ግጥም ብቻ 📘
66.5K subscribers
1.54K photos
31 videos
61 files
175 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
እናት አለሜ🤱🏽 ♥️
Yohannes_Lawgaw @Sleenee ስለ እኔ ስለ ኔ ዮሀንስ ላውጋው
እናት አለሜ🤱🏽 ♥️
ስለ_እኔ
Yohannes_Lawgaw 🌿
#High_quality
@getem
@getem
@getem 🌿
👍1
🔆ፊደል ነው ጠላትሽ🔆

የእውነት: ደራሲ: የታደለ: ጠቢብ
አምላክ:ያቀመሰው:ከሰሎሞን:ዘቢብ
በምናብ: አለሙ: የሚኖር:ተራቆ
ነገር :የሚከትብ:በስሜት:ውስጥ:ጠልቆ
ከተራማጁ ሰው: ከአዳም -ዘር: ሁሉ
(ordinary person)
እጅግ:የሚለየው::ረቂቅ:አመሉ:-
የእውነት: ደራሲ : ከሆነ: ፈላስፋ
1-ሃሳቡ:ገናና: ምልከታው :የሰፋ!!!!
2-አኗኗሩ :ግሩም: :የደፋበት:ውበት
ጠባዩ :የተለየ: ጥያቄ :ያለበት::
3-የስሜቱን: ይዘት :የሚፅፍ :በብዕር
ኮከብ: ነው: ደራሲ: የህይወት: መምህር!
🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆አንቺም:ተለይተሽ:በገጣሚው :ልብ:ውስጥ:ብታገኚም:ቦታ
ቆንጆ :ተለይተሽ:በደራሲው:ልብ:ውስጥ:ቢኖርሽም:ቦታ
ሲያሻኝ:ትሻርያለሽ:ሲያሻኝ:ትተኪያለሽ:በብዕሬ:ቃታ
እናልሽ:አንዳንዴ:እጅጉን:ከራኩሽ
እናልሽ:አንዳንዴ/ትኩረት:ከነፈኩሽ
በማስታወስ:ፋንታ:ውዴ :ቸላ:ካልኩሽ
ያንቺ:ተቀናቃኝ:ሌላ:ሴት :ሳትሆን ፊደል:ነው:ጠላትሽ!!


ገጣሚ:::ዳዊት :ጥዑማይ

2/12/2013E.C

@getem
@getem
@paappii
👍2
አንድ ቀን በድንገት !
(ሚካኤል . አ )
አፈቀርኩሽ የሚል ስፅፍ አንዲት ጦማር
ነው ለካ በስካር!
ወደድኳት እያልኩኝ ለሰው ሳወራ
ደልቶሀል ይለኛል ሁሉም በየተራ
ሀገር ለጦር ከቶ ሲወጣ ዘመቻ
ዱላውን ሲያነግት ለጠላቱ መምቻ
ከወንድ ሁሉ ቀበጥ እኔ ነኝ ለብቻ!
አፍቃሪ ሰው ስሆን...
ኑሮ በአንድ ጎኑ ሲያወርድብኝ እቶን
በርበሬና ሽሮ ዋጋው እየናረ
ወድጃለሁ ማለት ቅብጠት ሆኖ ቀረ!
ደግሞ ሌላ ጦማር.. .
ደግሞ አዲስ ስካር.. .
አይንሽ ይመቸኛል ፀጉርሽ ይገርመኛል
ስስ ልቤ በለሊት አንቺን ይከጅላል
እያልሁ እየፃፍኩኝ
ፍቅሬን እያለምኩኝ
እህል አልወርድ አለኝ... ብዬ እንዴት ላክል?
እንቅልፍ እንቢ አለኝ ... ብዬ እንዴት ላክል?
በልቶ ም ለመተኛት
ማለፍ ያስፈልጋል የመከራን ክልል ።
በቃ እንደውም ተውኩት አልፅፍም ደብዳቤ
አፍራለሁ ለመውደድ...
ማፍቀሬ ቧልት ነው
ህዝቤ በቋፍ ታስሮ.. . ክምር ሆኖ ሲነድ።
ደግሞ ሌላ ጦማር
ደግሞ አዲስ ስካር
አነሳሁኝ ብዕር.. .አነሳሁ ወረቀት
ኑሮ ሲያነሳልኝ የጫንቃየን ክብደት
ይኼን እፍን አየር ሰላም ሲያረብበት
እልካለሁ ብዬ አንድ ቀን በድንገት
"ይድረስ ላንቺ" ብዬ ጀመርኩኝ ፅህፈት!

