(የሞገሴ ልጅ)
ከእኔ ካልመጣ
ሂጂልኝ ማለትን - አፌ ካልተማረ፣
ካልሄድኩ ካለ ልብሽ፣
ብከለክለውስ - መቼ ትቶት ቀረ?
ኁሌ አትሂጂ ባይ
ኁሌ ልሂድ በሚል ረባሽ ከተገፋ፣
ሰይጣንን ያስቀናል፣
እንኳንስ በሌላው በራሱ ሲከፋ!
By @eyadermoges
@getem
@getem
@getem
ከእኔ ካልመጣ
ሂጂልኝ ማለትን - አፌ ካልተማረ፣
ካልሄድኩ ካለ ልብሽ፣
ብከለክለውስ - መቼ ትቶት ቀረ?
ኁሌ አትሂጂ ባይ
ኁሌ ልሂድ በሚል ረባሽ ከተገፋ፣
ሰይጣንን ያስቀናል፣
እንኳንስ በሌላው በራሱ ሲከፋ!
By @eyadermoges
@getem
@getem
@getem
❤19🔥5👍1🤩1
እጠራጠራለሁ
ተቃርበሽ ተቃርበሽ ስጠፊ ስላየሁ
ደግሞም እቀናለሁ
እንደኔ ምትወጂው ይኖር ወይ እላለሁ
አልመስል አለኝ እውነት-የምትስሚኝ የምታቅፊኝ
ተቃርበሽ ልጠፊኝ?
ፍቅር ጣዕም አስለምደሽ ከአይን ልደበዝሽ
ለምንድነው የምትስሚኝ?
ለምንድነው የምስምሽ?
እጠራጠራለሁ
ስትርቂኝ ስላየሁ
ስትስሚኝ ስላየሁ
ካንቺ ፍቅር ውጥን ብርቅም ብሸሽም
እወድሻለሁኝ ግን ልቤ አያምንሽም
አፈቅርሻለሁኝ ግን ልቤ አያምንሽም።
ብቻ
አለሁ እንዳለነው
ስትቀርቢኝ እያየው
ስትርቂኝ እያየው
አለሁኝ እንዳለሁ
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
ተቃርበሽ ተቃርበሽ ስጠፊ ስላየሁ
ደግሞም እቀናለሁ
እንደኔ ምትወጂው ይኖር ወይ እላለሁ
አልመስል አለኝ እውነት-የምትስሚኝ የምታቅፊኝ
ተቃርበሽ ልጠፊኝ?
ፍቅር ጣዕም አስለምደሽ ከአይን ልደበዝሽ
ለምንድነው የምትስሚኝ?
ለምንድነው የምስምሽ?
እጠራጠራለሁ
ስትርቂኝ ስላየሁ
ስትስሚኝ ስላየሁ
ካንቺ ፍቅር ውጥን ብርቅም ብሸሽም
እወድሻለሁኝ ግን ልቤ አያምንሽም
አፈቅርሻለሁኝ ግን ልቤ አያምንሽም።
ብቻ
አለሁ እንዳለነው
ስትቀርቢኝ እያየው
ስትርቂኝ እያየው
አለሁኝ እንዳለሁ
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
👍13❤8😢2
ወንድ አይደለሁ?
ታውቂም አይደል?
ወንድነቱ የሰጠኝን - ክብር ኩራት እንዴት ልጣል?
ላንድ ላንቺ ተንበርክኬ፣
ላንድ ላንቺ በመሸነፍ፣
ጠመንጃዬን ዝቅ አድርጌ ባንቺ ፍቅር - ራሴን ስፅፍ፤
ወንድነቴ ጠፍቶ አይደለም - ላንቺ ሲሆን ዝም ያለው፣
ከናት እቅፍ ሙቀት በላይ - ያንቺ መሳም ቢደላው ነው።
ግን ፀባይሽ ተለዋውጦ - እሹሩሩ እስካልዳኘው፣
ትንሽ ግዜ ቢቆይ እንጂ - ወንድነቴን እንዳሞኘው፤
ጠብ እርግፍ እያልኩልሽ ከቆጠርሽው እንደምንም፣
ረስተሽ እንጂ የማረክሽው - ሓይል ያጣ ልብ አልነበረም።
ግን ያው ተውኩት!
ዳግም ራራሁ!
አንከባክበኝ ስትይ እማ - መቼ ድሮስ አመነታሁ!
