ግጥም ብቻ 📘
67.4K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
* ኑ .ዛ . ዜ .***

ጌታ ሆይ....
ከሞትኩኝ በሁዋላ....
ሚስቴን እንዳያይዋት፤
ህይወቷን በሙሉ ቤት ዘግተህ አቆያት።
እነዛ ከዋክብት ፣ አብረቅራቂ አይኖቿን
የማታ ብርሀን ፣ የቀን መኩሪያዎቿን
በሌላ ተማርከው ፣ግራ እንዳይገባቸው
መአቱን አውርደህ ድርግምግም አርጋቸው።
...............................................
ገጣባ አርገህ ተወው ፣ ያንን ሐር ጸጉሯን
ሌላ ከሚያይብኝ ፣;ትቅር ባዶ ቅሏን::
..............
ከሞትኩኝ በሁዋላ....
ቀጥ ብሎ የቆመ ፣ ያን ሰልካካ አፍንጫ
ከርክመህ ጣልልኝ ፣ በያዝከው መቁረጫ
ያንን የሚያሰጎመጅ ፣ ያን እንጆሪ ከንፈር
ፍቀድልኝና.....
ወስላታ ሳይቀምሰው ከ'ኔ ጋር ይቀበር::
....................
ከሞትኩኝ በሁዋላ....
እነዛ ጡቶቿን ፣ እንደጦር የሰሉ
ኪንታሮት አክለው ፣ የት ሄዱ? ይባሉ
ያንን ችቦ ወገብ ፣ ቀጥኖ የተሰቀለው
ወጥረህ ወጥረህ ፣ ከበሮ አሳክለው::
.
ከሞትኩኝ በሁዋላ....
ጀግና የሚያሳድድ ፣ ያን ኩሩ ዳሌዋን
ድንገት ንሳትና ፣ ትፈልግ ሁዋላዋን።
በማታ በማታ.....
ወጣ ብሎ መግባት ፣ ሁሉ እንዳያምራቸው
እግሮቿን አልምሸህ ፣ መሄድ ይሳናቸው::
..................
ኡፍፍፍ....
እንዲያውም ወፍ አርጋት ፣ በአየር ትመላለስ
ወንድ አንኩዋኩቶ አይጥራት....
ጎጆዋን በዛፍ ላይ ፣ በስንጥር ትቀልስ።
በቃ....
በፍቅር ጎዳና ፣ ሌላ ከሚመራት
ፈቃድህ ከሆነ …
ሳትሞት በቁሟ ፣ ከ'ኔ ጋር ቅበራት።
.
.
አምላኬ....
መቼም መሄዴ ነው...
ጊዜዬን ጨርሼ ፣ መሰናበቴ ነው
ብቻ አደራህን...ብቻ አደራህን...
ከሞትኩኝ በሁዋላ ፣ ማንም እንዳይነካት
ማንም ተመኝቶ ፣ በልቡ እነዳይለካት።
........
በቃ አልፈልግማ ፣ በቃ እንዳያዩብኝ
ከህመሜ ይበልጥ ፣ አልጋ ላይ ከጣለኝ
ከሞትኩኝ በሁዋላ .....
የሌላ ስትሆን ፣ ማሰቡ ነው 'ሚያመኝ::

#ፌስቡክ_መንደር

@getem
@getem
@getem
ግጥም ልክ እንደ አትክልት ነው በኮተኮትከው መጠን በውበቱ መልሶ ያረሰርሳል ተውቦ ያስውባል......

ግጥም ልክ እንደ አትክልት እምቡጥ 'የመገለጥ ነው!!

ጎበዝ ገጣሚ ነው ሀሳቡ ከእድሜው በላይ ናቸው። ለነገሩ እድሜ ተራ
ነገር ነው።በንቃት ሁሉን የቅርበት ክንዋኔ ለሚያጤን ሰው ባስተውሎት እንጂ በማርጀት የሚመጣ ልባምነት የለም። አስተዋይ ነው ልባም ጭምር!

#በጣም በቅርቡ የምትወጣ "ሰው ፍቅር ናፍቆት " የግጥም ስብስብ ተገላግሏል......ገዝታቹ ብታነቡ ትወዱታላቹ! በእርግጠኝነት!!

ግጥሞቹን ለማንበብ ከሻቹ ደሞ #ፌስቡክ ላይ "ዳግም ሔራን" ብላቹ ተወዳጁት አትራፊ ትሆናላቹ!!

ሰላም እደሩልኝ!💚

@getem
@getem
@Nagayta
👍1