ግጥም ብቻ 📘
67.4K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
እናንተ የምወድዳችኹ ፤
ስነ-ፅሁፍን የምትወድዱ ፤
የግጥም ነፍስ ያላችኹ ፤
ወንድሞቼ ፤ እህቶቼ ፤ ወዳጆቼ ፤ ታላላቆቼ እና በደስታዬ ደስ የሚላችኹ የዘመን ተጋሪዎቼ ኹሉ ፤ ይቺን የመጀመሪያ ስራዬን ቅድሚያ ገዝታችሁ ፤ ከጓዳ ወደ አደባባይ እንድትሸኙልኝ ስል ፤ የተወደደ የወዳጅነት ግብዣዬን እጋብዛችዃለሁ ።

ከወዲኹ ...
እጅግ እጅግ አመሰግናችዃለሁኝ
ኑሩልኝ !
ቴዎድሮስ ካሳ

____

የመፅሐፍ ቅድመ ሽያጭ ማስታወቂያ
Reserve yours now—it's on pre-order!

ርዕስ /Title - የዱር አበባ / Wild Flower
ዘርፍ / Genres - ስነ-ግጥም /Poetry
ዋጋ/ price - 300 ብር/ birr

የባንክ ቁጥር / Bank Accounts :
ቴዎድሮስ ካሳው አስረሴ
Tewodros Kassaw Asresse
ንግድ ባንክ / CBE - 1000360039847 ወይም 1000292025185 (ናትናኤል እሸቱ)
አዋሽ ባንክ /Awash Bank - 01320885596200
ሲቢኢ ብር / CBE Birr - 0972338625
ቴሌብር/ Tellebirr - 0972338625

[ ማሳሰብያ : ዃላ ለማስታወሻ ይረዳኝ ዘንድ Screenshot አንስታችሁ በውስጥ በሜሴንጀሬ አልያም በቴሌግራም አድራሻዬ @Poet_tedi መላኩን እንዳትረሱት ይሁን ።]
👍23🔥65
34👍12🔥3
# ይድረስ ለጨረቃ #
እንዴት ነሽ ጨረቃ
እንዴትነሽ በሰማይ
ምን ይታይሻል
ምን አለ ምድር ላይ… ?
በየጉራንጉሩ ሰው ነውሩን ደብቆ
የሚሰራው ስራ ህሌናውን ሰርቆ
ይታይሽ ከሆነ ሴራ ሲጎነጎን
የመከራ ጎጆ ሲሰራ ሲጠግን
የክፋት እንጀራ ሲቦካ ሲጋገር
የልቦና ቁስል ሲማገር ሲታጠር
ንገሪኝ በሞቴ ይገለጥ ጉዱ
የሰውልጅ ዶሴ የበደል ሰነዱ
እኔም ልናገር ልመስክር ለፍርዱ ።

@topazionnn
@getem
@getem
41👍29🔥8😁1
እኔ ያንቺ አለም
ደብዘዝ የምል ደማቅ ቀለም
የምተጋ ነገን ማልም
ለኔም ላንቺም የምሆን ህልም
ተዛምደናል ኪዳን መተን
መሃላችን ለቃል ሰተን
ነበርሽ የኔ ብርቱ ወገን
ጥንካሬሽ አንድ ያረገን

ያሳዝናል ጊዜሽ እቱ
ተዛምደሻል ከማዕቱ
የሄድሽበት ከኔ ይርቃል
ረስተሻል መሃላ ቃል
የኔ ገላ ያልታደለ
አንቺን ልኮ ባዶ አደረ
ደህና አድሯል ወይ ያንቺ ገላ
ባሉን ትቶ የተዳራ
ሽሎሽ ነው ወይ ከኔ እሱን
ቃል ማሃላን ማፋረሱን
ያሳዝናል ጊዜሽ እቱ
ተዛምደሻል ከማዕቱ
አንድን ይዞ ሳይራቡ
ምን ይሉታል መደረቡ

ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
👍5311😢3🔥2😱2🎉1
እልፍ ስትል እልፍ አበሳ ሄድ ስትል ጉድ ጭካኔ በመንገድህ ለሚነጉደው
ምን ለማትረፍ ምን ለማግኘት እርምጃህን 'ምትቀጥለው
ወዴት ይሆን ህይወቴ ሆይ የምትሄደው
የብቻነት የስቃይ ቤት ምን ይሆን ‘ምትፈልገው
እዚህ የእንባ ጎርፍ ውስጥ አለምን ከሰራት
ብትሰምጥ ብትሞት እርሷን እንደው ይቸግራት?
ደስታ ፍለጋ ‘ምትባዝን ህይወቴ ሆይ
ከንቱነት ነው አንተን ‘ሚቆይ
አንተ አበባው በሜዳህ ላይ የምትስቀው
አንቺም ወፏ ከዛፍሽ ስር ተደብቀሽ 'ምታለቅሺው
ፍፃሜያቹ ለካ አንድ ነው
ለማይዘገን ጥቂት ደስታ ዞሮ እንደ ጉም ለሚበነው
በስለቱ በጫፉ ላይ አየዘለልክ 'ምትጨፍረው
.....አንተ እኮ ነህ የምትደንቀው


