ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#እግዜሩ ነው የሚገርመኝ
ምኞትን ያህል ነገር ተፈጥሮ ስትቸረኝ
በእጁ አበጃጅቶ የኳላትን እንስት ደጄ እያሳየኝ
አታመንዝር አለኝ!
.
እግዜሩ ነው የሚገርመኝ
በእሾህ በአሜኬላ ዓለሚቷን አጥሮ
አዳም ይብላ አለ በላቦቱ ግሮ።
እሺ የት እንስራ?
በዚም በዛም ያለው አለበት ደንቃራ
በቃ ልስረቅ ልንጠቅ
ቀን መሽቶ ቢያልፍልኝ...
እንዲህ አልል ነገር የርሱ ህግ አለብኝ።
.
እውነት!
እውነት!
እውነት!
እግዜሀር  ነህ የምትገርመኝ
ድመት አርገህ ፈጥረህ ወተት አትንጠቀኝ
ነብር አርገህ ፈጥረህ ፍየል አትስረቀኝ
ስትለኝ...
እንደዚህ አትበለኝ...
ብዬም አልበሳጭ አልሳደብ ነገር
ፈጣሪህን አክብር ይላል የህግህ በር ።

(ሚካኤል.አ)

@getem
@getem
@getem
👍4628👎16😁5🔥4
#እግዜሩ ነህ የምትገርመኝ
ምኞትን ያህል ነገር ፣ ተፈጥሮ ስትቸረኝ
በእጅህ አበጃጅተህ የኳልካትን እንስት ደጄ እያሳየኝ
አታመንዝር አልከኝ!
.
እግዜሩ ነህ የምትገርመኝ
ምድሪቷ ታጥራብን ፣ በእሾህ አሜኬላ
ወዙን ሲያዘንብ ነው ፣ አዳም የሚበላ።
እህስ እንዴት ይሁን?
ተመልከት መንገዱን…
በዚ’ም በዛ’ም ያለው ፣ አለበት ደንቃራ
በቃ ልስረቅ ልንጠቅ
ቀን መሽቶ ቢያልፍልኝ...
እንዲህ አልል ነገር ፣ እሳት ዲን አለብኝ።
.
እውነት!
እውነት!
እውነት!
እግዜሀር ነህ የምትገርመኝ
ድመት አርገህ ፈጥረህ “ወተት አትንጠቀኝ”
ነብር አርገህ ፈጥረህ “ፍየል አትስረቀኝ”
እያልከኝ ፣
እንደዚህ አትበለኝ...
ብዬም አልበሳጭ ፣ አላሸሙር ነገር
ፈጣሪህን አክብር ይላል የሕግህ በር ።

(ሚካኤል.አ)

@getem
@getem
@getem
35👍25😁10😱3👎2