ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
አምና እና አቻምና ተብሎ አመት አልፎ
ዛሬ ያልነው ዕለት ከታሪክ ተፅፎ
ለ አዲስ አመት በቃን !
ለአዲስ ፀደይ በቃን ! እንደ ቸርነቱ
ሰላም አይለየን ሁሌ በእየ አመቱ
.
አደይ ስትፈነድቅ ማልዳ ስትፈካ
ወቅቶች ሲቀየሩ ቀን በቀን ሲተካ
ያማሩ እንስቶች ደጃፍን ሲያደምቁ
አዛውንት እናቶች ሁሉን ሲመርቁ
ዕንቅጫ ቄጤማው !
እንጉርጉሮ ዜማው! ሲዳረስ ለሁሉ
ለአመቱ ያድርሰን ለጋ ልቦች ሲሉ
ማየቱ ሲያኮራ ማየቱ ሲያስደስት
ዘማሪው በተራው ብሎ ሲዞር ቅድስት
ምንኛ መታደል የዚህ አካል መሆን
ድሮም የነበረ አይደለም የሰሞን
.
እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ ደርሰናል ይመስገን
በፍቅር አስውቦ ሁልጊዜም አንድ ያርገን
በአልቡታ ወሬ ማንታለልበት
ለፍቅር ለሰላም የምንዘምርበት
ቸር ቸሩን ሚያሰማ እልልታን ሚደግስ
የሁሉን አይምሮ ቀልብን የሚመልስ
ብሩክ አመት ያርገው ፀጋው አይለየን
እንዲሁ እንዳለነው በሰላም ያቆየን


እንኳን ለ 2016 የዘመን መለወጫ በሰላም እና በጤና አደረሳቹ🙏 በዓሉን ከምንም ነገር በላይ የ #ሰላም#መተሳሰብ#አንድነት ያድርግልን። እንዲሁ እንዳለነው ለዓመቱ በሰላም እና በጤና ያድርሰን🙏

              🌼🌼🌼🌼 መልካም በዓል🌼🌼🌼🌼

በ ኪሩቤል አሰፋ
@Ebuh_bhr

@getem
@getem
@paappii
👍291🎉1