#አትሟት
© ሲራክ ወንድሙ
.
መሬት የሚጠርገው የቀሚሷ ጫፉ፣
በወንጌል ቢታሰር የሚቀድስ አፉ ፣
ምናልባት እዚህ ቤት...
ፀሀይ ፈገግታዋን የተሻማ ሁሉ ፣
ከፈገግታ ጀርባ መከልከል እንዳለ የነገራት ውሉ ፣
ባይገባው ነው እንጂ...
እስኪ አትሟት ይህቺን...
ለቆረባት ሁሉ እህትነት ይዟት ከመጣው ብትቆርብም ፣
እሷ ቀሚሷን ነው ሳቋን አትሰስትም።
................... //////....................
ሲራክ @siraaq
< የብርሃን መንገድ >
@getem
@getem
@getem
© ሲራክ ወንድሙ
.
መሬት የሚጠርገው የቀሚሷ ጫፉ፣
በወንጌል ቢታሰር የሚቀድስ አፉ ፣
ምናልባት እዚህ ቤት...
ፀሀይ ፈገግታዋን የተሻማ ሁሉ ፣
ከፈገግታ ጀርባ መከልከል እንዳለ የነገራት ውሉ ፣
ባይገባው ነው እንጂ...
እስኪ አትሟት ይህቺን...
ለቆረባት ሁሉ እህትነት ይዟት ከመጣው ብትቆርብም ፣
እሷ ቀሚሷን ነው ሳቋን አትሰስትም።
................... //////....................
ሲራክ @siraaq
< የብርሃን መንገድ >
@getem
@getem
@getem
❤1
............. ስንቅና ማህሌት .............
_ © ሲራክ ወንድሙ _
.
እኩለ ሌሊት ላይ - መርዶ እንዳባተተው ፥
እኩይ ዜና ሰምቶ - ቀልቡ እንዳቃተተው ፥
በሀሳብ ናውዤ......
በምናብ ተጉዤ.....
ሽሚያ እንደበዛበት የሰንበቴ መና ፥
በናፍቆትሽ ሳሳው ፥
በትዝታሽ ጠናው ዘንድሮም እንዳ'ምና።
#
እንደኮከብ ድምቀት - እንደጥቢ ፍካት ፥
እንደብርሃን ዥረት - እንደሞገድ ንጣት ፥
የሚያበራ አይንሽን - የተራበ አይኔ ፥
ከስጋው ተኳርፎ - ገብቶ ከምናኔ ፥
አለም እንደናቀው - አለም እንደናቃት ፥
እንቅልፍም በኔ ላይ - መሪር ኩርፊያ አላት።
.
ኦኦኦኦኦ!..
.
ሰማኒያ አሀዱ ፥
የቅዱሳን መፅሀፍ - አንዱ ሆኖ በአንዱ ፥
ከመስኮቱ ምዕራብ - ከማዕዘኑ ቀዬ ፥
ይታየኛል ድርድር - ከወደ ግርጌዬ ።
.
አሁን....
ዘራሰብ በልማድ ከትንሽ ሞቱ ጋር ግብግብ ገጥሟል።
እኔ...
ትንሽ ህመም አማኝ ፥
ትንሽ ሞት ረስታኝ ፥
ፍቅርሽን እያልኩኝ - እምከነከናለሁ፥
በዚህ ድኩም ሌሊት - አንቺን አስባለሁ።
.
ኤዲያ!
.
የትዝታን ክቡድ - ቀንበር ፣
የናፍቆትን ግዙፍ - ሞፈር ፣
አጥምጄ በላዬ - በምኞት ቤት ድግር፣
በኑረት ክንዴ ላይ - እየወዘወዝኩት ፣
የእምባዬን ስል ጅራፍ - እያወናጨፍኩት፣
የነብሴን ውብ ጋራ - ብራብሽ አረስኩት ።
.
እህ....
.
እኔ ቀድሶ አዳሪ - የደብር ሲምቢሮ ፣
አንች የባላባት ጭራ - የከበርቴ ሮሮ፣
እንደ የኔታ ጋቢ - ውብ ገፅሽ ሳያድፍ፣
በሳቅሽ ቅላፄ ቅኔ ሳይዘረፍ፣
ምንጯ ስር ብቅ በይ - እኔም ከዛው አለው፣
ለሀሴትሽ ጉቦም - ዋሽንቴን ይዣለሁ።
.
