ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ጥላና የሰው ልጅ ይመሳሰላሉ
አለውልህ ብለው ሲመሽ ይጠፋሉ
ጨለማ ሲወርስህ ብርሀንህ ሲጠፋ
ቅን እኮ ነው ያልከው ታያለህ ሲ'ከፋ

[ ጥሩቤል ]
@ebuh_bhr

@getem
@getem
@getem
76👍37🔥10👎1
አገኘሁ ብሎ ቀልቡ 'ማይጠፋ
አጣሁኝ ብሎ የማይከፋ
እንድሆን አርጎ ጌትዬው ካጨኝ
ብኖር ሸጋ ነው ፥ ብሞት አይቆጨኝ ።

By Hab HD

@getem
@getem
@paappii
69👍21🔥8🤩1
የሰዉ ልጅ የሰራዉ
አብረቅራቂ መንገድ
ሳይታክት ይወስዳል
መዉሰዱ ሳይበቃዉ
አዙሮ አዙሮ....
እዛዉ ይመልሳል
እግዜር የፈጠረዉ
የሰዎች ዘመን ግን
አንድቀን ያበቃል
ሳይታሰብ
ያ  ል  ቃ  ል...........

By ዔደን ታደሰ

@ediwub
@getem
@getem
31👍25
አንደበት

ከእሩምታው በላይ
እንደሀሳብ አታላይ
ከድርብ ገለባ....
በስማ በለው ላይ
ሰሚው ጆሮ ሊሰጥ
አክብሮ ቢገኝም...
በሀፍረት ባህር ውስጥ
ሰጥሞ ቢኳትንም....
ተናግሮ አናጋሪ
የዱር አጋፋሪ.....
ስስ ልቡን ለሰጠው
ጊዜ ቢታትርም
ለማገዶው እንጂ
ለቀን ለሌሊቱ...
አይቆረጥለትም።

          by ኢያሱ ከበደ
                ሚያዚያ 20 2017 ዓ.ም

@getem
@getem
@getem
👍347👎1
( ለሆነ ሰው )
=============

ሁላችንም ....
ለሆነ ሰው መፈወሻ
ለሆነ ሰው ድብቅ ህመም
ለሆነ ሰው ጠባብ መንገድ
ለሆነ ሰው ግዙፍ ዓለም

የአንድ ስፌት ሁለት ህብር
የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጾች

ለሆነ ሰው ክፉ መርገም
ለሆነ ሰው በረከቶች
ለሆነ ሰው መሸሸጊያ
ለሆነ ሰው ራቁቶች

ለፍርድ ቀን የማንመች
ግማሽ ጥቁር ግማሽ ነጮች !!!

By @Kiyorna

@getem
@getem
@paappii
107👍34🔥15🤩4
ሀቁን ሁሉም ሰው፡
ቢሸፍንም...
ሰው ካለም ክፋት ፡ እንዳይማር
በሴትነት ዘንድ የሚፈፀም
ትልቅ ወንጀል ነው፡
አለማማር!።
እንደ አምላክ በስም ባይመለክ
ባይሰዋለት ዘቢብ ፣ እጣን
ማንም ሸፋፍኖ የማይክደው
ውበት በሰው ላይ
አለው ስልጣን።
መልኳ ያልገነነ ምትደንቅ ሴት
ሀሳቧ አለሙን ቢያገናኝም
በቆንጆ ልጅ ሳቅ ይሸፈናል
ስባሪ ትኩረት ፡ አያገኝም፤
ምንም በህጉ ባይፀድቅ እንኳ
ቃል በቃል ሰፍሮ በትዕማር
ወደው እንዳረጉት የራስ ምርጫ
ትልቅ ወንጀል ነው ፡ አለማማር!።

by @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
👍2318😱6🔥3
ግዴታ ሆኖ — ብለ፟ይሽ
ባላይሽ — ዳግም  ደግሜ....
የማይሞላን ባዶ ጊዜ....
(የቀረኝን ግንጥል ዕድሜ....)
በነፍስሽ ጠረን ትዝታ.....
በመንፈስሽ እኖራለሁ ፤
(አልጥልሽም አራግፌ..)
ተሸክሜሽ እዞራለሁ  ።

ባ`ካሌ — በስሱ ገላ...
በፊቴ — ደግሞ በኋላ....
በጣቴ — ጫፎች አሻራ....
በራሴ — በፀጉሬ ስፍራ ....
(ይዤሽ ነው — ዘመን ምሻገር !)
በልቤ  በደሜ — ማገር ፥
በሆንኩት — በቀረኝ ነገር ።

