ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ዶሮው ርግብ አፈቀረ።
የተበተነውን ጥሬ
እስኪለቅሙ አብረው ቢቆሙ
ተታለለ።
ከጎኑ ስላያት እኩያው... ቢጤው መሰለችው።
ክንፏ ሲርገበገብ፣
ቅንቅኑን ሊያራግፍ ክንፉን አርገበገበ።
ስታኮበኩብ አጎበጎበ።
«መብረር» ይሉት ታምር እንዳለ መች አወቀ?
ቀና ብላ ሄደች።
አቀረቀረ።
ዶሮው ርግቧን ጠላት።
«የማይበር ክንፉን አስታወሰችው...»
ርግቤ ሙዚቃ ነበረች።
ሰማኋት ብዬ የምድር ስበት ሕግ ላይ አመጽኩ።
እስትንፋሳችን
ለቅጽበታት ቢተሳሰር ...ዜማ ቢጤዬ ነው አልኩ።
ከምቱ እኩል
ተርገብግቤ
... ተንገብግቤ
ላርግ ቅፅበት ሲቀር ...
የሰወረኝ ዜማ ወደማልከተለው ሩቅቅቅቅ ይሰወርብኛል።
ከትኩስ ፈጣን ትንፋሼ ጋር ብቻዬን እቀራለሁ።
ሙዚቃን ጠላኋት።
አብሯት የማይበር ክንፌን...
አብሯት የማይሰወር ስጋዬን
ታስታውሰኛለች።

#Rediet_Aseffa
@getem
@getem
አፈራረስ።
.
.
ሕይወት
ድለቃ
ሕይወት
ድሰቃ
ከእንግዲህ
ይብቃ።
ልብ
ከበሮ
አይደበድብም፡
እንደክራር
ክር
ቋንጃ አይረግብም፡
አየር
አይወጣም
እህል አይገባም፡
አንጀት
አይቆስልም
ሆድም አይባባም፡
እድሜ
አይነጉድም፡
ሀሳብ
አይከብድም፡
እግር
አይሄድም፡
እጅና
ተስፋ
አይወራጭም፡
ፍቅር
በወረት
ሰርክ አይቋጭም፡
ያደረጉትም
ያላረጉትም
በቃ አያስቆጭም፣
ጌትዬ
መጣ
ሞት አባ ጠቅልል፡
ይዘለኝና
ሸክ`ሜን ላቅልል።
ሕይወት
ረብሻ
ሕይወት ድለቃ፡
ለፍቅር
መርዶ
ደረት ድሰቃ፡
ለተስፋ
ቀብር
ዋንጫ ልቅለቃ፡
ደክሞኛል
ልረፍ
ከንግዲህ በቃ፡...
ጌትዬ መጣ...

#rediet_aseffa

@getem
@getem
@getem
👍1