒሻን ቀርቶ
ሽልማቷ እኔ ሆንኩኝ።

ለምን እኔን ?
ለምን ለሷ?
አዳፋ አይደል ማንነቴ
ንፁህ አይደል ገላ ልብሷ
እሰጋለው ዛሬም እንኳን
ማንነቷን እንዳልቀማት
ጭራሽ በቃው ለሽልማት?

እሺ እምባዋስ?
እሺ አባቷስ?
ወዳጅ፣ ዘመድ ጎረቤቷስ?

አይ እዳዋ

ዝቅ ብላ አንገት ደፍታ
ምሽት ገብታ በሌት ወታ
አንዴ ዳዊት አንዴ ጥምቀት
አንዴ ቅኔ  አንዴ ሰንበት
ብላ ኖራ ቤተ መቅደስ
እንደበራች የጧፍ ግማጅ
እምነት ፍቅሯን ሳትቀንሰው
ገላ ክብሯን ጠብቃ አድጋ
ሽልማቷ ፦ "ዘማዊ ሰው!"።

© @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
55👍18🔥4😢2
(የአብስራ ሳሙኤል)

በለስ ሆነበት
እውነት
ስትነግረው
ሰበረው
ውሸት ምን ያህል ውብ ነበረ
ተሰበረ
የነፍሱን ሀቅ
ሳቅ
ነጠቀችው
ነገረችው
የሄደ ጊዜ
ነጠላ ረግጦ
አማግጦ
ጭኗን ሲተካው
ምርጫ ሲያስመካው
ጠረኗን ተፍቶ
ትቶ
የሄደ ጊዜ
የሄደ ለታ
ተስፋዋን ትታ
ዘሟች ፍቅሩን
ክብሩን
ልጠብቅ ብላ
እኔ ነኝ አለች
ፍቅሩን የገፋው
ስቼ ያጠፋው
የማገጥኩበት
ቁስል የሆንኩበት
እንጂማ የእሱ
ጻድቅ ነው ነፍሱ
አያቅም ነበር ክፉ ተናግሮ
ስድብ ወርውሮ
አያይም ነበር የሌላ ገላ
ከእኔ ሌላ
እንጂማ የእሱ
ጻድቅ ነው ነፍሱ
ለመጣሁ ሁሉ ምን ሆነሽ ላላት
ለስምህ የጻፈች ገድል ነበራት
የምትነግረው
የምታበስረው
መቼ ሆኖላት ስሙን አጥፍታ
አውርታ
ለመጣው ሁሉ ትኩውለው ነበር
ክፋ ማን ነበር ?
እሷ
የረከሰች ነፍሷ
በነገረቻቸው ልኬት
አበጁላት ስፌት
ነጠላዋን ቀደው
ክብሯን ንደው
የውርደት ቃል ነሰነሱ
እንጂማ የእሱ
እንጂማ የእሷ
ጣት ቀስሯ አታቅ
ታማኝ ነች ነፍሷ
ብቻ ለሱ ነገረችው
ይመጣ ይሆን ብላ መሰል
የሱን ሀጥያት እሷ መምሰል
የሱን ውርደት ዝሙት ሀቁን
እንዳለቀሰች ተውሳ ሳቁን
ሱሪ አስታጥቃው
ቀሚስ መቅደዷን
መዋረዷን
ለጠየቋት ሁሉ
እምነቷ መቅለሉ
ለሱ ብቻ ነገረችው
ያዝን ይሆን ብላ መሰል
ጽድቋን ችራ
የሱን ሀጥያት እሷ መምሰል
ብትነግረው
ሰበረው
ውሸት ምን ያህል ውብ ነበረ
ተሰበረ
በሀቋ
ባዳፋ ሳቋ
ስሟን አጉድፋ ስም ብትቸረው
ረግጧት ሲሄድ
የምትጽፍለት ገድል ነበረው

By @yabisrasamuel

@getem
@getem
@paappii
👍2614🔥2
አምላኬ
ጣሉኝ አጣጣሉኝ ከሞት ተጋፈጥኩኝ
እንደ ቸርነትህ ሁሉም አልፎ ቆምኩኝ
ዕንባዬ ታብሶ ጤናዬ ሲመለስ
ለምን ይሆን እንደው
አናንቆ የገፋኝ ከበሬ ሚመለስ?
.
ታውቀው የለ ዐቅ እወነቴን
ስጠኝ እንዳልኩ ስንቴ ሞቴን
ታውቀው የለ የኔን ቁስል
ለምን መጡ ፈገግ ስል?

