ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ውሉድ ወወላድ*


የወለደች ኹሉ . . .
እናት አትባልም ! ግብሯ ካልተለየ ፤
የተወለደ ልጅ . . .
አይባልም ጧሪ ! ምግባሩ ካለየ ።

ዘር ስላካፈለ . . .
የአባት መሆን ክብር በከንቱ አይሰጥም !
ከልጅ ስም ቀጥሎ ስሙ አይቀመጥም !

እፍኝትን እይዋት . . .
እናት ትሞታለች ፣ ትውልድ ለማስቀጠል
አባትም ይሠዋል ፣ በፍትወት መቃጠል ።
አንበሳም ደቦሉን . . .
በጊዜው ካልቀጣ ንግስናው ይቀማል ፤
የልጅነት ሥሥት ፣
የአባትነት ድርሻ ለክብር ይወድማል ።

አዎ !
እናት ክብሯን ይዛ ፣
ልጅ ግብሩን ተላብሶ ፣
አባት በስም ነግሦ ፣
ካልተነፃፀረ ፤
የመዳን ምሳሌው ትንቢቱ ተሻረ ።

#የሞት ጥቁር ወተት
#ተስፋሁን ከበደ
@getem
@getem
@beckyalexander
👍2
የፈጣሪ_ልሳን
እጆቼን ዘርግቼ........
ልጸልይ ልማልድ ከደጅኽ ተገኘኹ
አንጋጥጬ ሽቅብ በሐሳቤ ዋኘኹ
ተንበርክኬ ለምሕላ በግንባሬ ተደፍቼ
ቀና ማለት ተዘነጋኝ የቃል ጸሎት ረስቼ

ያ'ንደበትኸ ልሳን ከየት ተሠወረ?
ቃል ከምላሴ ላይ እንደምን ታወረ?
ዝም....
ዝም ዝም....... !
እንደው ዝም! ዝምታዬ ቀረ
ሰምተኸኛል አንተ
በዝምታ ልሳን ጸሎቴ ሰመረ።

ገጣሚ #ተስፋሁን_ከበደ

@getem
@getem
@paappii
63👍11🔥3🤩1