ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ፈጣሪ አምላኬ ~ ይቅር በለኝ ዛሬ
         ህግህን ሳፈርሰው

አትፍረድ ብትልም ~ እኔ ግን አልቻልኩም
        ፈርዳለው በዚህ ሰው።

የክፋትን ጥጉን ~ የመቆሸሽ ጥጉን
        ገደቦች ላለፈ

ያንዲት ምስኪን ህፃን ~ ክብሯን በግፍ ገፎ
         ነፍሷን ለቀጠፈ

የእጁን እንዲያገኝ ~ ስቃይ እና ሞቱን
          ለሱ መመኘቴ

የጨቅላዋን ህመም ~ ማሰብ ቢያቅተኝ ነው
       ባይችል ነው አንጀቴ



የቆሰለ ውስጧን ~ የእናቲቱን እምባ
ሚያብሰው ሲጠፋ

ፍትህ እየተዛባ ~ ተበዳይ ሲበደል
ውስጣችን ቢከፋ

አቤቱ ፈጣሪ ~ አነባን ወዳንተ
አነባን ወደላይ

ፍርድህን አሳየን ~ ክፉዎች ቀጥተህ
በምድርና በሰማይ



#ፍትህ_ያለእድሜዋ_በግፍ_ለተነጠቀች_ነፍስ
#ፍትህ_ለሔቨን

@BegitimEnawga


@getem
@getem
@getem
😢136👍4235