@getem
@getem
@paappii
1
" ማርያምን!" እያለ
#ቃለአብ ፀጋዬ
ኪሴ የመሉትን የሳንቲም ጥርቅም
እራብ ይድፋኝ እንጂ አንዷን አላጎልም
እል እንዳልነበርኩኝ
ግጠምልኝ ብለሽ
ብዕሬን ሳስተፋ ወረቀቴን ሰቀድ
ሳንቲሜን ጨረስኩኝ
ምን አውቅልሽ
ብለሽ?
ቃላትን ወርውሮ ቤት ስለመደብደብ
በለዛ በጥበብ
ስለመግለፅ ሀሳብ
. . . . . . . .. .. . .. . .. ... . .. . . .. . .
ሂጂ እሱን ጠይቂ . . .

ቃላት መርጦ ቆርጦ
በወግ ያገንሻል
አይ! ካልሽ አይገደውም
ቃላት አስሸብርቆ ልዕልት የሰኝሻል
"ማርያምን!" እያለ
ማመን መቀበልን ላንቺ ይተውልሻል

እኔ እንዲያ አይደለሁ . . . . .
ምትሐት ካለው ምናብ
የሚያማልል ሐሳብ
ምሉዕነት ካለው
ድንቅ ችሎታው ላይ
ጥቂት እንዲያደርስሽ
ሚካኤል ጋር ሄደሽ

ቅጥ የጣ ፍላጎት
ግዙፍ ግብዝነት
ይህ ሁሉ አመልሽን . . .
በቃላት ቆራርጦ
ብዙ ትንንሾች አድርጎ አስቀምጦ
እንደምትፈልጊው
በስንኝ ቆጣጥሮ እጅግ ያረቅሻል
"ማርያምን!" እያለ
እንኳን እምነትሽን ልብሽን ይወስዳል፡፡

እሱን ፈራሁ እንጂ: እነግረው ነበረ
ማርያም በቸረችው
መግጠምን ያውቀዋል ቃል እየቀመረ፡፡
@Kalsagi
ነሀሴ 4/2013
ለ፡ ሚካኤል አስጨናቂ
ለድንቅ ችሎታ ጥቂት ሙገሳን ለመለገስ. . . ጥሩ ለሰራም ምስጋና ይገባው ዘንድ እነሆ፡፡

@getem
👍5
የት ልሁን ንገሩኝ

ከግራ ወይስ ከቀኝ
የት ሄጄ ልገኝ
ከማን ጋር ልመደብ
በየትኛው መዝገብ
በምን አይነት ስሌት በየትኛው ቀመር
እ-ን-ዴ-ት-ስ ልሳፈር 
የቱ ጎራ ልግባ ማንንስ ልከተል
ሄጄ የቱን ልምሰል

የት ልሁን ንገሩኝ
መጥታቹ አማክሩኝ
ብቻ.............. ከውነታዉ አካፍሉኝ
ምንም አትደብቁኝ
ላይነጋ ከመሸም
ብርሀን ከሸሸም
ግዴለም ልወቀው
መጀመሪያዬ ላይ ደርሼ እንዳየዉ

የት ልሁን ንገሩኝ
ግልምቢጥ  መንገዴ መርቶኝ ከምጠፋ
መድረሻዬን ልወቅ አንዴ ላግኝ ተስፋ

ተፃፈ በ ጃሒዝ (@ja_hiz)
-2012-

@getem
@getem
👍2
Forwarded from አቶ anu😎
#ወዲያ_ሽሽ_ይለኛል!