From: Charles Bokouski : “ Living on luck”¹
__
¹ =.......
ⁱᶠ ⁱ ⁿᵉᵛᵉʳ ˢᵉᵉ ʸᵒᵘ ᵃᵍᵃⁱⁿ
ⁱ ʷⁱˡˡ ᵃˡʷᵃʸˢ ᶜᵃʳʳʸ ʸᵒᵘ
ⁱⁿˢⁱᵈᵉ, ᵒᵘᵗ ˢⁱᵈᵉ
ᵒⁿ ᵐʸ ᶠⁱⁿᵍᵉʳ ᵗⁱᵖˢ
ᵃⁿᵈ ᵃᵗ ᵇʳᵃⁱⁿ ᵉᵈᵉᵍᵉˢ
ᵃⁿᵈ ⁱⁿ ᶜᵉⁿᵗᵉʳˢ
ᶜᵉⁿᵗᵉʳˢ
ᵒᶠ ʷʰᵃᵗ ⁱ ᵃᵐ ᵒᶠ
ʷʰᵃᵗ ʳᵉᵐᵃⁱⁿˢ

By @Bekalushumye

@getem
@getem
@getem
👍3625🔥6🤩2😱1
ሳትፈልጊ መስጠት ~ ፈልጎ እምቢ መባል አልለመደብሽም ፤

አጣሁ አልሸኝ እንጂ ~ አጣሁ የምትይው አልጎደለብሽም ፤

ትፈሪያለሽ እንጂ ~ ይታመምልሻል ያሳመመሽ ህመም ፤

የበደለሽ ሁሉ ~ ድሮ እንዳመለከሽ ፈፅሞ አይረሳውም ፤

እና ለኔ መውደድ ..? እና እምባ ከኔ ፊት..? ሀዘን ያጣላሻል ተይው ከመለኮት ... !

ሳትሞት አትተርፊም ግን ደግሞ ተርፈሻል ... እንኳን የኔ አይነት ሰው ሞት ይራራልሻል።

@getem
@getem
@paappii

By Natnael mulu
25👍17🔥5🎉3
ካለብኝ ጸባይ

የግንባር ስጋ ነው እንደሚሉት አይነት ሆኖ ባህሪዬ
ነገሬ ፊት ለፊት ቀጥታ መጥራት ነው ሰውን ተፈጥሮዬ
አህያን አህያ ቅልን ቅል ብዬ😊😊

አንበሳን አንበሳ ቀፎውንም ቀፎ ብዬ የምጠራ ሁሉን በቀጥታ
ምን ይሉኛል ብዬ ሳይኖረኝ ይሉኝታ🤷‍♀🤷‍♀
  ተፈጥሮዬ ነዋ

"ጦቢያ"እንደጻፈችው

@getem
@getem
@getem
👍263👎3
ማር ወለላ ከከንፈሯ
ውበት አላት ከምግባሯ
ባነጋገር ምትቆርጥ ጥም
ስትቀመስ የምትጥም
ቅመሜ ናት ለመኖሬ
የወስጥ ቁልፍ የሚስጥሬ
ተፈጥሯዊ መልከ ሸጋ
ቀን ሲጨልም የምትነጋ
ባህሪዋ ወይናደጋ
የተሰጣት ፍቅረ ፀጋ
ከሷ
      ጋ።

ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
🔥25👍1211
መተያየት በዝምታ
መተፋፈር ደግሞ ላፍታ
መፈራራት ለማናገር
ጉድ ሲቀለብ በጉድ ሀገር
መተያየት ዝም ብቻ
ፈገግ ማለት በፍራቻ
ፍርሃት ፍርሃት ለፍቅር ቃል
አላማውራት ያራርቃል


ዮኒ
     ኣትን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
👍6010🔥9🎉4🤩2
ሰው ነበርኩኝ

ተወለድኩኝ
(ከመሀፀን ወደኩኝ )
አለቀስኩኝ
(ሀዘን ገባኝ ሰው ፈለኩኝ )
አፌን ከፈትኩ
(የሆድ ጥልቀት አወኩ )
በቃኝ አልኩ
( በእድሜ ሰከንኩ )
ጠረን ለየሁ
( ምቾት አየሁ )
ቋንቋ ለመድኩ
(በቆፈሩት ወረድኩ )
መልክ ለየሁ
(እኔን አወኩ  አዲስ ካየሁ )

አንተ ግን ለቤቴ
( እንግዳ ላጥንቴ )
ሆነህ የሩቅ ሩቅ
(እንደ ዘመድ እንቅ )
ለምን አደረኩህ ....?

