ግጥም ብቻ 📘
66.5K subscribers
1.54K photos
31 videos
61 files
175 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
አንዱ ለአገሩ ፤
አንዱ ለ'ርስቱ ፤

አንዱ ለልጁ ፤
አንዱ ለሚስቱ ፤

ጥይት ወልውሎ ፤ ጎራዴ ስሎ ፤
በዱር በገደል ይከታከታል ፤

ሲሻው ይገድላል ፤ ሲሻው ይሞታል ።

እኔ ግን ወዲህ . . .

ወይ አገር የለኝ ፤
ወይ ርስት የለኝ ፤
ወይ ልጅ አልወለድኩ ፤ ሚስት አላደለኝ ፤

ጎራዴ ሳልስል ፤ ጥይት ሳልገዛ ፤ በተኛሁበት ሀሳብ ገደለኝ ።

By Tewodros kassa

@getem
@getem
@paappii
👍6152😁31🔥6😱3😢1🎉1
ስለ አይኑ ብዛት
ስለ ፈርጣማ እግሮቹ፣
የእሱን ክፋት ሀያልነት
ስለ ትላልቅ እጆቹ፤

በሚል ተረት ተራቶች
እያደግን ስለመጣን፣
በህይወት መስመር ጎዳና
የፍቅርን ጣእም አጣን።

@getem
@getem
@paappii
42👍11🔥7😁5😢3
መስከረም
------------------------

አበቦች ለምልመው
ፀሀይ ሳያት ደምቃ፣
በፍንጣቂዋ
አደይ አበባ ፀድቃ፤

በየቦታዉ ደስታ
በየቦታው ጥንዶች፣
ባጠገቤ ሲያልፉ
ቆነጃጅት ሴቶች፤

አሻግሬ በሀሳብ
እያየዉ ስገረም፣
ትዝ ትይኛለሽ
ሲመጣ መስከረም።

@getem
@getem
@paappii
67👍6😢5🤩5🔥3😁2
ሚስጥረኛ ብዬ
ሚስጥሬን ብነግርሽ፣

ሚስጥሩ ነው ብለሽ
በሚስጥር ተናገርሽ፤

ያ ሚስጥር በሚስጥር
ሲዞር ሲዞር ውሎ፣

በሚስጥር ነገሩኝ
ሚስጥር ነው ተብሎ።

@getem
@getem
@paappii
😁14063👍13🔥8👎3
የልብ ልሳኑ ስሜትና ቅፅበት
ማሰብ፣ማመዛዘን የአይምሮ አንደበት

(ሆነና ነገሩ)

ሲሰናዳ አፍቃሪ
ፍቅር ባቢሎን ላይ አርማውን ሊሰቅል

ጊዜ አምላክ ሲፈርድ
ልብና አይምሮ ቋንቋቸው ለየቅል

By @Absari_seven

@getem
@getem
37🔥6👍5
( እወቅ ... )
=========

የትላንትህ ሞገስ
ከመንደር ከቀዬው አዛውንት ሲጠፉ
እወቅ ታሪኮችህ በሀሩር ጠውልገው
እንደረጋገፉ ...

ነገን የሚያበሩ
ሕጻናት ረብሻ ሲናፈቅ በሀገሩ
እወቅ ተስፋዎችህ ያለ አቅም ተጭነው
እንደተሰበሩ ...

እናማ አሁንህ
ቢተልቅ ቢገዝፍ በጊዜ ሲተለም
መቼም አትኮፈስ
ከትላንት ያልመጣ ወደ ነገ ማይሄድ
ብርቱ ' ዛሬ ' የለም !!!

By @Kiyorna

@getem
@getem
@getem
36👍27🤩4
እላለሁ ተከዳው እላለሁ ተካድኩኝ
እላለሁ ተሰበርኩ እላለሁ ወደኩኝ
እዘረዝራለሁ ሆነብኝ ያልኩትን
ረሳሁት መሰል አንተን ያረኩትን

[ ጥሩቤል ]
@ebuhbhr

@getem
@getem
@getem
68🔥18👍4🎉2
ላንቺ ብፅፍ ግጥም
ቆረጥኩኝ የሴት ጥም
እንደው ባየሺልኝ
1 አንቺ ስትሄጂ ናፍቀሺኛል ብልሽ
በስንኜ በኩል
የእንስት ጋጋታ ህይወቴን ሞላልሽ
የምን በትዝታ ሰክሮ መንገዳገድ
ሀሳብ ውሎ ይግባ በብዕሬ መንገድ

(ይህንን አትርሺ)