እምም...
ኩርማን ለማደሪያ - ሰው አጥር ታክኬ ፣
እንደ ፀሎት ምልጃ - አይኔን ወዲያ ልኬ፣
የህዝቡን መማረር - ይሁን ብዬ ድኬ፣
እንደ በላኝ ቅማል - በደል ሲያሳክከኝ፣
ቀስሳለሁ ብሎ ደብር መቀላወጥ እንደ ውርደት ታየኝ።
.
ኦኦኦኦ!..
.
ያቺ ከሲታዋ - ውብ አኩፋዳዬ...
ግብር እንደጠሩት - እንደ ሆዳም እረኛ፣
ፍርፋሪ ሞልቷት - ጠጋግባ በማኛ፣
ጀምበር ስታቅላላ - ከደብር ብትደርስም፣
ለሚያያት ነው እንጂ - እንደእኔ ለኖራት .. በጭራሽ አትደንቅም።
.
ለምን??
.
እንደጭን ስር ቅማል ፣
ሀሜት ያሳክካል ።
አሽሙር ያሳምማል።
.
አምና በዚህ ጊዜ - ከዚያ ከአረን-ጓዴ፣
ግራሩ ስር ቆሜ - በአርባ ጦም ሁዳዴ፣
እህል ውሃ ሳልል - አይቼሽ ለመግደፍ፣
ከእግዜር ጋር ቅያሜ - ለመያዝ ስጣደፍ፣
ለውብ አይንሽ ብዬ - በሀፂያት ታምሜ ፣
ከእርኩስ ሀሳብ ዳራ - ምልዋጤን ደግሜ፣
እባብ ሆኜ መጣው ....
አባትሽ ገደሉኝ - አፈር ልሼ ነቃው።
.
ደግሞም በነጋታው....
.
ሰው መሆን ውበቴን - ፍቅርሽ ሲያስመንነው
ዳግም እርግብ ሆኜ አጥርሽ ላይ ብቆም
የእረኞች ወንጭፍ - ቃታው የከረረ ፣
ጠጠር ተወርውሮ - አክናፌን ሰበረ።
.
ኦኦኦኦ.....!
.
ሰማኒያ አሀዱ ፣
የቅዱሳን መፅሀፍ - አንዱ ሆኖ በአንዱ ፣
ከመስኮቱ ምዕራብ - ከማዕዘኑ ቀዬ፣
ይታየኛል ድርድር - ከወደ ግርጌዬ።
.
አሁን.....
.
ወዲያ ወዲያ ወዲያ ወዲያ ከአምባው ላይ፣
ወዲያ ከደብሩ ላይ፣
ወረብ አሰካክሮት - ደወል አስደንግጦት ፣
ከቤተ መቅደሱ - ደርሶ የሚሸፍት፣
ይሰማኛል ለእኔ - የሌ'ቱ ማህሌት፣
የዲያቆናት ዜማ - የካህናት ፀሎት።
ዜማው ምጥን ያለ እንደድምፅሽ ቃና ፣
እንደወፍ ዝማሬ - እንደመላዕክት ዳና።
ጥፍጥ ፣ እርግት ያለ - እንደ እንደአይንሽ ብርሃን ፣
ኑረትን የሚያሞቅ - የነብስ ሀሴት ኩርማን ።
.
እናልሽ..
.
አሁን በዚህ ሰዓት....
አሁን በዚህ ቅፅበት...
የምኩራቡ እጣን - በሰመመን ሸቶኝ፣
እጅብ ያለ ጉሙ - ሲንገዋለል ታይቶኝ፣
የወረቡ ስምረት - በቁሜ አስክሮኝ፣
የቅዳሴው ዜማ - በመዳፉ ዳሶኝ ፣
ከድኩም አልጋዬ - ፈገግታሽ አብርሮኝ ፣
ካልጠራሁት አለም
ከኖርኩበት ቀዬ - አድማስ አሻገረኝ።
.
እና
.