ሴት ነበርኩኝ

የተጣፈ እጣዬ
( ግልጥ ጎባጣዬ )
ሊያውም በእኛ መንደር
( እንቢ ነው መግደርደር )
እያለ ከሚረግጥ
( በዘመን ረመጥ )
በዘር ማን ዘር እሳት
(የምትቃጠል ሴት) !!!

ጨዋ እኮ ነበርኩኝ

አፈነገጥኩልህ
( እራሴን ተውኩልህ )
ወፍ ሆንኩልህ ጫጩት
(ሳይበር እንደ ቀጩት )
ረግጬ ህጌን
(ገላምጬ ወጌን)

ክር እኮ ነበረኝ

የገባሁት ኪዳን
( የመነንኩለት ሀቅ በነፃ ለመዳን )
የወሰዳት ነፍሴን
( ያሳረፈኝ ምናብ ቆርጦ ግሳንግሴን )

ጌታ እኮ ነበረኝ

የልቤ ጉልበቱ
(ሰርክ መስዋእቱ )
የምገብርለት
(ያደረገኝ ዐለት )

ብዙ ነኝ 

የማላውቃት እኔ
( ተለየች ከጎኔ )
ወጣች አፈትልካ
( እኔን ላንተ ልካ )

እንደ ሰው ....
(ሞትን እንድቀምሰው)
እንደ ሴት
( እንዳምጥ  በምሬት )
እንደ ጨዋ
( እንድፈተን እንድሰዋ )
እንደ አማኝ
(እንድቀበል ሳይቀማኝ )
እንደ ድኩም
( እንዲያነቃኝ ህማም ኩርኩም )
እንደ ብዙ
(አንድ እንድሆን ጠፎ ጓዙ )
ህግ አዝዬ
(ትምክት ልቤን እንዳይንጠኝ )
ተኝቼ እንድነቃ
(አንተን መርጦ ሰጠኝ)

(በእምነት )

@getem
@getem
@getem
42👍34🔥5
ይህ ቀዥቃዣ ዝናብ ገላሽን ይንካና
ወዮለት ሰማዩ
ወዮለት ደመና ።

ወፍ አይዘምርልሽ
ዛፍ አያስጠልልሽ
በቃ እኔ አለሁልሽ ።

ደግሞ ይሄን እወቂ
ሆዴ እንደሚበላኝ ካለ እኔ ስትስቂ
እንቅልፍ እንደማጣ
በፀሐይ ስትፈኪ
ምራቄ እንደሚመር
በእግዜር ስትመኪ ።
እኔ ነኝ ጠባቂሽ
እኔ ነኝ ደስታሽ
እኔ ነኝ ፈገግታሽ
ሁሉንም የምሆን
እግዜር አላህ ሰማይ
ንፋስ ውሃ ድንጋይ
ያንቺ ብቻ አገልጋይ
ያንቺ ብቻ ታጋይ ።

ክነፍ በዪኝ ልክነፍ
እረፍ በዪኝ ልረፍ
ብቻ ደስታሽ ሁሉ በእኔ በኩል ይለፍ ።

By Hab Hd

@getem
@getem
@paappii
64👍28👎19🔥9🤩9😁4🎉2
( የድሮ ባሏ )
==========

እባክህ አምላኬ ተሰምቶ የማያውቅ
ግለጥልኝ ቃላት
የቀደመ ባሏ ደራሲ ነው መሰል
የለም እኮ ያላላት  ....

እርሱ አሐዱ ብሎ
በሳመው ከንፈር ላይ እኔ እየደገምኳት
ቃላት አሽሞንሙኖ
የነገራትን ፍቅር እኔ እያስታወስኳት
መሰረት በጣለው
ስውር ርስቱ ላይ ሠርክ እየደከምኩኝ
ልቧ ላይ ምንኖረው
እርሱ እየደመቀ እኔ እየፈዘዝኩኝ !!

By @Kiyorna

@getem
@getem
@paappii
😁6936👍25😢11🔥1
ብታውቂ!
***
ስትስቂ!
ጠፈርን እንደምታደምቂ
መንፈስን ካዚም እስራት
እንደምታላቅቂ
ብታውቂ!
ስትስሚ!
አጥንት እንደምታለመልሚ
ታማሚ ልብ እንደምታክሚ
ብታውቂ
****
ስታወሪ!
ዱዳ እንደምታናግሪ
መነኩሴውን ከሱባዔ
ፈላስፋውን ከጉባዔ
እንደምትጠሪ
ብታውቂ !
**"
እንኳንስ በኔ ልትስቂ
ከራስሽ ጋር ፍቅር ይዞሽ
አይሽ ነበር ስትማቅቂ!!!