© ሲራክ ወንድሙ @siraaq
.
ኑረት ሲረክስብኝ ፥ ሲሆን እንደ እቃ 'ቃ ፣
አዎን ያስፈራኛል ፥ የዘመን አታሞ
.................... ፥ የዘመን ድለቃ ፤
የድግግሞሽ ሰልፍ ፥ የእሽ ፡ ክርክሪት ምልዓት ፣
ሰው ሆኖ ተኝቶ ፥ ትል ሆኖ እንደመንቃት ።

ንጋት አድባር ሆኖ ፥ የሀገር ጌጥ የሀገር ዳስ ፣
ጀምበር በሰረቀ በአመሻሹ ፈለግ ፥ እንደካህን መርከስ ፤
እንደምኩራብ ከብሮ ፥ እንደ እንትን መንኳሰስ ።

አዎን ያስፈራኛል...
ወዲያ ሽሽ ይለኛል...
ወዲህ ግድም እሩጥ ፣
ወዲህ ግድም አምልጥ ፤
ወዲያ ጥግህን ያዝ ፥ ይለኛል ይለኛል ፤
የዘመኑ ቅኔ የዘመኑ መንፈስ ፥ መንን ያሰኘኛል ፤
ወዲያ ሽሽ ይለኛል ።
.............. | ። | ...............
ነሐሴ ፳፻፲፫ ዓ.ም
@getem
@Getem
@getem
👍3
በ +251984740577
ወይም @gebriel_19 ላይ ፎቶ በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ ሥዕል ማዘዝ ይችላሉ!
#ሥዕል_ብቻ የቴሌግራም ገፅ


@seiloch
@seiloch
#ጅብ እና ዘንድሮ

የድሮ ጅብ ትህትናው
ከማያውቁት ሄዶ፣<<ቁርበት አንጥፉልኝ ?>>
ነበረ ልመናው ።

የዛሬ ጅብ ድፍረቱ
ባለቤቱ እያየው ፣ ባይኑ በብረቱ
ይሰለቅጥና ፣ ላሚቱን ዘርግፎ
እበረቱ ያድራል ፣ ቁርበቷን አንጥፎ።

@getem
@getem
👍4
#አንዲት አንቺ

ባንዲት ሕይወት
ባንዲት ዓለም
አንዲት ሩህ
ለማለምለም ፤

አንዲት አንቺ - - - -
ያንዲት ምሥጢር ፣ አንዲት ፍቺ
ያንዲት ፍቺ ፣ አንዲት ፋና
ያንዲት ፋና ፣ አንዲት ዳና
አንዲት እንቺ - - - - - -
ያንዲት አንዲት - ህልውና
መጣሽ ሙሉ ፣ ጠፋሽ ኦና !

@getem
@getem
1
#ውሉድ ወወላድ*


የወለደች ኹሉ . . .
እናት አትባልም ! ግብሯ ካልተለየ ፤
የተወለደ ልጅ . . .
አይባልም ጧሪ ! ምግባሩ ካለየ ።

ዘር ስላካፈለ . . .
የአባት መሆን ክብር በከንቱ አይሰጥም !
ከልጅ ስም ቀጥሎ ስሙ አይቀመጥም !

እፍኝትን እይዋት . . .
እናት ትሞታለች ፣ ትውልድ ለማስቀጠል
አባትም ይሠዋል ፣ በፍትወት መቃጠል ።
አንበሳም ደቦሉን . . .
በጊዜው ካልቀጣ ንግስናው ይቀማል ፤
የልጅነት ሥሥት ፣
የአባትነት ድርሻ ለክብር ይወድማል ።