ነይ ተጠጊ ወደጎኔ - ፍርጥም ክንዴን ተንተራሽው፣
አትተወኝ ባልተለየው ሄዳለሁ ቃል - እንደልብሽ ግፊው እሺው፤
ብስጭቴን - አባሪልኝ - በከንፈርሽ ውድ መና፣
ከእጆችሽ መድሓኒቴን - አቀብይኝ ዳብሽኝ እና፤
እስትንፋስሽ እንፋሎቱ - ብርዴን ይዞት ገደል ይግባ፣
ቀለበቴን አጥልቄልሽ ዛሬም ዳግም እንጋባ!
By @eyadermoges
@getem
@getem
@getem
ታውቂም አይደል?
ወንድነቱ የሰጠኝን - ክብር ኩራት እንዴት ልጣል?
ላንድ ላንቺ ተንበርክኬ፣
ላንድ ላንቺ በመሸነፍ፣
ጠመንጃዬን ዝቅ አድርጌ ባንቺ ፍቅር - ራሴን ስፅፍ፤
ወንድነቴ ጠፍቶ አይደለም - ላንቺ ሲሆን ዝም ያለው፣
ከናት እቅፍ ሙቀት በላይ - ያንቺ መሳም ቢደላው ነው።
ግን ፀባይሽ ተለዋውጦ - እሹሩሩ እስካልዳኘው፣
ትንሽ ግዜ ቢቆይ እንጂ - ወንድነቴን እንዳሞኘው፤
ጠብ እርግፍ እያልኩልሽ ከቆጠርሽው እንደምንም፣
ረስተሽ እንጂ የማረክሽው - ሓይል ያጣ ልብ አልነበረም።
ግን ያው ተውኩት!
ዳግም ራራሁ!
አንከባክበኝ ስትይ እማ - መቼ ድሮስ አመነታሁ!
ነይ ተጠጊ ወደጎኔ - ፍርጥም ክንዴን ተንተራሽው፣
አትተወኝ ባልተለየው ሄዳለሁ ቃል - እንደልብሽ ግፊው እሺው፤
ብስጭቴን - አባሪልኝ - በከንፈርሽ ውድ መና፣
ከእጆችሽ መድሓኒቴን - አቀብይኝ ዳብሽኝ እና፤
እስትንፋስሽ እንፋሎቱ - ብርዴን ይዞት ገደል ይግባ፣
ቀለበቴን አጥልቄልሽ ዛሬም ዳግም እንጋባ!
By @eyadermoges
@getem
@getem
@getem
❤31👎3🔥3🤩1
ፍትህ ለቃላት
ቤት ለመድፋት በሚል ሰበብ አሳብቤ
እንቅልፌን ሰውቼ ቃላትን ሰብስቤ
ከቶ አልማግጥም ቃል በቃል ደርቤ፡፡
ማንስ ሆኜና ነው ቃላትን ምመርጠው
አንደኛው ከሌላው የማበላልጠው?
ላንዲት ተራ ግጥም
ወይ ሊጥም ወይ ላይጥም
የአንዱን ክብር ጥዬ ሌላ ቃል አልመርጥም!
ቃል ሁሉ እኩል ነው መነሻው ከፊደል፤
አይከብድም ወይ ታዳ ሺህ ቃላት መበደል፡፡
ያኛው አይመጥንም ቤት ያፈርሳል ደርሶ
እንዴት ሰው ፊት ይቀርባል የግጥም ህግ ጥሶ
በሚል አጉል ልማድ ብዬ ቤት ለመድፋት
በቃላት ዘር ላይ አልፈፅምም ጥፋት፡፡
By @Abuugida
@getem
@getem
@getem
ቤት ለመድፋት በሚል ሰበብ አሳብቤ
እንቅልፌን ሰውቼ ቃላትን ሰብስቤ
ከቶ አልማግጥም ቃል በቃል ደርቤ፡፡
ማንስ ሆኜና ነው ቃላትን ምመርጠው
አንደኛው ከሌላው የማበላልጠው?
ላንዲት ተራ ግጥም
ወይ ሊጥም ወይ ላይጥም
የአንዱን ክብር ጥዬ ሌላ ቃል አልመርጥም!
ቃል ሁሉ እኩል ነው መነሻው ከፊደል፤
አይከብድም ወይ ታዳ ሺህ ቃላት መበደል፡፡
ያኛው አይመጥንም ቤት ያፈርሳል ደርሶ
እንዴት ሰው ፊት ይቀርባል የግጥም ህግ ጥሶ
በሚል አጉል ልማድ ብዬ ቤት ለመድፋት
በቃላት ዘር ላይ አልፈፅምም ጥፋት፡፡
By @Abuugida
@getem
@getem
@getem
❤19🔥4👍3👎2😁2🤩2🎉1