By በውቀቱ ስዩም

@getem
@getem
@paappii
93👍30🔥8🤩4👎1
ቁራኛ
ዘመን ያላዳነኝ
ያልፈታኝ ርቀት
ተአምር ያላነጻኝ
ያልፈወሰኝ ጥምቀት
ከናፍቆት ሚነጥል
የታጣልኝ ዳኛ
እድሜ ይፍታህ ያሉት
የፍቅር ምርኮኛ
ሆንኩልሽ ቁራኛ።
           

By @poetkidus

@getem
@getem
@paappii
37👍19😁5👎2🔥2
ዘንባባን አስቀምጦ ከመናፍቅ
ጉዞ ዘላለም መበጠር
ፍቅር ሳያውቅ ኖሮ የካደ
አንደበት ከህልሙ መስፈንጠር
ሲቃዡ ነው ማደር
ስርን ነቅሎ መኖር
ስር ሰዶ መመንጠር
የፍቅር እናት ክዶ በውሸት
አብነት ዘላለም ማመስጠር

  by @ygolaw16

@getem
@getem
@getem
👍3713😁7👎6🔥1🎉1
¯
..‎ተስማምቶኛል  ፀሀይነቷ
‎መጥፋትን አልሻም ከፊትለፊቷ
‎ ያለርህራሄ  ብትወርድም በላዬ
‎ንዳዷ ጥሞታል ለውርጫም ገላዬ

‎ልዩ አረገችኝ
‎ቀየረች ፍጥረቴን ፣
‎ከጥላ መሸሽ...
‎ከጥላ መጠለል አድርጋው ህይወቴን።


by @yoseph_Gezahegn

@getem
@getem
@paappii
24👍8🤩2🔥1
ሁሉንም ነበረች
አለሌም ጭምትም
እሬትም ወተትም
እሾህም በለስም
በራድም ትኩስም
አሳቢም
ተግባቢም
ሳቂታም ፡ አልቃሻም
አሁን ምንም ነገር
ለመሆን አትሻም።

ኖራለች ከልቧ
ስታልም ስትነካ
ስትጨልም ስትፈካ
ሲቆላት
ሲደላት
ሲከፋት ሲመቻት፥
ለምን እንደሆን እንጃ
ሰው መሆን ሰለቻት!።

© @mikiyas_feyisa

@getem
@getem
@paappii
42👍25😢17🔥6😱1
(የአብስራ ሳሙኤል)

1....
ተይው
መች ተናግሮ ያቃል
የልቡን
ሀሳቡን
ወንድ አይደለ
እያነባ ይስቃል
ደና ነኝ እያለ
አለ
መኖር ካሉት
በእግዜር ምስጋና ቢኩሉት
በፈገግታ ቢቀበር እንባ
ወንድ አይደለ
ይመስገነው ብሎ ገባ
በትጨልምም
በትዘምም
ዙፋኑ ናት
ጎጆው ..... ማጀቱ
ቤቱ
የጻፈበት ገድል
የኑሮ ድል
የወዝ ዋጋ የላብ ፍሬ
ደና ነኝ ለዛሬ
2....
ተይው
ወንድ አይደለ
መች ደህና ሆኖ ያቃል
ደህና ነኝ እያለ
በገረባው
በሲጃራው
በእጣን ጢሱ
የተረሱ
መአት ብሶት
የጭስ ለቅሶ
አይን ያሟሿል
ሌላን ደርሶ
ሆድ አስብሶ
ግን ግድ ነው
ዛሬ የዱአ ከተገኘ
ይመስገን ነው
ደህና ነን ነው
3....
ተይው
ወንድ አይደለ
ባሬላ ጭኖ
ኩንታል ተጭኖ
መሪ ጨብጦ
ከብቶች እረግጦ
ባመጣት ሀሴት
ላፈቀራት ሴት
የ አበባ ጉንጉን
የወግ የወጉን
የወርቅ ሀብል
የባዕድ መብል
በርገር
ቢዛ
ማክያቶ
ተገባብዞ
ተጎንጭቶ
ሩም ይዞ
ባናት ባናት መዳራት
ፍቅር መስራት
ከሰመረ ገላዋን
ካልሆነም ጸጸት ታቅፎ
ትዝታ በውሀ አራግፎ
ደህና ነኝ ነው
ወንድ አይደለ
የልቡን ጠባሳ የሚያወራ ማን ነው
4....
ተይው
አትጠይቂው
እንዴት ዋልክ እያልሽ ?
ላትጸድቂ በነፍሱ
ደህና ባይሆን እንኳ
ደህና ነኝ ብቻ ነው
የወንድ ልጅ መልሱ!

By @mad12titan

@getem
@getem
@getem
41👍20🔥7