ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ከ እየሩሳሌም ወደ አለም
#ቃለአብ_ፀጋዬ

ከእየሩሳሌም ሸሽቶ እርቆ
ያለምን ደስታ ውበት ናፍቆ
ከ ኮበለለ ሰነባብቷል
ከ ክንአን ወቶ ካራን ገብቷል፡፡
............................................
ምን ቢጨንቀው ነው ምን ቢጠፋ
እየሩሳሌም ምን ብትከፋ
ከ አበምኔቱ አልተጣላ
ከ ማህሌቱ አልታጎለ
እየሩሳሌም ምን ብትከፋ
ከ ቅጥሯ ወጥቶ ኮበለለ?
......................................
ከ ደብሯ ቆሞ
ዳዊት ደግሞ
ቅኔ ማህሌት
ቆሞ በሌት
መስቀል ተሳልሞ
ጉልበት ስሞ
ከ የኔታ ጋር አልተጣላ
ከ አብነቱ አልታጎለ
እየሩሳሌም ምን ብትከፋ
ከ ደጇ ርቆ ኮበለለ?
.......................................
ተላምዷት ኖሮ ለ አመታት
ከቤተ መቅደስ ሲቀድሳት
ቃልም ሳይሰጣት ለመመለስ
ወይ ተቀብቶ ሳይባል ቄስ
በ ወግ ደጃፏን አልዳበሰ
ጠበል ጠዲቋን አልቀመሰ
እየሩሳሌም ሳትከፋ
ልቤ ሸፍቶ ቢጠፋ
ከ ደጇ ህይወት ሳያጣ
ከ አለም መኖር ቢቃጣ
ያጠናውን ቃል ከሱ ዳስ
ቃለ ወንጌሉን ሲያስታውስ
እንደው ትርጉሙ ቢዘልቀው
ልቤን እውነታው አነቀው፡፡
....................
ጥር 9/2013

@getem
@getem
@getem
👍1
" ማርያምን!" እያለ
#ቃለአብ ፀጋዬ
ኪሴ የመሉትን የሳንቲም ጥርቅም
እራብ ይድፋኝ እንጂ አንዷን አላጎልም
እል እንዳልነበርኩኝ
ግጠምልኝ ብለሽ
ብዕሬን ሳስተፋ ወረቀቴን ሰቀድ
ሳንቲሜን ጨረስኩኝ
ምን አውቅልሽ
ብለሽ?
ቃላትን ወርውሮ ቤት ስለመደብደብ
በለዛ በጥበብ
ስለመግለፅ ሀሳብ
. . . . . . . .. .. . .. . .. ... . .. . . .. . .
ሂጂ እሱን ጠይቂ . . .

ቃላት መርጦ ቆርጦ
በወግ ያገንሻል
አይ! ካልሽ አይገደውም
ቃላት አስሸብርቆ ልዕልት የሰኝሻል
"ማርያምን!" እያለ
ማመን መቀበልን ላንቺ ይተውልሻል

እኔ እንዲያ አይደለሁ . . . . .
ምትሐት ካለው ምናብ
የሚያማልል ሐሳብ
ምሉዕነት ካለው
ድንቅ ችሎታው ላይ
ጥቂት እንዲያደርስሽ
ሚካኤል ጋር ሄደሽ

ቅጥ የጣ ፍላጎት
ግዙፍ ግብዝነት
ይህ ሁሉ አመልሽን . . .
በቃላት ቆራርጦ
ብዙ ትንንሾች አድርጎ አስቀምጦ
እንደምትፈልጊው
በስንኝ ቆጣጥሮ እጅግ ያረቅሻል
"ማርያምን!" እያለ
እንኳን እምነትሽን ልብሽን ይወስዳል፡፡

እሱን ፈራሁ እንጂ: እነግረው ነበረ
ማርያም በቸረችው
መግጠምን ያውቀዋል ቃል እየቀመረ፡፡
@Kalsagi
ነሀሴ 4/2013
ለ፡ ሚካኤል አስጨናቂ
ለድንቅ ችሎታ ጥቂት ሙገሳን ለመለገስ. . . ጥሩ ለሰራም ምስጋና ይገባው ዘንድ እነሆ፡፡

@getem
👍5