ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
“Life is hard; it’s harder if you’re stupid”
# John_Wayne
.
# ሲተረጎም
...
ህይወት ፈተና ነች
ከፍጥረት ትክሻ የማትወርድ ሸክም
በሃዘን እየወጋች
በሳቅ የምታክም
ምንም ለማይሞክር
በተለይ ለቂል ሰው
የክብደቷን መጠን ‘እግዜር’ ኣያድርሰው ።
# KeeP_Your_DistancE

@getem
@getem
#alex_yih
#Hope is important because it can make the present moment less difficult to bear”
#David_Hum
.
# ሲተረጎም
.
ተስፋ የነፍስ ወጋገን ...
በ`ቅኖች ልብ ውስጥ
የሚደምቅ ጮራ
ዛሬን ያሳምራል _ ነገ’ን እያበራ ።
.
# ዴቪድ_ሁም

@getem
@getem
#alex_yih
#ገጣሚ#ፀሃፊ_ተውኔት#መምህርና #የሥነ_ፅሁፍ ተመራማሪ #ደበበ_ሰይፉ #ረቂቅ ግጥሞች መካከል ኣንዷ:
.
#ተይው_እንተወው
.
ተይው እንተወው
የዘመን ቃፊሩን
ማለፍ ኣልቻልንና
ይህ ዓለም ጥበቱ አልመጠነንና
ተይው እንተወው
ውጥኑ ግብ ይሁን
ጅማሬው ፍፃሜ
ቅፅበቷ ሙሉ እድሜሽ
ወቅቷ ዘላለሜ
ተይው እንተወው ።
.
#ደበበ_ሠይፉ

@getem
@getem
#alex_yih
1
“The earth has music for those who listen”
.
#George_Santayana
.
#ሲተረጎም
.
መሬት ኣላት ድርሰት
ምድር ኣላት ዜማ
‘ፀጥ’ ባልን ጊዜ
ጎልቶ የሚሰማ ።
.
#Moral : Practice Mindfulness

#alex_yih
@getem
@getem
#Alex_Yih

"Two things are #infinite : the #universe and human #stupidity ; and I'm not sure about the universe" #Alebert_Einestein
. . .
ይ`ቺን ገራሚ #የኣነስታይን ኣባባል . . . ወደ ግጥም ስቀይራት የሚከተለውን ኣይነት ትርጉም ሰጠችኝ :
.
.
ባሰላሰልኩኝ
ባሰብኩኝ ጊዜ
ማለቂያ የሌለው _ ኣገኛለሁ እውነት
የጠፈር ዳር እና _ የሰው ልጅ ቂልነት
. . .
ኣለማወቃችን _ ኣያልቅም ኣውቃለሁ
ነገር ግን ጠፈርን _ እጠራጠራለሁ

@getem
@getem
@getem
👍1
ሰውየው
--------------------

ካልጠፋ ክዋክብት
ካልጠፋ ጨረቃ
ፀሃይን ወደደ
ነገር ግን
ስትሞቀው ሲቀርባት
ሲቃጠል ሲርቃት
ዘመናቱ ሄደ።

@getem
@getem
@paappii

#alex yih
👍51
አሳ ሆኜ ሳለ
ከወፍ ፍቅር ያዘኝ
አለመብረሬ ነው
ቅር ቅር የሚለኝ።

@getem
@getem
@paappii

#Alex yih
😁8648👍27😢17😱5🎉5🤩3