ደብሬን ክጃለሁ - ደብር ነሽ ለነብሴ ፣
ቅዳሴም ትቻለሁ - አንቺው ነሽ ምላሴ።
.
እናም .....
.
እንደየኔታ ጋቢ ውብ ገፅሽ ሳያድፍ ፣
የእድሜሽ ጀምበር ጠልቆ ውበትሽ ሳይረግፍ ፣
በሳቅሽ ቅላፄ ቅኔ ሳይዘረፍ ፣
ምንጯ ስር ብቅ በይ እኔም ከዛው አለው ፣
ለሀሴትሽ ጉቦም ዋሽንቴን ይዣለው።
////////////___ ስንቅና ማህሌት //////////
_ _ © ሲራክ ወንድሙ ____
ታህሳስ ፳፻፲፫ ዓ.ም
@getem
@getem
_ © ሲራክ ወንድሙ _
.
እኩለ ሌሊት ላይ - መርዶ እንዳባተተው ፥
እኩይ ዜና ሰምቶ - ቀልቡ እንዳቃተተው ፥
በሀሳብ ናውዤ......
በምናብ ተጉዤ.....
ሽሚያ እንደበዛበት የሰንበቴ መና ፥
በናፍቆትሽ ሳሳው ፥
በትዝታሽ ጠናው ዘንድሮም እንዳ'ምና።
#
እንደኮከብ ድምቀት - እንደጥቢ ፍካት ፥
እንደብርሃን ዥረት - እንደሞገድ ንጣት ፥
የሚያበራ አይንሽን - የተራበ አይኔ ፥
ከስጋው ተኳርፎ - ገብቶ ከምናኔ ፥
አለም እንደናቀው - አለም እንደናቃት ፥
እንቅልፍም በኔ ላይ - መሪር ኩርፊያ አላት።
.
ኦኦኦኦኦ!..
.
ሰማኒያ አሀዱ ፥
የቅዱሳን መፅሀፍ - አንዱ ሆኖ በአንዱ ፥
ከመስኮቱ ምዕራብ - ከማዕዘኑ ቀዬ ፥
ይታየኛል ድርድር - ከወደ ግርጌዬ ።
.
አሁን....
ዘራሰብ በልማድ ከትንሽ ሞቱ ጋር ግብግብ ገጥሟል።
እኔ...
ትንሽ ህመም አማኝ ፥
ትንሽ ሞት ረስታኝ ፥
ፍቅርሽን እያልኩኝ - እምከነከናለሁ፥
በዚህ ድኩም ሌሊት - አንቺን አስባለሁ።
.
ኤዲያ!
.
የትዝታን ክቡድ - ቀንበር ፣
የናፍቆትን ግዙፍ - ሞፈር ፣
አጥምጄ በላዬ - በምኞት ቤት ድግር፣
በኑረት ክንዴ ላይ - እየወዘወዝኩት ፣
የእምባዬን ስል ጅራፍ - እያወናጨፍኩት፣
የነብሴን ውብ ጋራ - ብራብሽ አረስኩት ።
.
እህ....
.
እኔ ቀድሶ አዳሪ - የደብር ሲምቢሮ ፣
አንች የባላባት ጭራ - የከበርቴ ሮሮ፣
እንደ የኔታ ጋቢ - ውብ ገፅሽ ሳያድፍ፣
በሳቅሽ ቅላፄ ቅኔ ሳይዘረፍ፣
ምንጯ ስር ብቅ በይ - እኔም ከዛው አለው፣
ለሀሴትሽ ጉቦም - ዋሽንቴን ይዣለሁ።
.
እምም...
ኩርማን ለማደሪያ - ሰው አጥር ታክኬ ፣
እንደ ፀሎት ምልጃ - አይኔን ወዲያ ልኬ፣
የህዝቡን መማረር - ይሁን ብዬ ድኬ፣
እንደ በላኝ ቅማል - በደል ሲያሳክከኝ፣
ቀስሳለሁ ብሎ ደብር መቀላወጥ እንደ ውርደት ታየኝ።
.
ኦኦኦኦ!..
.
ያቺ ከሲታዋ - ውብ አኩፋዳዬ...