Translated from "hymen of death " the movie

By yodan

@getem
@getem
@getem
👍339🔥1😢1
ተራራ የሆነብንን የዳህንበትን አቀበት
እየናጠጡ እየፈረጠጡ ተንደረደሩበት

መስከኛ  ያለውን    ለም መሬት
ፎሮሹ   ፈጩበት
ወቁ ሰለቁበት


አደራ  አማን ብለን ሳለ
አልተዘገረ
አልተመተረ
ከተባለ
አኑር ጠብቀን   ብለን ሳለ
ከሆነ የሞት ሹም
አይሳሉ ስለት   ለሞታችን የተሳለ

ተመርቆለትም ከኪሎው ካለየ
ወደ ተመዛኙ ካላዘነበለ 

አይጠረጥርም ወይ
ምንም ያልጠየቀ   ?

ክሳት ገፅ የለውም 
አጥንት ካልገለጠ ?


ነገር  ነገሩን ቢለይም
ምኑን ከምኑ
ውል ያልያዘ ሰው
ቢመሽበትም  አይነጋለትም

ዘንድሮም ዘንድሮ ተባለ
ሹም ሽረቱ ፍርዱም ተሻረ
ውሸቱ ሲፍም  እውነት ከሰመ

ጊዜ ለሁሉ መልስ ቢያኖርም    
ምኑን ከምኑ
ውል የተሳተው
ቢመሽበትም   አይነጋለትም

By mik

@getem
@getem
@paappii
👍328🔥1
ስምን መሄድ ጥሎ
ከታሪክ ተካፍሎ
አሸብርቆ መኖር
በወርቅ ተጠቅልሎ ፤
ዘርን በመተካት …
ወዳጅን በማፍራት
የምድር መናዋን
ብዙውን በመብላት
ሸጋውን በመልበስ
ፋሽን በመጫማት
ማርሴዲስ መኺና
ሸምቶ በመንዳት
ነው እያልን ስንኖር
መለኪያ ፣ ሚዛኑ
ሁሌ በየቀኑ…
ከልብ መሳቅ ኖሯል
የስኬት ተመኑ !

(ሚካኤል አ)

@getem
@getem
@getem
27👍20🔥6🤩2
ጭጋጉ ሲያከትም በክረምቱ ማብቂያ፤
ፀሐይ ስትፈነጥቅ በመሬት መድረቂያ፤
የፀደይ አበባ ማበብ ስትጀምር ፤
አደይዋ ለሰዎች ተስፋን ስታበስር፤
በወርሐ ጥቅምት በመጀመሪያው ቀን፤
ዛሬን ነዉ የወጣሁ ከእናቴ ማኅፀን።

ያቺ እናቴ በጭንቋ ቀን ምጧ ደርሶ፤
እያነባች ላብ አጥምቋት ፊቷ ርሶ፤
ማርያም ማርያም እያለች፤
ምጧ ቀለለላት ስሟን እየጠራች።

በልደቷ ቀን መታሰቢያ.........
ሰምታ ጸሎት ስዕለቷን፤
ማርያም ማረቻት እናቴን።
በዚያች ሴኮንድ በዚያች ቅፅበት........
ከልቤ ታትሞ ማርያም የሚለው ስም፤
ለዛሬ ደረስኩኝ በፍቅሯ ስሸለም።

የእቅፏን መዓዛ እየመገበችኝ፤
የትህትናን ዋጋ እያስተማረችኝ፤
የልጇን ጌትነት በልቤ ሰሌዳ፤
የእርሷን ትሁትነት በፍቅር አዋድዳ፤
የንስሐ እድሜን ፈጥና አሰጠችኝ፤
አዲስ ቀንን እንዳይ ድንግል ባረከችኝ።
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎊🎊🎊🎊
ዔደን_ታደሰ @ediwub
ጥቅምት ፩/፳፻፲፯
መልካም ልደት ለእኔ🎂🎂🎊🎊🎊
@getem
@getem
@getem
68🎉27👍24🤩4
Forwarded from TIZITA21
💕ትዝታ ወልዴ(@Tizita21)

@getem
@getem
22👍8🔥7
ቀጥቅጬ የገደልኩት~እባብ የትናንቱ
ሳይተነፍስብኝ~ሳይነካኝ መሞቱ
ተረሳው መሰለኝ...
ዛሬ እንደነደፈኝ~በዛ መጠዝጠዙ
በቃ እንደፈራሁት~ያንተ ነበር መርዙ

ዘማርቆስ

@getem
@getem
@getem
21👍15😁3
...ትዝታ

ትዝታ ገዳዩ ናፍቆትን ያብሳል
በጥላቻ መሀል ፍቅርን ይሰብካል
እንባን አሳብሶ በምናብ ይወስዳል
ትዝታ ከባዱ ቫይረስ ነው ይገላል

By
@Hanipia

@getem
@getem
@Hanipiagetem
👍373👎2🔥1😱1😢1🤩1
Forwarded from TIZITA21
💕ትዝታ ወልዴ(@Tizita21)