ሰው በቃል ይረሳል
ሰው በቃል ይፈርሳል ሰው በቃል ይሰራል
ባለቀሰበትም ድንኳን ይሞሸራል

By @Absari_seven

@getem
@getem
61🔥12👍5😱2
የራበህም ብላ የጠማህም ጠጣ ፣
       ከዚህ የተሻለ ምንም ቀን አይመጣ ፤
       ላገኝ ነው በማለት ሞትኩኝ በሰቀቀን ፣
       ሔዶ ሔዶ አለቀ የምጠብቀው ቀን ፤

     በእውቀቱ  ስዩም

@getem
@getem
@paappii
65👍21😢2
በቀል የእግዚአብሔር ነው ብለን ብንተዋቹ
ትሳፈጡን ጀመር ሞኝነት መስሏቹ
አይ አለማወቅ
አይ አለመረዳት
አልገባቹም መሰል ተንቆ መረሳት


[ ጥሩቤል ]
@ebuhbhr

@getem
@getem
@getem
53👍12😁5🔥4😱2
ወደግራ ወድቆ
ፍቅራችን ዳመራው
የትዝታሽ ጭሱን  ናፍቆት ሰማይ ጠራው

እሄዳለሁ ብዬ ሶዶ ወይ ጉራጌ
አንቺ የሌለሽበት
መስቀል እንዴት ላክብር እንደምን አድርጌ


By @Absari_seven

@getem
@getem
47😁14👎2
ወራቱ ቀኑ ጠዋቱ ምሽቱ ፤
እንደከርሞው ነው እንደትናንቱ ፤

ጣዕሙም ጠረኑም አልተቀየረም ፤
ለእኔ አዲስ ዓመት አዲስ አይደለም ፤

ያው ነው አበባው ያው ነው ዘፈኑ
ያው ነው ደመራው ያው ነው እጣኑ ፤

አልተቀየረም እጣና ዕድሌ
አልዳነም ጎኔ አልሻረም ቁስሌ ፤

ዛሬም እንዳምናው . . .

ጭጋግ አጥልቷል ፍዝ ነው ቀኔ ፤
በአበባ ብቻ የሚሻር ዘመን አላውቅም እኔ።

By Tewodros kassa

@getem
@getem
@paappii
44🔥11😢8😱5👍1
ቢታነፅ ቢወቀር!
(በእውቀቱ ስዩም)

እኔም አንድ ሰሞን
ልክ እንደ ሰለሞን
"ሁሉም ከንቱ ከንቱ ንፋስን መከተል
ላይጥሉ መታገል: ላይከብሩ መባተል"
እያልሁ አጨልሜ
በራሴ ለግሜ: እፈላሰፍ ነበር!

ከዚያ አንቺን አገኘሁ
በጓሮ በር በኩል: ሰለሞኔን ሸኘሁ
መፈጠሬን ወደድሁ
ንፋስ አሳድጄ እንደ ቆቅ አጠመድሁ
ከፀሀይዋ በታች: ግልገል ፀሀይ ፈጠርሁ
ለኦናው አምፖሌ: ብርሀን አበደርሁ

ማቅ የነበረው ጨርቅ: ሸማ ሆኖ ቆየኝ
"ከንቱ የነበረው: "አንቱ" ሆኖ ታየኝ!

ለካስ...

ጠቢብ ቢያስተምረው
መከራ ቢመክረው
አካሉና ልቡ: ቢታነፅ ቢወቀር
ሰው አቅሙን አያውቅም: ካልወደደ በቀር!

@getem
@getem
@paappii
64🔥20👍6🎉1
በህይወት መንገድ ላይ
በኑሮ ትሩፋት
ማስተዋል ከሌለ
በጥልቀት በስፋት
በእብዶች መንደር ውስጥ
ጤነኞች ከሌሉ
ጤነኞች ለእብዶች
እብዶች ይሆናሉ።

@getem
@getem
@paappii
71👍9🔥7🤩3
‎የሴትነት እጣ ክፍልሽ
‎ ምን ቢደብቅ ማፍቀርሽን
‎አይንሽ አጋልጦሻል
‎ አላምነውም ምግባርሽን

‎የወንድነት ወጌን
‎ ምን ባስቀድም አንደበቴን
‎መጠራጠር ሰርክ ልማድሽ
‎ አላመንሽም እኔነቴን

‎ እወድሻለሁ

‎ ብትሸሸጊው ያንቺን ስሜት
‎  አይንሽ ሁሉን ይነግረኛል
‎  አትደብቂኝ....ወደሽኛል


‎ዮኒ
‎     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
👍2517
ስወደው ነው የጠላሁት
ሳፈቅረዉ ነው የሸሸሁት

