ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ከሩካቤ ወይራ፥ በጨመቅሁት ቅባት
ስባርክ አደርኩኝ፥
ደረቅ ምዑት ዳሌ፥ቀዝቃዛ በድን ባት።
ሕይወት እና ፍትወት
አልተጠባበቁም
አንድ ላይ ለማርጀት
ለቁርባን አልበቁም።
አንዱ አንዱን ቀደመ
ቀድሞውን ሳይጠብቅ፥
የቅባቱን ማዕድ፥ኋለኛው ታደመ
ፍትወት አላወጣም፥ የሕይወትን ተዝካር
ለብቻው ተጣሞ፥ ተንገዳገደበት፥ የጋራውን ስካር።
እነሆ ሰክሮም አልቀረ፥ ሲለቀው ነቃ ሩካቤ
ስካር ያንከራተተው፥ ማረፊያ አገኘ ውቃቤ...
ውቃቤ ተቅበዘበዘ፥ ሕይወት በድን ላይ ጨፈረ
ሀቅ እውነታውን ሊናገር፥ ከቅባቱ ላይ ሰፈረ...
መስፈሩን እንደተረዳ፥
ሕይወቱ መሞቷ ገባው፥ ፍትወት ዕርቃኑን አፈረ።
የሩካቤ ሰፈፍ፥
ባወረዛው ፈትል፥ ጧፌን ሳበጅ ውዬ
ሳበራው አደርኩኝ፥
እስትንፋስ ያጣውን፥ የሞተውን ቀዬ
እርግጥ ቀዬው ሞቷል
ዞር ዞር ቢሉ፥
ሕይወት ያቃጠለው፥ ደማቅ ቀዬ ሞልቷል
ግን ጧፌ ፈዝዛለች
ከጋለው ከሞቀው፥
ከበራው ባስገባት፥ እንዴት ትታያለች?
እርግጥ ቀዬው ሞቷል፥ ሞቷል ነፍስ የለውም
ትንፋሽ የተራበ፥
ትርታ የጠማው፥ ጭራሽ አያየውም
ጣለለት እንጂ እኔን
ጨለማ እሚማትር፥ በድን የሚናፍቅ፥ የኩለ ሌት ጋኔን
ጣለለት እንጂ እኔን...
ባለወይራ ቅባት፥ ባለሰፈፍ ፈትል
ርሃቤ 'ነፍስ ያለው' ፥ ደመ ሙቅ የማትል
ጥማቴን "ነፍስ አልባ" ፥ ነው ብዬ የማልጥል
ጣለለት ለዳሌው..
ጣለለት ለባቱ፥
ጣለለት ለቅዬው፥ ጣለለት እንጂ እኔን
ሬሳ እማይጠላ፥
ሙት የማይጠየፍ፥ የኩለ ሌት ጋኔን
ጣለለት እንጂ እኔን።

@getem
@getem
@paappii

#Rediet aseffa
ተደፈረች
ፅጌረዳነቷን፥በሾህ ተሰፈረች
የፈካች በደስታ
በጣር ተቀጠፈች
ረገፈች።
ለሙግት ለፍትህ፥ በዳኛ አስነግራው
ቆራጭ በቀኝ ቆመ፥ ቆመች በስተግራው
ተመልክታ
ፍትሕ ተመክታ
የእንባ እጢዎቿን፥ ካፏ ጋራ ከፍታ
የፈሰሰን ሕይወት፥ በቃላት ለማበስ
የተራቆተን ክብር፥ እስትንፋስ ለማልበስ
አለች ቀና ጎምበስ...
ለፍርድ ለፍትሕ፥
የጠራችው ዳኛ፥ እግዜር ስለነበር
ዳኛውን ካርጋፊው፥ ጠምዶ ባንድ ቀንበር
ከረገፈችበት፥ ከቀጣፊው እግር
እስከ እግዚ'ያሔር የሚያርስ፥ፈለቃት ንግግር...
አለች
"መርገፍ መንታው ነበር፥ መፍካት ሲጠነሰስ
ከሕይወት እኩል ነው፥ መሞት የሚለገስ
የመጣ እንደሚሄድ፥ ሀቁ የታወቀው
መርገፍ አይበርደውም፥ መፍካትም አይሞቀው።
ማርገፉ በደል ነው?
ቀን የሚያረግፈውን፥ ቀድሞ መከወኑ?
የጊዜን ብርቱ ክንድ፥
የእርጅናን በትር፥ መስሎ መተወኑ
ያንተን የእግዚ' ያሔርን፥
የማርገፍ አለንጋ፥
ተቀብሎ መግረፍ፥በደል ነው በውኑ?
የለም የለም
ማርገፍ ግፍ አይደለም
ግፍ እንኳ ነው ቢባል፥
ከፍጡሩ ስሜት፥ በላይ መች ይሰፋል?
ለማርገፍ ከማፍካት፥
ለመግደል ከመፍጠር፥ እኩል መች ይከፋል?
በል ይቀየርልኝ፥
ከምድር ወደ ሰማይ፥ ይዙርልኝ ክሱ
ባ'ምሳያህ ፈጥረኸው፥
እያንፀባረቀ፥
አንተን አሳየ እንጂ፥ መች በደለኝ እሱ?"

@getem
@getem
@paappii

#Rediet Aseffa