© መላኩ አላምረው
ደሃ የሆንህ እንደሁ...
ደሃ የሆንህ እንደሁ... ሲኦልህ ናት ምድር
ውልደትህ፣ ዕድገትህ... ኑሮህም አያምር !!!
...
ደሃ የሆንህ እንደሁ...
ከአፈር ቤት ተወልድህ - በአፈር ትድሃለህ
የአፈር ሲሳይ ርቆህ...
ከአፈር ከቆሻሻ - ምግብ ትለቅማለህ
በእንጀራ ሳይሆን - በረኃብ ታድጋለህ !
.
(በደሃ ሀገር ውስጥ - በውል ላስተዋለ
ምግብ ተከልክሎ - በረኃብ የሚያድግ አለ)
.
ልብስህም አፈር ነው - ቆሻሻ ያልፀዳ
ኑሮህ የሰቀቀን - የሰቆቃ፣ የዕዳ....
.
ዳኛው ቢፈርድ ባንተ - ስለማትሰጥ ጉቦ
መንግሥት ቢቀጣ አንተን - ያለ ፍርድ ያለ አግቦ
ግብር ቢጣል በአንተ - ያለህን ለመውሰድ
ምትገፋው አንተ - ከሀገር እንድትሄድ
የምትሞተው አንተ - በስደትህ መንገድ
.
ስደት አልሆን ብሎህ - መጠጊያ ፍለጋ
ሰው ከማይኖርበት...
የቆሻሻ ክምር - ሄደህ ብትጠጋ
ቆሻሻውም በአቅሙ - እንዳየህ በሩቁ
ሊበላህ ያዛጋል - ይበዛል ምራቁ
.
ሀብታም ከእርሱ አርቆ - የጣለው ቆሻሻ
ግማቱን ታግሰህ... ከጎኑ፣ ከስሩ ልትኖር ብትሻ
እርሱም ቢሆን ደሃን - አይፈልግምና
በነገ ዓለምህ - ተስፋህ እንዳይፀና
አንድ ቀን ጠብቆ - ኃይል አስተባብሮ
በላይህ ተጭኖ - ይገድልሃል ቀብሮ
...
.
በቃ ደሃ ከሆንህ - ገሃነምህ ናት ምድር
እንኳን ኑሮህና - ሞትህም አያምር !!!
-----//-----
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
@getem
@getem
@getem
@kinchebchabi
ደሃ የሆንህ እንደሁ...
ደሃ የሆንህ እንደሁ... ሲኦልህ ናት ምድር
ውልደትህ፣ ዕድገትህ... ኑሮህም አያምር !!!
...
ደሃ የሆንህ እንደሁ...
ከአፈር ቤት ተወልድህ - በአፈር ትድሃለህ
የአፈር ሲሳይ ርቆህ...
ከአፈር ከቆሻሻ - ምግብ ትለቅማለህ
በእንጀራ ሳይሆን - በረኃብ ታድጋለህ !
.
(በደሃ ሀገር ውስጥ - በውል ላስተዋለ
ምግብ ተከልክሎ - በረኃብ የሚያድግ አለ)
.
ልብስህም አፈር ነው - ቆሻሻ ያልፀዳ
ኑሮህ የሰቀቀን - የሰቆቃ፣ የዕዳ....
.
ዳኛው ቢፈርድ ባንተ - ስለማትሰጥ ጉቦ
መንግሥት ቢቀጣ አንተን - ያለ ፍርድ ያለ አግቦ
ግብር ቢጣል በአንተ - ያለህን ለመውሰድ
ምትገፋው አንተ - ከሀገር እንድትሄድ
የምትሞተው አንተ - በስደትህ መንገድ
.
ስደት አልሆን ብሎህ - መጠጊያ ፍለጋ
ሰው ከማይኖርበት...
የቆሻሻ ክምር - ሄደህ ብትጠጋ
ቆሻሻውም በአቅሙ - እንዳየህ በሩቁ
ሊበላህ ያዛጋል - ይበዛል ምራቁ
.
ሀብታም ከእርሱ አርቆ - የጣለው ቆሻሻ
ግማቱን ታግሰህ... ከጎኑ፣ ከስሩ ልትኖር ብትሻ
እርሱም ቢሆን ደሃን - አይፈልግምና
በነገ ዓለምህ - ተስፋህ እንዳይፀና
አንድ ቀን ጠብቆ - ኃይል አስተባብሮ
በላይህ ተጭኖ - ይገድልሃል ቀብሮ
...
.
በቃ ደሃ ከሆንህ - ገሃነምህ ናት ምድር
እንኳን ኑሮህና - ሞትህም አያምር !!!
-----//-----
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
@getem
@getem
@getem
@kinchebchabi
የናፍቆት መድሀኒት
~~~~~~~~~~~
ናፍቆት ልቤን ሰልቦ ... ሲገዘግዘኝ==
ፓራስታሞል ሆኖ ... ድምፅሽ ፈወሰኝ
ደጋግመሽ ደውይ
ከስልኬ ጫፍ ላይ መድሀኒት እንዳገኝ
© ዳንኤል ከበደ
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
@getem
@getem
@gebriel_19
~~~~~~~~~~~
ናፍቆት ልቤን ሰልቦ ... ሲገዘግዘኝ==
ፓራስታሞል ሆኖ ... ድምፅሽ ፈወሰኝ
ደጋግመሽ ደውይ
ከስልኬ ጫፍ ላይ መድሀኒት እንዳገኝ
© ዳንኤል ከበደ
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
@getem
@getem
@gebriel_19
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
የተስፋ ቃል
ፀሀፊ ዳግም ደጀኔ (ሄራን)
✍ @dagiamen12
አንባቢ ሱራፌል ጌትነት
ሱራ ቢራቢሮ🦋
@surabirabiro 🦋
@getem
@getem
@getem
የተስፋ ቃል
ፀሀፊ ዳግም ደጀኔ (ሄራን)
✍ @dagiamen12
አንባቢ ሱራፌል ጌትነት
ሱራ ቢራቢሮ🦋
@surabirabiro 🦋
@getem
@getem
@getem