የጠላሁትን እሹሩሩ የተካንኩበት
እንደጦረኛ ገፊዬን ማቅረቡ’ን ሳዉቅበት

በል…….
ወደድኩሽ ባልክበት አፍህ ጠላሁ በል
ናፈቀሺኝ ያለአንደበትህ - ላይ ታበል

እሾህን በእሾህ
ፍቅርን በመጥላት
እየወደዱ በመገፋፋት
እናስቀጥለዉ

ሰይጣኔን ሰይጣንን መስለህ ግፈፈዉ
አይነ ጥላዬን ናና እንሸዉደዉ።


ትዝታ ወልዴ✍️

@getem
@getem
@Tizita21
47👍8👎4🔥1
ቃል ከአፋቸው ሳይወጣ
ፍቅር ተሰናብቶ መለያየት መጣ
ቻው እንኳን ሳይሉኝ
ሁሉም አገለሉኝ

እኔ ብቻ ሆነ እኔን የወደደው
እሱስ ተራው ደርሶ መች ይሆን ሚሄደው

By @Absari_seven

@getem
@getem
37🤩9🔥5
የአንተም ልብ ድንጋይ
የኔም ልብ ድንጋይ ...
(ለዚያ ነው መሰለኝ )
በተጋጨን ቁጥር በፍቅር የምንጋይ።

By meron ghetnet

@getem
@getem
@paappii
54🔥20🤩14👍7
ራሱ’ንደማይጠጣ - የውሃ ማሰሮ፣
መሆን ላልተቻለው - ክው ያለ ጉሮሮ፤
አስመሳይ ደጋጎች - ውሃ ሰጡት’ና፣
የሞት ሞቱን ሲኖር - ችግሩ እንደጠና፤
ጉሮሮ ማሰሮ - ተመሳስሎባቸው፣
ያጠጡትን ቀድተው - መውሰድ ላቃታቸው፤
ረሃብ አንጎራጉሮ - ለለመደው ውሃ፣
ሰጥቶ ተቀባዮች አስቀየመልሃ!

(የሞገሴ ልጅ)
@eyadermoges

@getem
@getem
@getem
19👍14🔥1
ላውሊያ ንጉስ ለጠቋሪት ደጋሽ
ዚያራ: ላይ ካድመሽ
ህልሜን ግራ አጋባሽ
የፅልመት እጆቼን ለኑሮሽ: ከነዳሽ
በኔ ጉሜ: ይዘሽ ተፋሽው ልብሽን
ካድመሽ: አገባሽው የልደት: ቀንሽን
ድቤው ስራ አልፈታ: ከህልሜ አለው ጋንታ
ላንቺ ኑሮ ሰቶ እኔን እሚያፋታ::
  
                                            by አለምሰገድ ወልዴ

@getem
@getem
@getem
23👍3
ዛሬ ሌላ ሰው ነኝ።

ያኔ ትንሽ ሆኜ-
በእድሜዬ ለጋ - በበሓሪ ችኩል፣
አፍንጫ አሽትቻለሁ፣
ቀድሞኝ ከበሰለው - ለመታየት እኩል።

ልጅነትን ሳልፈው-
ሌላን ማየት ትቼ - ራሴን ዐየሁ እና፣
ገደብ ሰራሁለት፣
ጉጉቴ ልክ አልፎ -ስጎድል እንዳይቀና።

ልልሽ የፈለግሁት-
አንቺ ላታስቢኝ አትበይ “ረስተኸኛል”፣
የሰርግሽን ፎቶ-
ከልቤ ሳደንቀው እራሴም ገርሞኛል።
ምክንያት፣...
ያኔ ወጣትነት - ኩራት የኮፈሰኝ፣
ትእቢት ላንዳፍታ - ወስዶ የመለሰኝ፤
እልህ እየጋተ - ምላጭ የሚያስውጠኝ፣
“ዛሬ ብቻ” ባይ ኅዝብ - አስሶ እሚመርጠኝ፤
ዛሬ...
አንቺ የኖርሽውን - ዘመን የኖርኩ እኔ፣
እራሴን ያስተማርኩ - በሕይወት ጠመኔ፤
አንቺ “ፈልጉኝ” ባይ - እኔ ራሴን መሪ፣
አንቺ ላይሽ ፋኖስ - እኔ ውስጤ በሪ፤
ከመንገድሽ እሩቅ - መንገዴ ወስዶኛል፣
ሺህ ግዜ አግብተሽ - ሺህ ግዜ ብትፈቺ ምን ያናድደኛል?

በርቺ 😐
@eyadermoges

@getem
@getem
@getem
26👍20🔥1😁1