[ ጥሩቤል ]
@ebuhbhr

@getem
@getem
@getem
42👍26🔥12
(የአብስራ ሳሙኤል)

ሰውና አምላኩ ሸንጎ ገጠሙ
ዳኛ እንዲሆኑ ጻድቃን ታደሙ
ገብርኤል ክንፉን እያናጠፈ
ሰጋሪው ውሀን እየቀዘፈ
ጸሀይ ከገባኦት
ጌታ ከጸባኦት
ህያዋን ሁሉ ተሰበሰቡ
እንዴት የሰው ልጅ
ጣት ለመቀሰር ደፈረ ልቡ
ጌታም ከዙፋን ቢያቀውም ድሉን
ይሞክር ብሎ ፍጡር የድሉን
ሸንጎ ቀረበ እንደገደፈ
°°°°°°°°°°°እንደቀጠፈ
ጸጥ እረጭ አለ ከንቱው ጫጫታ
መቼም ታላቅ ነው በል ጀምር ጌታ

1 .ተከሳሽ

በዕለተ ሰንበት ከመቅደስ ቆሜ
ወንጌል ሳስተምር ስሰብክ በስሜ
አንዲት መጻጉ ፩፮ አመት ደም የፈሰሳት
በጄ ዳስሼ እንድፈውሳት
መባ ጸሎቷ እውን እንዲሆን
እስቲ ትጠየቅ
ይሄን መፈጸም ቅጥፈት እንደሆን

2.ከሳሽ

መቼም ታቃለህ የልብ የሆዴን
ኖረህ ቃኝተሀል የዕድሜ መንገዴን
ለታመመ ሰው
በሰአት ስቅታ ደም ለሚፈሰው
ልጅነት ሳቁን በህመም በጣር ለተነጠቀ
ሄዋን ገላውን ፍቅር ተገፍቶ እንደወደቀ
በጭቃው ሰርቶ ምኞት ሀሳቡን
ትንፋሽ ስትነሳው የህይወት ቀለቡን
ሸንጎ ብሰይም ከቶ አትገረም
አረፈድክ እንጂ ቀረ አልተባለም


3.ዳኛ

ግራና ቀኙን እንዳደመጥነው
ጥፋተኛ ነው ብለን የወሰነው
ጌታን አይደለም
ሞልታ አትሞላም አንዲ ናት አለም
ስለዚህ ጌታን ወደዙፋኑ አሰናብተናል
ያንቺንም ሀዘን ሰምተን አዝነናል

4.????