አዎ !
እናት ክብሯን ይዛ ፣
ልጅ ግብሩን ተላብሶ ፣
አባት በስም ነግሦ ፣
ካልተነፃፀረ ፤
የመዳን ምሳሌው ትንቢቱ ተሻረ ።

#የሞት ጥቁር ወተት
#ተስፋሁን ከበደ
@getem
@getem
@beckyalexander
👍2
ይነጋል !
አዳም መንገደኛው ተስፋውን ይባጃል
ነገን እከብራለሁ ብሎ ላብ ይዘራል።
"ነገ እረዳለሁ ሚስኪናን ደጅ ሄጄ
ነገ እነፃለሁ ... ሀጥያቴን ክጄ
ነገ እወልዳለሁ ... አንዲት ሴት አግብቼ"
ብሎ እያሰበ ... ከቀን ጋር ይበራል...ከቀን ጋር ይከንፋል !
ማታ አመሻሽ ላይ ...
ቀስቱን የወደረ አዳኝ ሙት መልዐክ አዳም ላይ ይስቃል።

....#(ሚካኤል . አ)

@getem
@getem
@getem
#የእረኛ_ማዕረግ
.
.
ከወዲያ ከጨፌ ከውድማ ከመስኩ፣
ሺህ በግ መጠበቅ ነው የእረኛ ልኩ።
ቀበሮ ቢለፋ ተኩላ ቢነፋፋ፤
ጅብ ጥላውን ቢጥል ቢያጓራ ቢጀነን፣
ለበጎቹ መንጋ፤
መልካ አዋቂ ብልህ እረኛ ነው ደጀን።

ከጥንትም ከወንዙ፤
ተኩላ ያልበጠሰው ጅብ ያላፈረሰው፣
የቀትር ቀማኛ ቀበሮ ያልዳሰው።
የተቆላለፈ የተጠላለፈ፤
ዕጣ ያስተሳሰረው የመዋደድ ሀረግ፣
ተኩላዎች ሲራቡ፤
በኩር በግ መሆን ነው የእረኛው ማረግ።

ለዘመኔ ጥበብ፤
ለዘመንህ ኩታ፤
"ቀን ያልፋል" ላሉት ቃል፤
ጥለቱ እስኪቋጭ እኔ ችዬም አልደርስ፣
እረኛም ልሁን በግ፤
መሰሪም ልሁን ደግ፤
ተኩላው ከሚበላኝ በልቼው ልቀደስ።


"ዐብይ" ( @abiye12 )

@getem
@getem
@getem
1👍1
::::ጭስ::::

እኔ ማለት ጭስ ነኝ፣ መውጫ መግቢያ የማላጣ፣
የማልሞክረው የሌለኝ፣ወደ ሰማይ እስክወጣ፤
ምን አልባት ግን ጭስ ካልሆንኩ ስጋ ሁኖ ሰውነቴ ፣ እኔ ማለት ደፋር ሴት ነኝ መፍጨርጨር ነው ሽልማቴ።
(አቢሲኒያ ፈንታው)

ቅዳሜ ነሐሴ 15 በብሔራዊ ቲያትር "ስንቅ" መጽሐፌ ይመረቃል። ተጋብዛችኃል።

@getem
@getem
👍1
አትመጪም አውቃለው
ምድር አትችልሽም የት አደርግሻለው?

@getem
@getem
@paappii

#Migbar siraj
👍2
#ጊዜ_ጌታ
( #ናታን_ኤርሚያስ )
@UniqueDy
.
.
በልኬቱ : ወርዶች : ፍቅሩን : ደርድሮ፣
ነገ : አብሮሽ : ላይዘልቀው : ዛሬሽን አፍቅሮ፣
ልብሽን : ፈልጎ : ልቡ : ውስጥ ሊከትሽ፣
በሀሰት : ምህላው : የእውነት : ሲክብሽ፣

ትላንትን : ማልቀሱ፣
ሳትቆስል : ነብሱ፣
ከላይ : ከላዩ : ላይ፣
እንባውን : ዘርግፎት : መከፋቱ : እንዲታይ፣
.
.
እዘኚልኝ : ብሎሽ፣
አጥፎ : እያሳዘነሽ፣
በፍቅር : ለማረፍ : ብዙ : ተሰቃየሽ፣
ባለፍሽበት : መንገድ : እግሮችሽ ሲጣሉ፣
ዘመን : አሽከርክሮሽ : ወደቅሽ ከመሀሉ፣
መውደቂያው ቢደላሽ አልጎዳኝም ብለሽ፣
ራሱን : ለመያዝ : እግሩ : ስር : ተገኘሽ፣

ነግሬሽ : ነበረ : ጊዜ : ጊዜ : እንዳለው፣
ስንቱን : እያነሳ : ስንቱን : እንደጣለው፣
ላትረሺው : ረስተሽ : ዛሬ ላይ : ብትፈርጪ፣
ለጊዜ : ተስለሽ : ከራስሽ : አምልጪ !


