ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
* #በላይ_በቀለ_ወያ *

ሰው ሀገር ሆናችሁ
ሞቴን ባገሬ አርገው ፣
ምናምን ብላችሁ ፣ አታውሩልኝ ወሬ
ሬሳ ሰብሳቢ..
ጥንባንሳ አይደለችም ፣ ኢትዮጵያ ሀገሬ፡፡

ህይወታቹ እንጂ
እውቀታችሁ እንጂ ፣ የሚበጀው ላገር
ሞትማ ያው ሞት ነው!
የትም ቀባሪ አለ ፣ የትም አለ አፈር፡፡

@getem
@getem
@getem
#በላይ_በቀለ_ወያ
.
.
ተይ ይነጋል ስልሽ ፣ ብለሽኝ አይነጋም
ጥለሽኝ ስትሔጂ ፣ ይህ ቀልቤ ባይረጋም
ተለየችኝ ብዬ ፣ ያንች አይነት ልጋጋም
ለሰው አላወጋም።
።።
ብቻ ግን አንዳንዴ ፣ ደግም ይሁን መጥፎ
ትዝታ ናፍቆትሽ ፣ ፊቴ ተነጥፎ
አንቺ ከሔድሽ ኋላ
የመጣውን ነገር ፣ ሳስበው ለራሴ
ሺ ሟች ላለማየት
ብቻዬን ስቃለሁ ፣ በሺህ ገዳይ ጥርሴ።
።።።
አንቺ ከሔድሽ ኋላ
ከንቲባው በሙሉ ፣ ተሸክሞ ኩንታል
ለሚስኪኖች ሲያድል
የሚያሳይ ፎቶ ፣ ተግቶ ይፖስታል
ዘይት ሳኒታይዘር ፣ በየሱቁ ያደርሳል
ደሃ እንባ ቅርቡ አይደል?!
ሲከፋው ፣ ሲደሰት ፣ ለምዶበት ያለቅሳል
።።።
ፎቶ አይተው በሚያምኑ
የሚመሠገኑ
ከንቱና ከንቲባ
በፎቶ ምስኪን ቤት ፣ ኩንታል እያስገባ
የደሃ ቤቶችን ፣ በተግባር ያፈርሳል
ደሃ እንባ ቅርቡ አይደል?
በአንድ ከንቲባ ፣ ሁለቴ ያለቅሳል
አንድዜ ተከፍቶ ፣ አንድም ተደስቶ
በአካል የሚገፋን ፣ ያቅፈናል ለፎቶ።
።።።።
አንቺ ከሔድሽ ኋላ
አንበሳ ነኝ ባዩ ፣ በፒኮክ ያለቅሳል
ቤት ሁኑ በሚለን ፣ ቤታችን ይፈርሳል
ገዳይ ቁጭ ብሎ
ተበዳይ ጠያቂ ፣ ታስሮ ይከሰሳል
ብቻ ምን አለፋሽ
አንቺ ከሔድሽ ኋላ ፣ ሁሉ ሆኗል ከንቱ
እኔን ሚደንቀኝ ግን
የሚ"በር" ፒኮክ
የማይንቀሳቀስ ፣ "በር" ሆኖ መቅረቱ

@getem
@getem
@getem
1👍1