ግን ምን ይደረግ
አማኞች ፈራጅ በሆኗት አለም
አሜን ነው እንጂ ለምን! ቃል የለም

@getem
@getem
@getem
👍4515🔥3
**የአብስራ ሳሙኤል**

**የማርያም መንገድ ስጪኝ** 
ደክሚያለው አንቺው አውጪኝ! 
የማርፍ የምሸሸግበት 
ትንሽ ቦታ ትንሽ ህይወት 
የስቃይ አውዱን ማለፊያ 
የጊዜን መልህቅ መቅዘፊያ 
**የማርያም መንገድ አበጂ** 
የእድሜዬን ስንዝሯን ሂጂ 
ኩሬ ነው ያልኩት ባህር ካከለ 
ወዳጅ ነው ያልኩት ጦሩን ከሳለ 
በምን ልታገል አቅም አነሰኝ 
ያመንኩት ገላ ፍም ካንተራሰኝ 
ካልሞላ ጽዋው የዘር እዳዬ 
ወድቆ አፈር ይሁን በምን ተዳዬ 
በምን ልጋፋው በምን ልታገል 
መንገድሽን ስጪኝ እንድገላገል 
ደካማ ጎኔን ልመሽግበት 
ክፉ ቀናቴን ልሸሸግበት 
አላውቅም ልበል የለሁም ልበል 
አልችልም በቃኝ አቃተኝ ልበል 
ወደ ማረፊያው ምሪኝ 
ትግል ከሌለበት ጥሪኝ 
የአበባ ገላ ከማይረግፍበት 
ማላዳ ኮከብ ከማይጎልበት 
**ሁሉ ባይሞላም ከማይጎድልበት** 
**ምሪኝ ልሸሸግበት** 
**የማርያም መንገድ ስጪኝ** 
**ደክሚያለው አንቺው አውጪኝ!**


@getem
@getem
@paappii
38👍15🔥4🤩1
( ፍቅርማ .... )
===============

ፍቅር መጣ ፍቅር ጠፋ
አምና ከሳ ዛሬ ፋፋ
አንዱን ሳበ አንዱን ገፋ

ሲለው ሞላ ከዚያ አነሰ
አንዴ ጋለ አንዴ ጨሰ
እያለ ሰው ስንት ዘመን ተዋቀሰ
ግና እውነት ከከፍታው ማን ደረሰ ??

ፍቅርማ ....
ያኔ እንደገፋነው ተቸግሮ ሳለ
በእሾሀችን ውጋት እንደቆሳሰለ
አንገት እንደደፋ እንዳዘነበለ
የሚያወርደው አጥቶ
ዛሬም አርብ ላይ ነው ... እንደተሰቀለ !!

By @kiyorna

@getem
@getem
@paappii
101👍19🔥11😢7
የጉሊት እናት

መቀነቷን አጥብቃ ለልጆቿ ብላ
ኑሮን ለማሸነፍ የማይቻል ችላ
ከጠዋት እስከ ማታ እንጀራ ፍለጋ
ነገዋን ልትሰራ ጉልበቷ ሚተጋ
ብርቱ ሴት አንድ አለች
ጥቂት እቃ ይዛ መንገድ ዳር የዋለች፡፡
ዝናብ ሳያግዳት ሀሩር ሳይበግራት
ቁርስ እንኳ ሳትበላ ለልጆቿ እራት
ግልምጫው፣አሽሙሩ፣ሁሉን ተቋቁማ
በውድድር አለም ጨለማውን ቀድማ
ጎህ ሳይቀድ ወጥታ የምትገባ ሌሊት
ምስኪን እናት አለች የምትውል ጉሊት፡፡

ምንም ባታተርፍም ከባህሏ ሳትርቅ
ፍቅሯንና እቃ አብራ የምትመርቅ
የውስጧን አምቃ፣
በጥርሷ ደብቃ፣
ትልቅ ህልም ሰንቃ፤
ውላ የምትገባ በጥቂት ቸርችራ
ዕድሜዋን ሰውታ ቀልጣ ምታበራ
ከጉሊት መንደር ላይ አለች የሴት አውራ፡፡
            
                         by  @Abuugida

@getem
@getem
@getem
85👍12😢10
እንዲሁም ኑር ኑር ይለኛል

ልክ ያለው ዝናብ አይቼ
የነፋስ ሽውታ ሰምቼ
የፍቅር መንገድ እርምጃ
መምጣት እንደሆን ገምቼ…

ብን የሚል የሰው ለሆሳስ
ቢጻፍም በደብዛዛ እርሳስ
(ሳይጠፋ እንደሚነበብ)
ገምቼ…
ቢደርቅም ለምለም ቅጠሉ
(እግረኛ ትንፋሽ ሲገርፈው
የመኖር ድምፅ እያወጣ
በመኖር እንደሚረግፈው)