@getem
@getem
29👍5🔥5👎1
ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
37👍14🔥4
44👍10🔥4
ሰው ፈለገች የሚያፅናናት
ችግር ውስጧን ሚረዳላት
ሰው ፈለገች የሚያፅናናት
የአይኗን እንባ ሚያብስላት

ለጠየኳት ጥያቄዎች
ምንም ነበር መልሰ ቃሏ
ብዙ እንደሆነች ግን
ይናገራል ፊት አካሏ

ብቻ...ዝም ብላለች

ታስታውቃለች ሆድ ብሷታል
ታስታውቃለች እንደከፋት
ቆንጆ መልኳን ተመልክቶ
ማን ይሆን ሰው ደርሶ የገፋት
ደረቅ ብሏል ውብ ከንፈሯ
አላገኘም አንዳች እህል
ቀዝቀዝ ብሏል የእጇ መዳፍ
ምን ሁናለች እቺ ጉብል

ቀና ብላ እያየችኝ
ዘረገፈች የአይኗን እንባ
ስቅስቅ ብላ አለቀሰች
ነጠላ እጇን ተከናንባ

እንዲህ ነው እያለች መናገር ባትችልም የውስጧን አውጥታ
ብዙ አውርታኛለች ከኔ ጋራ ሳለች ቃሏን በዝምታ
ይገርማል አንዳንዴ
ቃላት ሳይደረደር ምስክር ሳይጠራ ሀቀኛ ሳይለካ
ብዙ ሳንናገር በዝምታ ብቻ ቃል ይወጣል ለካ!


ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
👍9050🔥9🎉3😁1😢1🤩1
ጥያቄ

ሊሰጠኝ ከሚችል ከብዙ ስጦታው ሞልቶ የተረፈኝ
ከሰው ከሀብት ከፍቅር ሁሉ የተሰጠኝ
ባልጎደለ ኑሮ እኝ እኝ የሚያስብለኝ
ምን ይሆን የጎደለኝ
ምን ይሆን የመረረኝ

By Yodan

@getem
@getem
@paappii
23👍12😢6🔥4
ረክሶ ነው እንጂ
እግዜር ሚባል አልማዝ
ይሻማበት ነበር
ፍጡር እንደቁስ ጓዝ

ረክሳ ነው እንጂ
ማሪያም ሚሏት ሀምሎ
ቤት አያጣም ነበር
ልብ 'ሚባል ኪሎ

ቀንሶ ነው እንጂ
ሰው ሚባል ሳጥናኤል
ወንበሩን ባልሸጠው
ለእነ ሊቅ ሚካኤል

ቅዱስ ሚካኤልስ
ይጠብቃል ሰውን
ቅዱስ ገብርኤልስ
ያወጣል እሳትን
እግዜር ግን ዝም ነው
ያቺን ቀን ያላትን

ሀገር ሚባል ዕዳ
ቃል ሚያክል ሚካኤል
ሸጦታል አሉ ሰውን ለሳጥናኤል

እግዜሩ ቢረክስ ገነት ይወደዳል
ሳጥናኤል ቢረክስ ሲኦል ሰውን ያጣል
ሰው ሰውን ካጣ ሰው ከየት ይገባል ?

ጨለማው ላይ ሆነሽ
ስሜንም አትጥሪ
ጊዜ ሚጠብቅ ሰው
አይባልም ፈሪ
እባክሽን ዓለም
ባይሆን አምላክ ፍሪ


@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት

@getem
@getem
@paappii
24👍19👎16🔥4😱1
ልሳነ አፍቅሮት

ለቃል
   ለትዕዛዙ
      ብርሀንም
      ጨለማም
       ተገዝቷል ።
      
    ለበጋ
          ወቅቱ በጋ
     ሆኗል።
ለማበብ
      አበባ ፈክቶ
               ደምቆ
              አሸብርቋል ...።
  .......
.....
ኩሉ አላፊ
       ወፈላሲ
    ሆኖ ሳለ



ከማስበው
     ስሩ
            ስሩ
ከውስጥ
          ከውስጥ
ከልቤ ላይ
እሷን መጥራት
መጥቀስ አለ
ቃል የሆነ
አልፋ ኦሜጋ
ልሁን ያለ
     
                  ምክያስ አለምሰገድ(mik)

@getem
@getem
@paappii
👍248🔥6🎉4🤩2
እስቲ ልመርቅሽ
        እስቲ ደሞ ልጣሽ
የልብሽን አይቶ እግዜር ከኔ ያውጣሽ
.


ዮኒ
      ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
28👍16🤩6👎3
የድሮው አምላክ
'
'
አዲሱ አምላክ ገና አልመጣም
የቀድሞ አምላክ አገናኜን ፣
ቢያንስ ቢያንስ ባያድሰን ፥
ለትዝታ እስኪፈጥረን ፥
አዲሱ አምላክ እስኪ ተወን ፣
'
'
@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት

@getem
@getem
@paappii
👍188👎3🤩3🎉2😁1