#ዝም_አልልም
እንደ እኩዮቼ ቦርቄ ሳልጨርስ
በጀንበሯ ፍካት እሮጬ ሳልጨርስ
አባቴ የምለው ቀበቶ ሲፈታ
ስህተት የሰራሁኝ መስሎኝ የምመታ
በእግሮቼ መሀል እጆቹን ሲሰደው
ለቁንጥጫ ምስሎኝ ጥፋቴን ሳስበው
እግሮቼን ጠፍንጎ ሱሪውን ያስፈታው
የወደፊት ህልሜን በንጭጩ ያስቀረው
ወንድነቱ ነበር ከህሊናው ያጣላው ።
-------------------------------------------
ምን አጥፍቼ ይሆን ምን አርጌ አባባ
ለስሜት ያስጣለህ ያባትነት ካባ
ምኔ አማሎህ ይሆን ያስጨከነህ በኔ
ያልጠነከረ እግሬ ወይ ጨቅላው አካሌ
ለጡት ያልደረሰው ገላጣው ደረቴ
ምኔ ነው ንገረኝ አባትነትህን ያሳጣህ በሞቴ
---------------------------------------------
አረ ተወኝ አባ ይከብዳል ቅጣቱ
የሲቃ ድምፆቼ አንተን ሲማፀኑ
በርኩሰትህ ብዛት የእንባዬ ጠብታ ከአካልህ ሲያርፉ
ንገረኝ አባባ ሴሰኝነትህን ከኔ ያስበለጠ
እምነትህን ቀብሮ ክህደት ያስመረጠ
አባትነትህን ለደቂቃ ስሜት ገደል የከተተ
በፈጠርከው ገላ በአካልህ ክፋይ እውሬ ያደረገ
ሰውኛን አሽሮ ከጅብ ያዛመደ
ቀዝቃዛው ጭኖቼን ልከፍት ያስገደደ
በጭካኔ እርክሰት ከኔ ያልከሰከሰህ
ምኔ ነው አባባ እኔን ያስደፈረህ
-------------------------------------------
መከታዬ ብዬ ጀርባዬን ሲበርደው
ህግስ የታለና ለማን ከሳሀለው
ለአመት ብትታሰር ለኔ ምን ዋጋ አለው
እኔስ ምን አቅም አለኝ ምን አረጋሀለው
በእንባዬ አቤቱታ ለሱ ትቼሀለው
ለአባቴ አምላክ በሰማያት ላለው ።
#መታሰቢያነቱ አባትነት በማይገባቸው በአረመኔ ወንዶች ለተደፈሩ ልጆች ይሁንልኝ።
📝...ኪሩቤል ወንደሰን
@kirwub
@getem
@getem
@getem
እንደ እኩዮቼ ቦርቄ ሳልጨርስ
በጀንበሯ ፍካት እሮጬ ሳልጨርስ
አባቴ የምለው ቀበቶ ሲፈታ
ስህተት የሰራሁኝ መስሎኝ የምመታ
በእግሮቼ መሀል እጆቹን ሲሰደው
ለቁንጥጫ ምስሎኝ ጥፋቴን ሳስበው
እግሮቼን ጠፍንጎ ሱሪውን ያስፈታው
የወደፊት ህልሜን በንጭጩ ያስቀረው
ወንድነቱ ነበር ከህሊናው ያጣላው ።
-------------------------------------------
ምን አጥፍቼ ይሆን ምን አርጌ አባባ
ለስሜት ያስጣለህ ያባትነት ካባ
ምኔ አማሎህ ይሆን ያስጨከነህ በኔ
ያልጠነከረ እግሬ ወይ ጨቅላው አካሌ
ለጡት ያልደረሰው ገላጣው ደረቴ
ምኔ ነው ንገረኝ አባትነትህን ያሳጣህ በሞቴ
---------------------------------------------
አረ ተወኝ አባ ይከብዳል ቅጣቱ
የሲቃ ድምፆቼ አንተን ሲማፀኑ
በርኩሰትህ ብዛት የእንባዬ ጠብታ ከአካልህ ሲያርፉ
ንገረኝ አባባ ሴሰኝነትህን ከኔ ያስበለጠ
እምነትህን ቀብሮ ክህደት ያስመረጠ
አባትነትህን ለደቂቃ ስሜት ገደል የከተተ
በፈጠርከው ገላ በአካልህ ክፋይ እውሬ ያደረገ
ሰውኛን አሽሮ ከጅብ ያዛመደ
ቀዝቃዛው ጭኖቼን ልከፍት ያስገደደ
በጭካኔ እርክሰት ከኔ ያልከሰከሰህ
ምኔ ነው አባባ እኔን ያስደፈረህ
-------------------------------------------
መከታዬ ብዬ ጀርባዬን ሲበርደው
ህግስ የታለና ለማን ከሳሀለው
ለአመት ብትታሰር ለኔ ምን ዋጋ አለው
እኔስ ምን አቅም አለኝ ምን አረጋሀለው
በእንባዬ አቤቱታ ለሱ ትቼሀለው
ለአባቴ አምላክ በሰማያት ላለው ።
#መታሰቢያነቱ አባትነት በማይገባቸው በአረመኔ ወንዶች ለተደፈሩ ልጆች ይሁንልኝ።
📝...ኪሩቤል ወንደሰን
@kirwub
@getem
@getem
@getem