ሲወድቅ እየጠበቁ
ለጆሮ እንደሚበቁ
(የመርገፍ የማረፍ ቃሎች)
ለሰውም ይሰማ የለ
እንኳን ለግዑዝ ሌሎች

እያልኹ…

ከጥቁር ከነጩ ሕይወት
የቱ ክንድ ማን ይለየኛል
እንኳንስ ተፈቅሬበት
እንዲሁም ኑር ኑር ይለኛል።

By yadel tizazu

@getem
@getem
@paappii
37👍19🤩6🔥4
✿༺ *የአብስራ ሳሙኤል* ༻✿ 

❁───────⋆⋅☆⋅⋆───────❁ 
ሀገር ነኝ ይለኛል 
  ጠቦ እያየሁት በቋንቋ በመልኩ 
እኔ ሀገር የለኝም 
  ሆዳም የሚቀርጻት የሰፋት በልኩ 


⁜ [ ሀገር ነኝ አትበለኝ ] ⁜ 
⁜ [ ሀገር ሳትሆነኝ ] ⁜ 
ምስራቅ ሁነኝ ለህይወቴ 
  ጮራ ሆነህ ቁስሌን ዳሰው 
አዋሽ ያርግ ወይም ጣና 
  የጠማኝ 'ለት የምቀምሰው 


⋆⋅☆⋅⋆───────⋆ 
ልመንብህ እመንብኝ 
  ሳቅህ አሾህ እንዳያዝል 
ከዳሽን ይጽኑ ቃላትህ 
  ደጀን ሁነኝ እኔ �ስዝል 


♢ እንደ እንጦጦ ለሀፍረቴ ♢ 
♢ እንደ ኮንሶ ለማጀቴ ♢ 
ሳትሰስት ወይ ሳልሰስት 
  ልስጥ እልፋን እያበዛው 
በማለዳ ይክዳ ዕንባህ 
  እንደ ለምለም እንደ ጤዛው 


❁───────⋆⋅☆⋅⋆───────❁ 
✧ [ ሀገር ሁነኝ ሀገር ልሁን ] ✧ 
በማንም ልክ ያልተሰፋ 
  በማንም ልክ ያልቀረጹት 
በከንቱ ቃል የማይጸና 
  "ነኝ"! በማለት ያላ'ነጹት! 


⁑⁑⁑ 
ቢነጥፍ እንኳ 
  ያጠባን ጡቷን ሳንነክሰው 
መኖሪያ አለን ከተስማማን 
  ይብቃ በለኝ ያገሬ ሰው 


ባልኖርንበት ቢመዝኑን 
  በታሪክ ጭልፋ ቢጨልፋን 
አለት ሁነን አንድንጸና 
  ንፋስ ሆነው ለሚገፉን 

✧ [ ሀገር ሁነኝ ሀገር ልሁን ] ✧ 


"ነኝ" በሚል ቃል ያላነጹት 
ባቀረሸ ታሪካቸው 
  ባዳፋቸው ያልቀረጹት። 
 
❁・゚゚・*:༅。.。༅:*゚:*:✼✿ *:༅。.。༅:*゚・゚゚・❁

@getem
@getem
@getem
👍3423🔥8
( አልጠይቅም ..)
==============

ከርማ መጣች
ካሻት ውላ ደርሳ የትም
ምስኪኑ እኔ .....
"እንኳን መጣሽ" ካልሆን በቀር
"የት ሄድሽ ? "ግን ... አልላትም

ነፍሴ ሴትን ማፍቀር እንጂ
መጠየቅን ትታዋለች
ያቺ ሚስቴም 'ወዴት ልትሄጅ ? '
ስላልኳት ነው ወጥታ የቀረች !!

By @kiyorna

@getem
@getem
@paappii
56👍26🔥4😁4
ምን አረቄ ቢግፍ
ምን ጠላ ቢሞላ
ምን ቅራሪ ቢያገኝ
ቀማሹ ነው እንጂ … አይሰክርም ብርጭቆ ።

ለምን ?

