ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
175 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ምኗ_ነው?
:
:
:
ምኗን ነው ግን የወደድከው አልፎ አልፎ ይለኛል ሰው፤
እንዲ ብሎ ሚጠይቀኝ የሆነ ብቃት እንዳነሰው፤
መጠይቁ ያሳብቃል፤
የልቡ ዓይን ያልበራለት ወትሮስ ፍቅርን እንዴት ያውቃል።
:
:
ብዙ ማዕረግ ብዙ ገድል የቀለም ቀንድ ጥልቅ ሀሳቡ፤
እስካልበራ እውር ልቡ፤
ፍቅር ወርሶ እስካልቋጨው፤
ሰው አይሆንም የምድር ጨው።
:
:
ሆነሽልኝ ዝርግፍ ጌጤ፣ ወርቀዘቦ፣ ተክህኖ፤
አዋቂው ሰው ለጋ ሆኖ፤
እንዲያ ብሎ ሲጠይቀኝ ያደርገኛል ደርሶ ብግን፤
የሚጠላው ምኗ ነው ግን?

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@getem
@getem
@getem
76👍25😁8🎉3😱1
#ምኗ_ነው?
:
:
:
ምኗን ነው ግን የወደድከው
አልፎ አልፎ ይለኛል ሰው፤
እንዲ ብሎ ሚጠይቀኝ
የሆነ ብቃት እንዳነሰው፤
መጠይቁ ያሳብቃል፤
የልቡ ዓይን ያልበራለት
ወትሮስ ፍቅርን እንዴት ያውቃል።
:
:
ብዙ ማዕረግ ብዙ ገድል
የቀለም ቀንድ ጥልቅ ሀሳቡ፤
እስካልበራ እውር ልቡ፤
ፍቅር ወርሶ እስካልቋጨው፤
ሰው አይሆንም የምድር ጨው።
:
:
ሆነሽልኝ ዝርግፍ ጌጤ
ወርቀዘቦ ተክህኖ፤
አዋቂው ሰው ለጋ ሆኖ፤
እንዲያ ብሎ ሲጠይቀኝ
ያደርገኛል ደርሶ ብግን፤
የሚጠላው ምኗ ነው ግን?

#ሄኖክ_ብርሃኑ (@yeneeyita)
(@yeneeyita)

@getem
@getem
@getem
67👍37🔥2👎1