#የአዳም ተቃርኖ!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።።።።
የአዕዋፍ ፣ የአዝርዕርቱ
ያውሬ ፣ የእንስሳቱ ፥ ንጉስ አ'ርጎ ሾሞኝ
ከመልኩ ደም ግባት.. .
ወዘናውን ጨልፎ ፥ ሰው አድርጎ ፈጥሮኝ
"አከበርሁህ" የሚል ፥ ቃሉን ቢሰጠኝም
የዱር አውሬን ያህል ..
የሚያስፈራ ግርማ ስለምን የለኝም?
እኔንጃ አላውቅም !
እውነት ንጉስ የሆንሁ ነኝ ወይ እንደ ቃሉ ?
እውነት እውነት ነው ወይ የርሱስ አባባሉ?
እንኪያስ ስለምን ነው?!
ሆዱን ጦም ሳያድር ፥ የምገዛው አዕዋፍ ፥ እውሩ አሞራ
በለምለም ተውበው ፥ አዝዕርት ተክሉ ፥ ከቆሙበት ስፍራ
እኔን እህል ናፍቆኝ ፥ ከጠኔ መጣፍ ላይ ፥ ብሶት የምቀራ?
በሉዋ መልሱ!
@getem
@getem
@getem
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።።።።
የአዕዋፍ ፣ የአዝርዕርቱ
ያውሬ ፣ የእንስሳቱ ፥ ንጉስ አ'ርጎ ሾሞኝ
ከመልኩ ደም ግባት.. .
ወዘናውን ጨልፎ ፥ ሰው አድርጎ ፈጥሮኝ
"አከበርሁህ" የሚል ፥ ቃሉን ቢሰጠኝም
የዱር አውሬን ያህል ..
የሚያስፈራ ግርማ ስለምን የለኝም?
እኔንጃ አላውቅም !
እውነት ንጉስ የሆንሁ ነኝ ወይ እንደ ቃሉ ?
እውነት እውነት ነው ወይ የርሱስ አባባሉ?
እንኪያስ ስለምን ነው?!
ሆዱን ጦም ሳያድር ፥ የምገዛው አዕዋፍ ፥ እውሩ አሞራ
በለምለም ተውበው ፥ አዝዕርት ተክሉ ፥ ከቆሙበት ስፍራ
እኔን እህል ናፍቆኝ ፥ ከጠኔ መጣፍ ላይ ፥ ብሶት የምቀራ?
በሉዋ መልሱ!
@getem
@getem
@getem