ግብር እንደጠሩት - እንደ ሆዳም እረኛ፣
ፍርፋሪ ሞልቷት - ጠጋግባ በማኛ፣
ጀምበር ስታቅላላ - ከደብር ብትደርስም፣
ለሚያያት ነው እንጂ - እንደእኔ ለኖራት .. በጭራሽ አትደንቅም።
.
ለምን??
.
እንደጭን ስር ቅማል ፣
ሀሜት ያሳክካል ።
አሽሙር ያሳምማል።
.
አምና በዚህ ጊዜ - ከዚያ ከአረን-ጓዴ፣
ግራሩ ስር ቆሜ - በአርባ ጦም ሁዳዴ፣
እህል ውሃ ሳልል - አይቼሽ ለመግደፍ፣
ከእግዜር ጋር ቅያሜ - ለመያዝ ስጣደፍ፣
ለውብ አይንሽ ብዬ - በሀፂያት ታምሜ ፣
ከእርኩስ ሀሳብ ዳራ - ምልዋጤን ደግሜ፣
እባብ ሆኜ መጣው ....
አባትሽ ገደሉኝ - አፈር ልሼ ነቃው።
.
ደግሞም በነጋታው....
.
ሰው መሆን ውበቴን - ፍቅርሽ ሲያስመንነው
ዳግም እርግብ ሆኜ አጥርሽ ላይ ብቆም
የእረኞች ወንጭፍ - ቃታው የከረረ ፣
ጠጠር ተወርውሮ - አክናፌን ሰበረ።
.
ኦኦኦኦ.....!
.
ሰማኒያ አሀዱ ፣
የቅዱሳን መፅሀፍ - አንዱ ሆኖ በአንዱ ፣
ከመስኮቱ ምዕራብ - ከማዕዘኑ ቀዬ፣
ይታየኛል ድርድር - ከወደ ግርጌዬ።
.
አሁን.....
.
ወዲያ ወዲያ ወዲያ ወዲያ ከአምባው ላይ፣
ወዲያ ከደብሩ ላይ፣
ወረብ አሰካክሮት - ደወል አስደንግጦት ፣
ከቤተ መቅደሱ - ደርሶ የሚሸፍት፣
ይሰማኛል ለእኔ - የሌ'ቱ ማህሌት፣
የዲያቆናት ዜማ - የካህናት ፀሎት።
ዜማው ምጥን ያለ እንደድምፅሽ ቃና ፣
እንደወፍ ዝማሬ - እንደመላዕክት ዳና።
ጥፍጥ ፣ እርግት ያለ - እንደ እንደአይንሽ ብርሃን ፣
ኑረትን የሚያሞቅ - የነብስ ሀሴት ኩርማን ።
.
እናልሽ..
.
አሁን በዚህ ሰዓት....
አሁን በዚህ ቅፅበት...
የምኩራቡ እጣን - በሰመመን ሸቶኝ፣
እጅብ ያለ ጉሙ - ሲንገዋለል ታይቶኝ፣
የወረቡ ስምረት - በቁሜ አስክሮኝ፣
የቅዳሴው ዜማ - በመዳፉ ዳሶኝ ፣
ከድኩም አልጋዬ - ፈገግታሽ አብርሮኝ ፣
ካልጠራሁት አለም
ከኖርኩበት ቀዬ - አድማስ አሻገረኝ።
.
እና
.
ደብሬን ክጃለሁ - ደብር ነሽ ለነብሴ ፣
ቅዳሴም ትቻለሁ - አንቺው ነሽ ምላሴ።
.
እናም .....
.
እንደየኔታ ጋቢ ውብ ገፅሽ ሳያድፍ ፣
የእድሜሽ ጀምበር ጠልቆ ውበትሽ ሳይረግፍ ፣
በሳቅሽ ቅላፄ ቅኔ ሳይዘረፍ ፣
ምንጯ ስር ብቅ በይ እኔም ከዛው አለው ፣
ለሀሴትሽ ጉቦም ዋሽንቴን ይዣለው።
////////////___ ስንቅና ማህሌት //////////
_ _ © ሲራክ ወንድሙ ____
ታህሳስ ፳፻፲፫ ዓ.ም
@getem
@getem
❤1