ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ከአንድ_ትውልድ_የበለጠ
( አዲሱ ጉግሳ )

ለአራዳዎቹ ለኛ ባኖ መንቃት
ጭስ ሆኖ ተራቆ መብቃት
ባህር ተሻግሮ ቀድሞ መማር
ከዛ አምጥቶ ደምቆ ማማር

አዎ ለኛ መሰልጠን መራቀቅ
ከራስ ባህል ተፋቶ መላቀቅ
አፋልጎ ለምኖ መጣበቅ

አዎ ለኛ ጀግንነት
አዎ ለኛ አራድነት
ቁስ ይዞ ቅል ሆኖ መገኘት
በቂቤ አፍ በወሬ መዳኘት
ሃብት አካብቶ በገንዘብ መዋኘት

አዎ ለኛ ሠልጥነን ላወቅነው
ትላንትን ክደን ዛሬን ከነገ ለተበደርነው
ክቡር ንቀታችን በጥቁርነቱ ያፈረው
ቅንቅናም ጥጋብችን ባለመገዛቱ ያኮረፈው
አተላው ዕውቀታችን ባለመረገጡ የሚቆጨው
ከንቱ ናፍቆታችን ብገዛ ብሎ ለነጭነት እራሱን ያጨው
እንዲህ በተከበረበት ወርዶ ያቀጨጨው

የጠፋብን ልብ ቢኖር ነው የተሰወረ
የራሱን ክብር አርቆ የወረወረ
የአያቱን ታሪክ ገፍቶ የቀበረ

የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ
የሚባል ተረት የሆነው ሞቱ!
አዲስ ትውልድማ መቷል በትላንቱ የሚስቅ
አዲስ ዘመንማ ቆሟል ታሪኩን የሚንቅ

ከዘር ዘራችን የተጣባ
ከደም ደማችን የተጋባ
አዲስ ትውልድማ ደርሷል የሚንቅ ትላንቱን
አዲስ ዘመንማ ጠብቷል የበላ እትብቱን

ምንም ባያረግም ጉራው መከራ
ምንም ባንፈይድም ወሬው ጠንካራ
ባህር ተሻግሮ ለምኖ ለመኖር
ከሰው በታች ሆኖ ለማደር በነውር
ለእሳት አባቱ አመድ ልጁ ደርሷል
ከአያቱ ጠላት ስጋ ልጁ ብሷል
የቤቱን ሞት ከጠላት ተውሷል

ግና ፦
አንዱ ምርቃት በቅን ተወርቶ
ቃል ተሰተካክሎ ተዘርቶ
ቀለም ተስተካክሎ ተቀብቶ
ኩርማን ትውልድ አለ በአያቱ ተባዝቶ
ጀግንነት ያማረው በአባቱ ተስማምቶ

በሚገፋው ዘመን ውስጥ
ከሚበላው የቃል ምስጥ
ከሚያሾፈው የስም ወዳጅ
ከሚሸጠው የወገን አራጅ

ከሁሉም ከሁሉም የነቃ
ለሃገር ምድሩም የበቃ
መነሻውን ያወቀ
በትውፊቱ የደመቀ
ቆሞ የመሞትን ዘመን ያመለጠ
የከረፋን ትውልድ የበለጠ
ዛሬን ወደ ትላንት ይዞ የፈረጠጠ

ከሚያኮራው ታሪክ ላይ የተቀመጠ
ላስከበረው ገድል የተመሰጠ
አንድ ልጅ አለ ብቻውን አንድን ትውልድ የበለጠ
----------------

#ሚካኤል_ሚሊዮን እግርህ በረገጠበት ሁሉ አድናቂው ማንነቴ አበሮህ ነው። from addis gugsa!

@getem
@getem
@paappii