@getem
@getem
@getem
👍3
Forwarded from —(•·÷[ ◔͜͡◔ Tizita21 ◔͜͡◔]÷·•)—
ፋራ እኮ ነኝ

መሳቅ መጫወትን የማዉቅ
በአላማዬ ቀልድ የማላቅ
ለናቀና ላንጓጠጠኝ
በቃላቶች ላሽሟጠጠኝ
ቀና እንዳልል ለሚራገም
የዉድቀት ቀኔን ለሚያልም
ሳቅ ነዉ መልሴ
ዝምታ ነዉ እስትንፋሴ
ፓሪ ኦቨር የማያምረኝ
ጌመር መሆን ማይታየኝ
በሠዎች ፊት የሠገጥኩ
እራሴን ግን ያከበርኩ
ለሩቅ ህልሜ የታመንኩ።
ለእድሜ እኩያ የማልመች
አካባጅ ነች የተባለች
እኔ ማለት የቺ ሴት ነኝ
ባንተ ቃላት የማይበርደኝ የማይሞቀኝ።

በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

@getem
@getem
@Tizita_wolde
👍41
Audio
100% የ ተስፋ እዉነተኛ ታሪክ
ተመስጣችሁ ስሙልኝ
ትዝታ ትልቅ ነገር እንደጠየኩሽ አዉቃለሁ ግን ከኔ ታሪክ ጋር ይመሳሰላል..........
እኔም የነገርከኝን እንደዚህ በደብዳቤ ሞነጨርኩልህ።
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

@getem
@getem
@Tizita_wolde
👍1
አንድ ሰው የሞላ!

ብሎ የሚጣራ...

ኑሮ ያባተለው ጨብራራ ወያላ

አንዱን ሰው ያወርዳል ሊተካ በሌላ

እልፍ ተጓዥ እግሮች መድረስ የቋመጡ

ለመድረስ ሲሮጡ

እድል የቀናለት ገዱ ያማረለት

መንገድ ይጀምራል በዚች ታክሲ ህይወት።

ሹፌሩ ፈጣሪ

ህላዌን አብራሪ 

እስትንፋስን ዘርቶ መንገድ እየለየ

ተጓዥ ይቀበላል

ግፊያውን የረታ የማህፀን ፍሬ

መንገድ ይጀምራል።

ወያላው ሙት መ'ላክ የፈጣሪ ረዳት

መለከቱን ነፍቶ ቆሞ ይለፍፋል

ህይወት ያባከነው ተጓዥ ይሳፈራል

አንድ ሰው የሞላ ...!

ለህይወት ሁለት መልኮች

ለችግር ለተድላ 

መሳፈር ... መሳፈር ...

መጓዝ ...መሄድ ... መብረር.. .

መድረሻን መማተር ...

ከዚህ ጉዞ ላይ ነው 

የደረሰ መስሎት አውርዱኝ የሚለው

ወራጅ የሚፈጠር!

....

ሚካኤል .አስጨናቂ


@getem
@getem
@getem
👍5
Audio
ናና እንከራከር
ምናልባት ምናልባት
ህይወት አስተምራህ
በአኗኗር ቃኝታህ
አንደበትህን ዘግታ
ጭንቅላትህን ገትታ
በችግር አጫዉታ
በማጣት አግባብታ
ከእጦት አጋብታ
ካላስተማረችህ ከሜዳዋ አግብታ
...................ናና እንከራከር
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

@getem
@getem
@Tizita_wolde