ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
Haileleul Aph

#ልጅነትና_እውቀት
.
ይመስለኝ ነበረ
.
.
ከእለታት አንድ ቀን
ጦርነት ሁሉ አልቆ፥ ሰላም የሚሰፍን
ይመስለኝ ነበረ
ትልልቅ ሰው ሁሉ
ሚስጥር የሚደብቅ፥ ገመና የሚሸፍን።
.
ይመስለኝ ነበረ
ቤተስኪያን ሂያጅ ሁሉ፥ እውነት የሚናገር
ሰው የመሬት ዜጋ
መሬትም የሰው ልጅ፥ ሁሉም የራስ ሃገር፡፡
.
ይመስለኝ ነበረ
የታመመ ሁሉ ፥ ታክሞ የሚድን
የተራበ ጠግቦ
የምስጋና ንፋስ፥ ምድርን የሚከድን።
.
ይመስሉኝ ነበረ
አብረው ያየኋቸው፥ ከልብ ሚዋደዱ
‘ሚዋደዱ ሁሉ
የማይለያዩ፥ የማይከዳዱ።
ሰው በሙሉ መልካም
ያጠፋ እንኳን ቢኖር፥ ወዲያው የሚቀጣ
መጥፎው ተወግዶ
ደግ የሚነግስበት፥ ዘመን የሚመጣ።
.
ይመስለኝ ነበረ
.
.
ማደግ ደስ የሚያሰኝ
ለሚራበሽ አለም፥ መድሃኒት የማስገኝ
በመኖሬ ምክንያት
የሌላውን ህይወት፥ ሳሻሽል የምገኝ፡፡
.
.
ይመስለኝ ነበረ....።
.
.
የዋህ ልጅነቴን
አደግሁና አየሁት፥ ትዝብቴ አሳቀቀኝ
ሃሳቤን ቢያውቁብኝ
መሳቂያ መሆኔን፥ ማን አስጠነቀቀኝ?
.
አደግሁና ጀመርኩ
በያደባባዩ፥ መካሰስ መወንጀል
ባከማቸሁት ላይ
ነጥቆ ማከማቸት፥ ያማኜን መከጀል።
በሰው ሰራሽ ድንበር
በሰው ሰራሽ ቀንበር፥ ቡድን እየሰራሁ
እንደ ሰኔ መሬት
እየተሸናሸንኩ፥ መባላት ከዘራሁ
ማነው ያስተማረኝ
ታቦት ሰርቆ መሸጥ፥ ክህነቴን ጥዬ
ማነው የነገረኝ
ሸንግሎ ማሳደር፥ የእግዜር ሰው ነኝ ብዬ?
የሚል ጥያቄ አለኝ
ለዚያ ልጅነቴ፥ ለዛሬው ማደጌ
ማን ያብራራልኛል
በሽታ መፍጠሬን፥ መድሃኒት ፈልጌ?
መሳሪያ ፈልስፌ
ጠብ-መንጃ መሸጤን፥ ለጦር ማስታጠቄን
ማን ይመልስልኝ
የማደግ ክፋቴን፥ የልጅነት ሃቄን?
.
አለም አኬልዳማ
በእድሜዬ እሾህ ማሳ፥ ደማምቼ ባለፍኩ
አደግሁና ገባኝ
ሌላው ምን አገባኝ.. ራሴን ካተረፍኩ?

@paappii
@getem
@getem
#ልጅነትና_እውቀት
.
ይመስለኝ ነበረ
.
.
ከእለታት አንድ ቀን
ጦርነት ሁሉ አልቆ፥ ሰላም የሚሰፍን
ይመስለኝ ነበረ
ትልልቅ ሰው ሁሉ
ሚስጥር የሚደብቅ፥ ገመና የሚሸፍን።
.
ይመስለኝ ነበረ
ቤተስኪያን ሂያጅ ሁሉ፥ እውነት የሚናገር
ሰው የመሬት ዜጋ
መሬትም የሰው ልጅ፥ ሁሉም የራስ ሃገር፡፡
.
ይመስለኝ ነበረ
የታመመ ሁሉ ፥ ታክሞ የሚድን
የተራበ ጠግቦ
የምስጋና ንፋስ፥ ምድርን የሚከድን።
.
ይመስሉኝ ነበረ
አብረው ያየኋቸው፥ ከልብ ሚዋደዱ
‘ሚዋደዱ ሁሉ
የማይለያዩ፥ የማይከዳዱ።
ሰው በሙሉ መልካም
ያጠፋ እንኳን ቢኖር፥ ወዲያው የሚቀጣ
መጥፎው ተወግዶ
ደግ የሚነግስበት፥ ዘመን የሚመጣ።
.
ይመስለኝ ነበረ
.
.
ማደግ ደስ የሚያሰኝ
ለሚራበሽ አለም፥ መድሃኒት የማስገኝ
በመኖሬ ምክንያት
የሌላውን ህይወት፥ ሳሻሽል የምገኝ፡፡
.
.
ይመስለኝ ነበረ....።
.
.
የዋህ ልጅነቴን
አደግሁና አየሁት፥ ትዝብቴ አሳቀቀኝ
ሃሳቤን ቢያውቁብኝ
መሳቂያ መሆኔን፥ ማን አስጠነቀቀኝ?
.
አደግሁና ጀመርኩ
በያደባባዩ፥ መካሰስ መወንጀል
ባከማቸሁት ላይ
ነጥቆ ማከማቸት፥ ያማኜን መከጀል።
በሰው ሰራሽ ድንበር
በሰው ሰራሽ ቀንበር፥ ቡድን እየሰራሁ
እንደ ሰኔ መሬት
እየተሸናሸንኩ፥ መባላት ከዘራሁ
ማነው ያስተማረኝ
ታቦት ሰርቆ መሸጥ፥ ክህነቴን ጥዬ
ማነው የነገረኝ
ሸንግሎ ማሳደር፥ የእግዜር ሰው ነኝ ብዬ?
የሚል ጥያቄ አለኝ
ለዚያ ልጅነቴ፥ ለዛሬው ማደጌ
ማን ያብራራልኛል
በሽታ መፍጠሬን፥ መድሃኒት ፈልጌ?
መሳሪያ ፈልስፌ
ጠብ-መንጃ መሸጤን፥ ለጦር ማስታጠቄን
ማን ይመልስልኝ
የማደግ ክፋቴን፥ የልጅነት ሃቄን?
.
አለም አኬልዳማ
በእድሜዬ እሾህ ማሳ፥ ደማምቼ ባለፍኩ
አደግሁና ገባኝ
ሌላው ምን አገባኝ.. ራሴን ካተረፍኩ?


#Haileleul_Aph
@getem
@getem
@getem
2