ከተንገዳገደ … እንደማይተርፍ አውቆ ።

By yoseph workineh

@getem
@getem
@paappii
😁10250👍22🤩9
(የሞገሴ ልጅ)
ከቅንነት ማማ-
ከወዳጅ ልብ ላይ - ውብ ገላ ተሰርቶ፣
ብርቱካን ጨዋታ-
ፓፓያ ቁምነገር - አንዠርጎ አፍርቶ።

ትዝታ ጣለ እንጂ-
አሁንን ከነበር - ለይቶ ያወጣ፣
ተናፋቂ ፀባይ፣
ድንቅ ስብእናን - አየን ደርሶን እጣ።

ባለፉ ውብ ቀናት-
ደጃች ውቤ ሰፈር - ጎዳናዋ እስኪላጥ፣
ሳይደክመን የዞርነው፣
በሃሳብ ሽው ይላል - ከትዝታ ሊያሰምጥ።

ከዛ ቅን ልብ ላይ፣
ውበት ያለው ገላ - በአምላክ ተለጥፎ፣
አልያዝ አለ እና፣
ሳይበላ ቀረ ሳይዋጥ ተቀጥፎ።

By @tafachgitm

@getem
@getem
@getem
26👍9
✤✤✤✤✤✤✤✤✤✤✤✤✤✤✤
         (የአብስራ �ሳሙኤል)   

           ሀሌ �ሉያ ብርሀን ሆነ 
   ✦✦    ከጥርሶቿ ፍንጭት በኩል   ✦✦ 
         መሰከርኩኝ ፈገግ ብላ 
   ❁❁  በዕሳት ላንቃ ምድሩን ስኩል  ❁❁ 

           ሀሌ �ሉያ መብረቅ ሳማት 
     ✧     ሄሎሄ አሉኩኝ እኔ አያየው     ✧ 
           ለተአምር �ሲፈጥረኝ ነው 
     ✷     ከእሷ መሀጸን የተገኘው     ✷ 

           ሀሌ �ሉያ እናቴ �ናት 
     ✺     እልል አሉኩኝ ደስታ ቢያንቀኝ     ✺ 
   በረከቷ ምርያ ሀኖ ከመከራ ለጠበቀኝ 
   ✾✾✾✾✾✾✾✾✾✾✾✾✾✾✾✾✾

         ተአምር ነው ራዕይ ነው 
     ✸   ፋኖስ ሆነኝ አንዲት ነፍሷ     ✸ 
         ከህይወት መቅረዝ የሚኖሩት 
     ❃     ብርሀን �ነው እስትንፋሷ     ❃ 

         ወፍ ሰፈረ ከጎጆዋ 
✵   እ...ሽ አትልም መች ጨክና      ✵ 
             ስለመልኳ አዜ'ሙላት
     ✹ አዲስ ጀንበር ንጋት ሆና ✹ 

         ሀሌ �ሉያ እናቴ ናት 
     ❊     አጃኢብ አልኩ እኔ እያየው     ❊ 
           ለተአምር ሲፈጥረኝ ነው 
          ከእሷ መሀጸን የተገኘው      

✤✤✤✤✤✤✤✤✤✤✤✤✤✤✤✤

@getem
@getem
@getem
46👍7👎1
✤•⊰❉⊱•✤  የአብስራ ሳሙኤል  ✤•⊰❉⊱•✤

☆  * * * * * * * * * * * * * * * ☆
   ልብ በይ አለሜ
   ንጋት እንዳይመስልሽ ወገግ ያለው ሁሉ
   ጀንበር 'ና ጥላ ይመሳሰላሉ
☆ * * * * * * * * * * * * * * * ☆

☀️ 1.  ለምሳሌ  ☀️ 
༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻
አንቺ ከአለሽበት ሴት አዳሪ መንደር 
ለዕሳት ዕራት ገላ ዕሳት ሲንደረደር 
ጭኗን ለአደባባይ ከፍታ ያመሳቀለች 
ጡቷን ለጎዳናው ሸርፋ የሰቀለች 
ወንድ ስትራገም ደግሞም ስትጣራ 
መንገዱ ሆኖበት በዚህ ለሚያመራ 
༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻ 
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂ 
ማለዳ ጥላ ነው 'ሌት የህይወት መልኩ 
የቄሳር ለቄሳር ብለው ለሚረኩ 
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂ 
༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻ 
እናም በዚች መንደር 
ከምስራቅ የወጣ ንጋት ያልሽው ጀንበር 
ቀንና ለሊቱን እንዳፈራረቀ 
ላይነጋ ይበራል ላይመሽ የጠለቀ 
༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻

