#ዓይኔን_ያርገው_ግንባር
፡
፡
፡
ቁመቴ ሎጋ ነው አንገቴ ጠንበለል፤
ስንቷን ሴት ጥያለሁ ዓይኔ ሲንከባለል።
ይመስላል አውቃለሁ የጥርሴ ድርድሩ እንደ ወቶአደር ሰልፍ፤
ከንፈሬን ሳሸሸው እኔን አይተው ማለፍ፤
እንዴት ይታሰባል፤
ጥርሴ እንደው ማግኔት ነው አንዴ ፈገግ ብሎ ብዙ ሴት ይስባል።
የደረቴን ስፋት ተክለሰውነቴን ያየች ቀና ብላ፤
ምራቋን ነው እንጂ እህሏን አትበላ።
ከትከሻዬ ላይ እጇን ጣል አድርጋ ለመሄድ ማትመኝ፤
ቢታሰስ ባገሩ አንድም ሴት አትገኝ።
አሳ መሳይ መልኬን በጣታቸው ዳብሰው ጉንጮቼን ለመሳም፤
የሚያዩት አበሳ አይጣል አይረሳም።
ወንዳወንድነቴ ያረማመድ ልኬ ባለበሰኝ ግርማ፤
እጇን ባፏ ጭና ስንቷን ታዝቤያለሁ እመንገድ ዳር ቆማ።
ጠረኑ ጠርቷቸው የፀጉሬ ክምክሞ፤
ስንቴ ብዬ አውቃለሁ ጀመራቸው ደግሞ።
፡
፡
፡
ሰው እንዴት ያደንቃል እራሱን በራሱ አይጠፋም የሚል ሰው፤
በሴት መሞካሸት እያማረኝ ቀርቶ እድሜዬን ቢገምሰው፤
አድናቂ ሴት ባጣ የወጠንኩት ተግባር፤
ብሎ መለፈፍ ነው ዓይኔን ያርገው ግንባር።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@getem
@getem
@getem
፡
፡
፡
ቁመቴ ሎጋ ነው አንገቴ ጠንበለል፤
ስንቷን ሴት ጥያለሁ ዓይኔ ሲንከባለል።
ይመስላል አውቃለሁ የጥርሴ ድርድሩ እንደ ወቶአደር ሰልፍ፤
ከንፈሬን ሳሸሸው እኔን አይተው ማለፍ፤
እንዴት ይታሰባል፤
ጥርሴ እንደው ማግኔት ነው አንዴ ፈገግ ብሎ ብዙ ሴት ይስባል።
የደረቴን ስፋት ተክለሰውነቴን ያየች ቀና ብላ፤
ምራቋን ነው እንጂ እህሏን አትበላ።
ከትከሻዬ ላይ እጇን ጣል አድርጋ ለመሄድ ማትመኝ፤
ቢታሰስ ባገሩ አንድም ሴት አትገኝ።
አሳ መሳይ መልኬን በጣታቸው ዳብሰው ጉንጮቼን ለመሳም፤
የሚያዩት አበሳ አይጣል አይረሳም።
ወንዳወንድነቴ ያረማመድ ልኬ ባለበሰኝ ግርማ፤
እጇን ባፏ ጭና ስንቷን ታዝቤያለሁ እመንገድ ዳር ቆማ።
ጠረኑ ጠርቷቸው የፀጉሬ ክምክሞ፤
ስንቴ ብዬ አውቃለሁ ጀመራቸው ደግሞ።
፡
፡
፡
ሰው እንዴት ያደንቃል እራሱን በራሱ አይጠፋም የሚል ሰው፤
በሴት መሞካሸት እያማረኝ ቀርቶ እድሜዬን ቢገምሰው፤
አድናቂ ሴት ባጣ የወጠንኩት ተግባር፤
ብሎ መለፈፍ ነው ዓይኔን ያርገው ግንባር።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@getem
@getem
@getem
