ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ውሉድ ወወላድ*


የወለደች ኹሉ . . .
እናት አትባልም ! ግብሯ ካልተለየ ፤
የተወለደ ልጅ . . .
አይባልም ጧሪ ! ምግባሩ ካለየ ።

ዘር ስላካፈለ . . .
የአባት መሆን ክብር በከንቱ አይሰጥም !
ከልጅ ስም ቀጥሎ ስሙ አይቀመጥም !

እፍኝትን እይዋት . . .
እናት ትሞታለች ፣ ትውልድ ለማስቀጠል
አባትም ይሠዋል ፣ በፍትወት መቃጠል ።
አንበሳም ደቦሉን . . .
በጊዜው ካልቀጣ ንግስናው ይቀማል ፤
የልጅነት ሥሥት ፣
የአባትነት ድርሻ ለክብር ይወድማል ።

አዎ !
እናት ክብሯን ይዛ ፣
ልጅ ግብሩን ተላብሶ ፣
አባት በስም ነግሦ ፣
ካልተነፃፀረ ፤
የመዳን ምሳሌው ትንቢቱ ተሻረ ።

#የሞት ጥቁር ወተት
#ተስፋሁን ከበደ
@getem
@getem
@beckyalexander
👍2