🌊 ምሳሌ.2  🌊 
~~~~ 
ጉሊት ከምታይው መደብ ከመደበ 
የሰማይ እጣቢ ፊቱ እየረገበ 
ሸርፎ ሲወስድበት 
ነጥቆ ሲያጎልበት 
~~~~ 
≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈ 
ጎርፍ አያሳድድም በውሀ ተሳፍሮ 
≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈ 
✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦ 
ተመስገን ነው ህይወት 
ተመስገን ነው ኑሮ 
✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦ 

🌫️ ምሳሌ.3  🌫️ 
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈ 
ብርሌውን አንቆ ከንፈሩን ለሚስም 
ተርዚና ወጥሮ ቅጠል ለሚቀስም 
ታታሪ ሱሰኛ ህላዌውን ገፊ 
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈ 
ጨለማ �ነው ሲልሽ 
ጀንበር ወቷል እያልሽ ሀቁን አትጋፊ 
▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃ 
ሳትሰክሪ አታ'ቂውም 
ሳትቅሚ አይገባሽም 
በሱሰኞች አለም 
▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃ 
✵ ✵ ✵ ✵ ✵ ✵ ✵ ✵ ✵ ✵ 
ሳይቃም አይነጋም 
ለሰከረ አይመሽሞ 
✵ ✵ ✵ ✵ ✵ ✵ ✵ ✵ ✵ ✵ 

.·:·. .·:·. .·:·. .·:·.
   ልብ በይ 'ሄን ሁሉ 
ንጋት እንዳይመስልሽ ወገግ ያለው ሁሉ 
.·:·. .·:·. .·:·. .·:·.

✧༺༻∞ ∞༺༻✧ 
አምኖ ላደረነው 
አሀዱ ወይ አዛን ማለዶ የሚያነቃው 
በቀን ለተረሱ 
✦⋆✦ ንጋት ነው ኮከቡ ✦⋆✦ 
✦⋆✦ ንጋት ነው ጨረቃው ✦⋆✦ 
∞•🌙•✧•☀️•✧•🌙•∞

@getem
@getem
@getem
60👍9🔥5👎2
¹
ገና ወጣት ንፁህ ነበር .....
ያለ  ግብሩ  ወነጀሉት ፤
ይግባኝ  ቢልም አልገባቸው
ግራ ቀኝ ሳይሉ ገ ደ ሉት ።
ከመሬት አጋድመው
አፈ ሙዝ ደግነው እየፎከሩበት
እሳት ያዘለ እርሳስ አርከፈከፉበት ።
²
የእሱስ ይሁን አንዴ ሄደ
እንደ ንፋስ ....ነፍሶ (ደርሶ)
አተረፈው ከሕይወቱ
(ከስቃይ አዳነው ሞቱ !)
ይብላኝ ለኗሪ እናቱ ።
³
ያኔ ፊትለፊቷ....
ልጇን  በመስቀል ላይ የቸነከሩት ለት
ያሰረችበትን የወላድ አንጀቷን
አላቀበለቻት ማርያም መቀነቷን ።
ውስጥ ውስጡን ተከፍታ በሀዘን ዝላለች
ስዕሏ ፊት ቆማ እንዲህ ትላታለች

“ለደረሰበት ምኑ ሊነገር ?
ታውቂው የለም ወይ የልጅን ነገር !?
የልጅን ነገር ታውቂው የለም ወይ ?
አይተሽ የለም ወይ?
ወስደው ሲያዳፉት
አስረው ሲገርፉት
በምስማር ፊትሽ ሲቸነክሩት
አካል ገላውን በደም ሲነክሩት
አይተሽ የለም ወይ?
ታመሽ የለም ወይ?
.
.
.
«ያንቺስ ተነስቷል በሦስት ቀኑ
የኔ ግን ይሄው ስንት ዘመኑ
በአካል በስጋ መች ይገለጣል
ትዝታው ብቻ በሌት ይመጣል ።
እስኪ ንገሪኝ ?
እነዛ አይሁዶች አንቺን
እንደ
ኔ በድለውሻል?
ልጅሽን ገድለው
አታልቅሽ ብለው
ከልክለውሻል?»

የታወቀ ነው.....
ደስታ ቢታሰር በሳቅ ያመልጣል
ሀዘን ፈንቅሎ በእንባ ይወጣል
(እሷ ትላለች ....)
«አልበቃ ብሎ ልጄን የነሱኝ
ባዋጅ በሕጉ እየመለሱኝ
እንደው በወጉ አላስለቀሱኝ »

ብዙ ቀን ሄዶ....ብዙ ቀን አልፎ
ከሕይወት ዛፍ ላይ ዘመን ረግፎ
ጎረቤቶቿ አብረው ሚኖሩ
በየሰርጉ ዳስ በየማ
በሩ
ድግስ ሲጠሩ
ትታደማለች ፤
እንደ ተፅናና ፈገግ ትላለች ።
ሀዘኗ ሳይሽር አውልቃው ማቋን ፤
ዕምባ ዕምባ ይላል ቢቀምሱት ሳቋን ።
እየዋሸች ነው እያስመሰለች
"እንደ ሚኖሩት ልኑር" እያለች ።
(አልተፅናናችም )

ተፅናናች እንዴ?
ፀኣዳ ቢሆን ከላይ ቀሚሷ
የሀዘን ማቋን ካልጣለች ነፍሷ
ውስጧ እንዳዘነ....
ልቧ ተከፍቶ ዘቅዝቆ ጥለት
‘ሞቶ መኖር’ ነው ....
“መፅናናት” ማለት ?
------
By @Bekalushumye
ነሃሴ 23 — 2016 ዓም

@getem
@getem
@getem
43😢25
...ስወድህ
እኔ አንተን ስወድህ መስፈርት አላወጣው
መልክና ቁመና ምንህን አላየው
እኔ አንተን ስወድህ ፍቅርህን ነው ያየው
መልክህ ምግባርህ ነው ሁሉን የሚገልፀው
እኔ ምልህ ሆዴ መውደድክን ልውደደው

By
@Hanipia


@getem
@getem
@getem
18👍4
እደውላለሁኝ የሚል ቃል ሳይወጣሽ
ስልኬን በፍጥጫ ቀለሟን ገፈፍኩት
ያለምንም ተስፋ በባዶ ሜዳ ላይ ተስፋዬን ሰነኩት
ጉድ እኮ ነው....
ወይ ደውለሽ ልቤ አረጋም
ወይ ትተሽኝ ቀኔ አልነጋም
እንዲ ስብከነከን እንደ ሰረቀ ሰው
ባጉል ተስፋ ኖሬ ሆዴን እንባ ባሰው።

ጉድ እኮ ነው....

ትንሽ ቆየሁና ስልኬን አስቀመትኩት
እርሳሴን አንስቼ ሃሳቤን አማጥኩት
ልግጠም
ልሳል
ልፃፍ
መርጊያ ምስ አጣሁኝ የመድረሻዬን ጫፍ

ልግጠምላት.....ስለምኗ?
ጠባይ መልኳን ወይንስ ላይኗ

ምኗን ልሳል.....ቀይ ከንፈሯን?
ሰውነቷን ወይንስ ጠጉሯን

ጉድ እኮ ነው....
እንዴት ልፃፍ ምን አንስቼ
እሷን ላግኝ እኔን ትቼ?


እጄን ላብ ጠመቀው
በጨበትኩት እርሳስ
ቆይ...ብትመጣስ?

ልትመጣ ነው!
ምን እየሆንኩ ልጠብቃት?
ምን ነበርኩኝ እሷን ሳቃት?

ኧረ እኔንጃ
ጉድ እኮ ነው....

ወይ አትደውል ወይ አትመጣ
እንዲ አያበድኩኝ ቀልቤን ስንቴ ልጣ

አሃ!
አሃሃ
አሃሃ አሃሃ አሃሃ!

አይ የኔ ነገር
ለካ አታውቀኝም...ኧረ እኔም አላውቃት
ታድያ ምን ቤት ሆና ልቤ ሚጠብቃት?

ጉድ እኮ ነው....

የት ነበር ያየኋት...?
ጎንደር ሸገር ጅማ ሽረ
የት ነው ያገኘኋት ልቤስ ነት ነበረ?

ወይ አታውቀኝ ወይ አላውቃት
ለምንድንው ምጠብቃት?

ዮኒ
    ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
69🔥11🤩6🎉4👍2👎1
የኔን ልንገርሽ
       አፈቅርሻለሁ፣
እየኖርኩኝ ምቼ          
      እጠብቅሻለሁ።
የኔን ልንገርሽ
      ሀሳቤ ሆነሻል፣
አካሌ ተወርሶ
  ልቤ ልብ ሰቶሻል።
የኔን ልንገርሽ
  ባንቺ ሰግቻለሁ፣
ምን ሆነች እያልኩኝ
   የትም አስባለሁ።
የኔን ልንገርሽ
ለሰው አወራለሁ፣
የኔ ናት እያልኩኝ
  ቀኔን አረዝማለሁ።
የኔን ልንገርሽ
መወሰን ከብዶኛል፣
እያጠፋሽ መተሽ
    ይቅርታ ቀሎኛል።
የኔን ልንገርሽ
ሳላጠፋ ይቅርታ እላለሁ፣
አንቺን ባፈቀርኩኝ
    ጌታን መስያለሁ።
የኔን ልንገርሽ
   ጨጓራዬ በስሏል፣
በቀናሁኝ ቁጥር
    ጥላሸት ይመስላል።
የኔን ልንገርሽ
   ቃላት አብዝቻለሁ፣
ፍቅር ፍቅር እያልኩ
    መድረስ ጀምሬአለሁ።
የኔን ልንገርሽ
   ሰው ያለ አይመስለኝም፣
ሴትም ሰውም ውብም አንቺ
ሆነሽ ሌላ አይታየኝም።
የኔን ልንገርሽ
    አይቀረኝ ሙሉቀን፣
    አይቀረኝ ብዙአየሁ፣
    አይቀረኝ ታምራት፣
    አይቀረኝ ቴዲ አፍሮ፣
ማዳመጥ ነው ልምዴ
            እየሰጠው ጆሮ👂
  አያቅም እኔ ጋር ዘፈን ውሎ አድሮ ።
   የአንቺን ግን ንገሪኝ ?
         እንደኔ ሆነሻል፣
     ወይስ እኔ እንደፃፍኩልሽ
         ለአንዱ ሰው ፅፈሻል።


ምንጭ፡- የሷን መልስ በመጠበቅ ላይ ሆኜ የተፃፈ
ማጀቢያ ሙዚቃ ፡- ልዑል ሲሳይ ( የኔ አመል )
ገጣሚ፡- ፓፒኤል

@getem
@getem
@getem
52👍6🔥3🤩2
ልቡ ለከነፈ ፥ ለናፈቀ ወዳጅ
ምን ያደረጋል ታክሲ ?
ምን ያደረጋል ባጃጅ ?
ወራጅ !
የመኪናው ጎማ ፥ ሺ ጊዜ ቢፈጥን
መውደዴን ላያክል
ጉጉቴን ላይመጥን !
ወራጅ !
ወራጅ !
ናፍቆቷ እንዳልደክም ፥ ይሆነኛል ነዳጅ ።

ጫማዬን አስሬ ፥ ወደ ቤቷ ላዝግም
አጋዥ አልፈልግም ።

መኪናም ይቅርብኝ ፥ ፈረስም አልጋልብ
እግር ይቀርባል ላሳብ
እግር ይቀርባል ለልብ ።

By Hab HD

@getem
@getem
@paappii
53👍6🔥4