😁59👍33❤7🔥3🤩1
#ዓይኔን_ያርገው_ግንባር
፡
፡
፡
ቁመቴ ሎጋ ነው አንገቴ ጠንበለል፤
ስንቷን ሴት ጥያለሁ ዓይኔ ሲንከባለል።
ይመስላል አውቃለሁ
የጥርሴ ድርድሩ እንደ ወቶአደር ሰልፍ፤
ከንፈሬን ሳሸሸው እኔን አይተው ማለፍ፤
እንዴት ይታሰባል፤
ጥርሴ እንደው ማግኔት ነው
አንዴ ፈገግ ብሎ ብዙ ሴት ይስባል።
የደረቴን ስፋት ተክለሰውነቴን ያየች ቀና ብላ፤
ምራቋን ነው እንጂ እህሏን አትበላ።
ከትከሻዬ ላይ እጇን ጣል አድርጋ
ለመሄድ ማትመኝ፤
ቢታሰስ ባገሩ አንድም ሴት አትገኝ።
አሳ መሳይ መልኬን
በጣታቸው ዳብሰው ጉንጮቼን ለመሳም፤
የሚያዩት አበሳ አይጣል አይረሳም።
ወንዳወንድነቴ ያረማመድ ልኬ
ባለበሰኝ ግርማ፤
እጇን ባፏ ጭና ስንቷን ታዝቤያለሁ
እመንገድ ዳር ቆማ።
ጠረኑ ጠርቷቸው የፀጉሬ ክምክሞ፤
ስንቴ ብዬ አውቃለሁ ጀመራቸው ደግሞ።
፡
፡
፡
ሰው እንዴት ያደንቃል እራሱን በራሱ
አይጠፋም የሚል ሰው፤
በሴት መሞካሸት እያማረኝ ቀርቶ
እድሜዬን ቢገምሰው፤
አድናቂ ሴት ባጣ የወጠንኩት ተግባር፤
ብሎ መለፈፍ ነው ዓይኔን ያርገው ግንባር።
#ሄኖክ_ብርሃኑ (@yeneeyita)
(@yeneeyita)
@getem
@getem
@getem
፡
፡
፡
ቁመቴ ሎጋ ነው አንገቴ ጠንበለል፤
ስንቷን ሴት ጥያለሁ ዓይኔ ሲንከባለል።
ይመስላል አውቃለሁ
የጥርሴ ድርድሩ እንደ ወቶአደር ሰልፍ፤
ከንፈሬን ሳሸሸው እኔን አይተው ማለፍ፤
እንዴት ይታሰባል፤
ጥርሴ እንደው ማግኔት ነው
አንዴ ፈገግ ብሎ ብዙ ሴት ይስባል።
የደረቴን ስፋት ተክለሰውነቴን ያየች ቀና ብላ፤
ምራቋን ነው እንጂ እህሏን አትበላ።
ከትከሻዬ ላይ እጇን ጣል አድርጋ
ለመሄድ ማትመኝ፤
ቢታሰስ ባገሩ አንድም ሴት አትገኝ።
አሳ መሳይ መልኬን
በጣታቸው ዳብሰው ጉንጮቼን ለመሳም፤
የሚያዩት አበሳ አይጣል አይረሳም።
ወንዳወንድነቴ ያረማመድ ልኬ
ባለበሰኝ ግርማ፤
እጇን ባፏ ጭና ስንቷን ታዝቤያለሁ
እመንገድ ዳር ቆማ።
ጠረኑ ጠርቷቸው የፀጉሬ ክምክሞ፤
ስንቴ ብዬ አውቃለሁ ጀመራቸው ደግሞ።
፡
፡
፡
ሰው እንዴት ያደንቃል እራሱን በራሱ
አይጠፋም የሚል ሰው፤
በሴት መሞካሸት እያማረኝ ቀርቶ
እድሜዬን ቢገምሰው፤
አድናቂ ሴት ባጣ የወጠንኩት ተግባር፤
ብሎ መለፈፍ ነው ዓይኔን ያርገው ግንባር።
#ሄኖክ_ብርሃኑ (@yeneeyita)
(@yeneeyita)
@getem
@getem
@getem
😁37❤21👍21🎉1🤩1