ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
▶️ ምስልና ቅርጻ ቅርጽ በየወቅቱ #በክርስትናው_እምነት ውስጥ ሰርገው ገብተውና #እያደጉ መጥተው ዛሬ እንደሚታየው #ልዩ_አምልኮ እየተሰጣቸው ይገኛሉ። #ህዝበ_ክርስቲያኑ በተለይም #የማርያም_ስዕሎችን #እንዲቀበሏቸውና_እንዲሰግዱላቸው ከተደረገበት ዋና ዋና #ምክንያቶች መካከል፦

〽️ ሀ. ምስሎቿ #ይናገራሉ {ያወራሉ} በሚል ማስፈራራት፦

<<በዚያም ቤተክርስቲያን የእመቤታችን ስዕል ነበረችና ያ ብላቴና ስእሏን እጅግ ይወዳት ነበር። መምህሩ በሄደ ጊዜ ወደ ስዕሉ ቆሞ እጅ ይነሳትና ቅዳሴዋን ይደግም ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን ስዕሉ ፊት ቆሞ ሳለ ስእሏ ተነጋገረችው። "ወዳጄ ሆይ አንተ ከምትወደኝ ይልቅ ፈጽሜ ወድጄሀለው! በአንተም ደስ ብሎኛልና በእኔ እመን! አለችው"። ያም ልጅ ከስእል ቃል በሰማ ጊዜ ፈጽሞ አደነቀ እጅግም ፈራ[1]>>

<<የኢትዮጽያ ሰዎች እነዚህን ትዕቢተኞች ራሳቸውን ተከናንበው እግራቸውን ተጫምተው ወደዚች ስዕል ሲገቡና ሲወጡ አይተው እንደ ግብጻውያን ክፉ ልማድ አደረጉ። ወደዚችም ስዕል ጫማ አድርገው ገቡ። . . . እመቤታችንም ወደ እኔ ስዕል ጫማ ተጫምታቹ የምትገቡ መራር ትምህርትና ክፉ ምግባር እንደምን አበቀላችሁ?! አለቻቸው ይህን ብላ የኢትዮጽያን ሰዎች ከስዕሏ በወጣ ቃል ገሰጸቻቸው[2]>>

〽️ ለ. ምስሎቿ ባለቡት #ይንቀሳቀሳሉ፣ የተለያየ #ድርጊትንም_ያደርጋሉ በሚል ማስፈራራት፦

<<በማርያም ስዕል ፊት ሲሰግዱ ስዕሏ ራስዋን ዘንበል አድርጋ ጸሎታቸውንና ስግደታቸውን ተቀበለች[3]>>

<<አባታችንም ከስእሏ ፊት ሲጸልይ እመቤታችን ከስእሉ አናገረችው። ጡቷንም አውጥታ እንካ ጥባ እንደ ልጄም አርጌ አሳድግሀለው አለችው። እርሱም ከጡቷ ጠባ[4]>>

<<አንዲት ሴት የወለደች ነበረች፧ ያቺንም ሴት ልጇን ጅብ ወሰደባት። ወደ ቤተክርስቲያንም ሄዳ በእመቤታችን ስዕል ፊት ቀይ ልