ግጥም ብቻ 📘
67.4K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
Audio
#ትዝታወልዴ
#YonnyAthan
#መሳይ
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

@Tizita21
@getem
10👍9🔥2
#ያመንኩሽን ያክል
አቤት ያንቺ ነገር የሰራሽው ስራ
ስትቀርቢኝ ለፍቅር መች መስሎኝ ለሴራ፤
ወድሀለው ያልሽኝ በማሪያም ስም ምለሽ በውሸት መማሉ ዓፅያት መሆኑ አይጠፋሽ
ግን አላዘንኩብሽም ይልቁን ደስ አለኝ
በጥልቀት ሳለምድሽ ክደትሽ አስተማረኝ
ምን ይሁጠኝ ነበረ አንቺን ያጣውኝ እለት
ባይሆን በጅምሩ የኔና አንቺ መለያየት
አጣው የለም ነበረ ይሄን ማንነቴን
በፍቅር የሚያምነውን ያን ሰብሃዊነቴን
አየሽ ለዚህ ነበር ብዙ ያልተጎዳውት እንዳልሽው ይሁን ብዬ ሁሉን ተቀበልኩት
ብዙም ባንቆይ እንዃን የ 2 ወር ጓዴ ነሽ
ክፉሽን ስለማልሻ አንድ ምክር ልምከርሽ ሳይገባሽ ቀርቶ ይሆናል ልጅነቱ ይዞሽ
አልያም ጥሬ ሆነሽ ሳትበስዪ የቀላሽ
ይህ ማስመሰሉ ያልሆኑትን ሆኖ
ዛሬ የለመድሽው ነግ ባንቺ ላይ ገኖ
ባዶ እዳያስቀርሽ የያሽውን ሁሉ በትኖ
ከብረትም ዝገት ከሰውም ስህተት ስል
የታል የታመንሽው ያመንኩሽን ያክል!?
#መሳይ-ግርማ

@getem
@getem
@getem
👍428👎4😢1
/እንዲሆን ጥረት አርግ/
ማድረግን እየቻል ቢሆንን ከመረጥክ
ነውን ከነ ንቀ በይሆናል ከከጀልክካሳብ ከሰመመን ውጭ እስኪ ምን አተረፍክ፤
ያንተህ ማብሰላሰል ያንተህ ባሳብ መጓዝ
ለኑሮክ እሾ እንጂ መች ይሆናል ጉዝጓዝ፤
በሰውነት አለም መመኘት ባይከፋም ምንምበማይሰራው በእርሱሰውአይነፋም
ይልቁን ምኞትክ በስራ ሲታጠን
ይስብስ የለም ወይ የሚወጣው ጠረን፤ ሁሉም በቁመናው ባካል ሲሆን ይበጃል
ምንም ጥቅም የለው በምናብ መጃጃል

#መሳይ ግርማ

@getem
@getem
@geten
👍29😱2
/እስቲ ልቀኝልሽ/
የሰራ አካላትሽ ከሌላው ሰው ቢለይ
ልቀኝ በውበትሽ ልጠበብ ባንቺ ላይ፤
የቁንጅና ጥጓ የውብ ዳር ውቢት
አፌስ መቼ ገዶት ላንቺ መቀኘት፤
ደምግባተ ግሩም ፈገግታሽ ማራኪ
ከራስ ደስታም አልፎ የሰው ልብን አርኪ፤
ያይኖችሽ ሽፋሽፍት የቅንድብሽ ሙላት
ከሚኳሉት በላይ ሰቶሻል ላንቺ ውበት፤
ከንፈርሽ ቀይ ነው መቼ ቀለም ያውቃል
ጉንጭሽ ዲንፕል አለው ስስቂ ያሳብቃ፤
አፍንጫ እረጅም ከነ አንገትሽ ጭምር
በቃ ሙሉ ሆነሽ ተፈጥረሻል ከምር፤
በላይ ተጨምሮ ያንቺ አመለካከት
ለውበትሽ ግርማ ሆኖለታል ድምቀት፤
ውበትሽን ስገልፅ ካንገትሽ አላልፍም
ሌላው እንዳይመኝሽ ሙሉውን አልፅፍም
ደሞም ቁንጅናሽን ለመግለፅ ቃል በቃል
ላላዩን ነው እንጂ ሙሉውን ማንያውቃል፤
በገሀዱ ሳይሆን በምናብ ምስልሽ
ማንነትሽን ሳላውቅ እንዲህ ምገጥምልሽ
ጥያቄ ሆኖብኛል ቆይ ግን አንቺ ማነሽ!?

#መሳይ ግርማ

@getem
@getem
@getem
24👍19😁14
/ቸልታው ምንድነው/
ስሚኝ እማ ቸልታ ባንቺ አያምርም
ነገሮችን መተው ካንቺ ጋር አይሄድም፤
ይልቁን የሚያምረው አንቺን የሚገልፀው
ጠያቂው ባእሪሽን እርሱን ነው ምወደው፤
ምክንያቱ ምን ይሆን ትኩረትሽንያሳጣኝ
ምን አጉድዬብሽ ነው ካሳብሽ ያወጣኝ፤
እኔ እስከማውቀው እስከገባኝ እውነት
መች ከጀልኩኝና ከልብሽ ለመውጣት፤
ይልቅ የምኖረው የማስበው ሁሌም
ከኔ ይልቅ ይበልጥ ላንቺ ደስታ አይደለም፤
እየሆነ ባለው እርግጡን ባላውቅም
ውስጤ ሚነግረኝን መተው አልፈልግም፤
ሳልወስን አስቀድሜ አንድ ነገር ለበልሽ
ልክ እንደ በፊቱ እንደማውቅሽ ካልሆንሽ፤
ኃላ እረፍዶብሽ ከህጅሽ ከምታጪኝ
አጠገብሽ ሳለው ባክሽ ትኩረት ስጪኝ

#መሳይ-ግርማ

@getem
@getme
@getem
👍5017👎8😁3😱1
/አረ እኔ አምንሻለው/
የትላንት ታሪኬን ሁሉንም ባወራሽ
እውነት እንዳያድር የሆንኩትን ባወጋሽ
ይህ ነገር አንቺን ለምን አሳሰበሽ፤
በያቺኛዋ ጥፋት እጅሽ መች አለበት
አምንሻለው ስልሽ ብታምኚ ምናለበት፤
እሱ አያምነኝም ብለሽ አጠርጥሪኝ
ከበፊቱ የላቀ ባንቺ እምነት አለኝ፤
በሌላዋ ጥፋት እኔ አልወቅስሽም
አንቺንም እንደሷ ከቶ አልይሽም፤
በቃ አትጨነቂ አሳብ እንዳይገባሽ
ከራሴ አብልጬ አንቺን ነው የማምንሽ፤
ይህን በማድረጌ ከሰው አፍ ቢከተኝ
ከትላን ማይማር ምንአይነቱ ነው ሞኝ፤
ቢሉኝ ቢናገሩኝ እኔ መች ሰማለው
ለማን ይመስላቸዋል መታመን ለራስ ነው፤
አንቺንም ባመንኩሽ እነሱ ካሉኝ ሞኝ
እስቲ ንገሪያቸው አንቺም እንደሷ ትሆኝ?

#መሳይ ግርማ
@getem
@getem
@getem
👍288😱2🔥1🎉1
/የኔ ወይ የማነሽ?/
የኔ ባላትና ባረጋት የግሌ
የራሴ የምላት በሆነች አካሌ፤
ብትሆነኝ ከጎኔ አጋሬ ሆናልኝ
ቢደርስ ልመናዬ ፀሎቴ ሰምሮልኝ፤
ነበረ ምኞቴ አብረን ብንዛመድ
ጠብቀን ብንታሰር በማይላላ ገመድ፤
መሻቴን ተረድቶ ጭንቀቴን ቢሰማኝ
ከሁሉ አስቀድሞ ለኔ አንቺን ቢሰጠኝ፤ ሌላ ምን እሻለው ምን ያስፈልገኛል
በብቻ ያጡት ነገር ባብሮነት ይገኛል፤
ግን እደዛ ባይሆን አንቺ የኔ ካልሆንሽ
ጊዜው እረፍዶብኝ ለኔ ያላት ሳትሸሽ፤
እውነቱን አውቄው ለኔም እንዲቀለኝ ፋታአልሰጥም ያለኝ ልቤ እንዲቆርጥልኝ፤
እባክሽ ቆንጂቷ ተንፍሺ እስቲ ልስማሽ
ሁለት ነው ምርጫው የኔ ወይ የማነሽ?!
#መሳይ-ግርማ
@getem
@getem
@getem
👍3721😢1
/እንዴት ሰው ለጉንፋን/
ለቁርጥማት ቢሉ
ለእራስ ማስታገሻ
ላደረብኝ እመም
ፍቱን መፈወሻ፤
ከቤቱ ሳላጣ
ፌጦ ደማገሴ
ከማድ ቤቱ ሳይርቅ
ሳትራቆት ኪሴ፤
ዝንጅብልን ጨምሮ
ነጭ ሽንኩርት ሳይጠፋ
ከራስ ላያልፍ ጉንፋን
ሆስፒታል ወረፋ፤
ማዳኛው እያለኝ
እረፍ የሚሰጠኝ
ለምንስ ካፍንጫዬ
ፈሳሽ ነገር ይውጣኝ፤
ይሄው ነው ድክመቱ
በራስ ለራስ ቅጣት
ማርከሻውን ይዞ
በእመም መቀጣት
😇😇😇
#መሳይ-ግርማ
@getem
@getem
@getem
👍7416🤩7🔥3😁3
/ከሄድሽም ምን ሆንኩኝ/
         ማህበል ማይበግረው                                        ወጀብ የማይረታው
      ምችም የማይመታው
ወረት የማይገታው፤
       እኔስ መስሎኝ ነበር
ፍቅርሽ ወረት ማያውቅ
         ሚቆይ ሚመስል እንጂ
መውደድሽ የማያልቅ፤
          ይህ ሁሉ ልፋት ነው
እንደው ድከም ሲለኝ፤
           ሳጠፋ መልካም ሴት
አንድ አንቺን ያስመኘኝ
            ግን ምን ይደረግ
አንዴ የሆነው ሆኗል
          ልቤስ እንደ ፊቱ
በጭፍን ሰው ያምናል?፤
          እድሜ ላንቺ ልበል
ቀጥተሽ ላስተማርሽኝ
          ላያዳግም ስህተት
መንገድ ላሳየሽኝ፤
           እኔስ ብልጥ አይደለው
ከስህተቴ ተማርኩኝ
          አሁን ላይ ደህና ነኝ
ከሄድሽም ምን ሆንኩኝ?😄
                      #መሳይ-ግርማ
@getem
@getem
@getem
👍5718🔥15😢3
/እስቲ አንቺ አውሺኝ/
ስንቱን ለንግግር ለሳቅ ለጨዋታ
ደግሞም ለመግባባት የቃላት ሁካታ፤
እንዳልደረደርኩኝ ከወሬ ማዕድ ላይ
እንዳደራረብኩኝ ነገረ በላይ በላይ፤
ልቤ የወደደሽን ዛሬ አንቺን ባገኝሽ
ልጥር ብከጅልም በቃል ላሳምንሽ፤
ከየት ይምጣ ቃሉ እንዲያ የዘረገፍኩት
ዛሬ ጠፋኝ ቅኔው ያኔ የዘረፍኩት፤
በምን ብናገር ይሆን አንቺን ምማርከው
ከምንስ ብጀምር እዴትስ ብተርከው፤
ላወራሽ እልና ምለው ይጠፋኛል
ስደርስ ካንቺ አጠገብ መናገር ያመኛል፤
ደሞ ሚያሳስበኛል!
በአፌ ተናግሬ ባይሽማማሽ ያልኩት ቃል
መዉደዴስ ባጭሩ ሳልጀምር ያበቃል፤
እላለው ከራሴ ጋር እያብሰለሰልኩኝ
ቆሞ ለታዘበኝ እብድ እየመሰልኩኝ፤
እና አንቺየዋ!
ከሆነ እስኪመጣ ቃል ከኔ ምትሸሺን
የሚያስማማንን ቃል እስቲ አንቺ አውሺኝ
#መሳይ ግርማ

@getem
@getem
@getem
👍4410😁4
/ ለምን ጠላሻለሁ/
መቼ ተለወጥኩኝ እንደዛው ነኝ እኔ
ተለዉጧል እርሱ አይደለም እንደ ያኔ፤
እያልሽ የሌለኝን ማንነት አትስጪኝ
ከመሬት አንስተሽ ከሰው አፍ አታውጪኝ፤
ደሞስ መች ሊጨክን ልቤስ ሊደነድን
በሕይወት ሳለሁኝ ከቶ ሳልሆን በድን፤
የኔ የዋነቴን የልቤንም አይተሽ
ዛሬ ምን ሲል ታየሽ ያኔ የሄድሽው ትተሽ፤
እርግጥ ሰው ባጠፋው ፀፀቱ ባይቀርም
ወደሽኝ ቢሆን ኖሮ በኔና አንቺ አይከርም፤
ታዲያ መች እንደዛ ሆኖ ያንቺ ቀረቤታ
ፌዝ አዘል ነበረ የጥርስሽ ፈገግታ፤
ያኔ ማፍቀርን ጠግቤው መፈቀር ቢርበኝ
ያንቺ ልብ በፍቅር መች አምኖ ቀረበኝ፤
አሁን ላይ ጥያቄሽ ለይቅር ከሆነ
ጥፋት እንዳጠፋሽ ልብሽ ይህን ካመነ፤
በሰው ቂም አሊዝም ይቅር ብዬሻለሁ
ዳግም ባልወድሽም ለምን ጠላሻለሁ;
#መሳይ ግርማ

@getem
@getem
@getem
👍5223🔥1😁1
/ይቀጥላል ፍቅር/
ሳላገኝሽ በፊት ሳትሆኚ በቅርቤ
በገሃድም ሳይሆን ሳለሽ በአሳቤ፤
የዛኔ የሆንኩት አንቺን ላገኝ ብዬ
ሙሾ ያስወረደኝ ያስባለኝ እዬዬ፤
ያ ፍቅርሽ ብዙ ጉድ ያሳየኝ
ጊዜው ደርሶ ዛሬ ካንቺ ቢያቆራኘኝ፤
አጣጥሜ በቅጡ ሳልቀምሰው
ልኖር ካንቺ ቤቴን ሳልቀልሰው፤
በጅምሩ በፍቅራችን ንጋት
የመውደድን ፅዋ አብረን ሳንጋት፤
" ዛሬላይ"
እስክረሳው ያንቺ ወደኔ መምጣት
እስክል ድረስ ለምን አፈቀርኳት፤
አርጎኝ የነበረው ላንቺ እንድረታ
ሰከን ያላረገኝ እንዳላስብ ላፍታ፤
የከለለኝ እሱ እንዳላይ ጋርዶብኝ
ፍቅርሽ አይደለም ሆይ ያረገኝ ባንቺሞኝ፤
ግን የሚገርመው የኔ ፅኑ አቋም
ይቀጥላል ፍቅር እንዴት ባንቺ ሊቆም:
#መሳይ ግርማ

@getem
@getem
@getem
👍2414🔥1
/በእንቅልፌ አትምጪ/
በሰመመን አሳብ በረዘመው ለሊት
በማይመች አልጋ ቅዠት በሞላበት፤
ትንቅንቁን ይዤው ስገላበጥ ካልጋው
አልገፋ ያለኝን ለሊተቱን ላነጋው፤
ቆሞ የቀረ ይመስል ቀርዝዞ ሰዓቱ
ላነጋ ይቅርና መሸብኝ ለሊቱ፤
እረፍት የነሳኝን ያጣውለት መላ
ታወቀኝ ምክንያቱ ከነጋ በኃላ፤
አልጋው አልነበረም ምቾቴን ያሳጣነኝ
ለሊቱስ መች ሆኖ ከእንቅልፌ ያወጣኝ፤
ለካስ አንቺ ነበረሽ ቀን በአሳቤ ያኖርኩሽ
ይኸው ለሊቱን በአልጋ በቅዠት ተረኩሸ፤
እናየኔዋ አሳብ አዘኔታው ኖሮሽብታዝኚልኝ
ላስቸግርሽ እስቲ አንድ ውለታ ዋዪልኝ፤
በብርሃኑ አለም ከቀን አሳብ ውጪ
እባክሽ ልተኛበት በእንልፌ አትምጪ
#መሳይ ግርማ
@getem
@getem
@getem
👍5619🤩8👎4
(መልክ ልስራ ይቅር?)
ለጌጥ ልኑር ለውበት?
     ውስጥ አዳክሞ እላይ ኩራት
ልዋብ ለታይታ ለሰዎች እይታ?
      ላይቀርፍልኝ የእንባዬን ጠብታ
ሆዴ ባዶ ከአንጀቴ ተጋምዶ
            የኔ ይሉኝታ ጉድለቴን አይፈታ!
ልተወው ታዲያ የላይኛውን ውበት?
          ልመገባት የማምሻዬን እራት?
ይገምቱኝ በአሁኔ ገፅታ?
        ልተው  ጭንቄን ማሰብ ለይታ?
ይቦጭቁኝ በወሪያቸው?
          ያስለቅሱኝ በሳቃቸው?
      እሺ ምን ይሻላል??
  ሰው ለአይን ውበት
         ፆሙን እንዴት ያድራል??!
ግራ ገባኝ ከራሴው ስማከር
      እስኪ እናተስ መልክ ልስራ፥ ይቅር??
           ,,,,,,,,,,,,,,,,,,   #መሳይ ግርማ
@getem
@gexem
@getem
👍2315🔥3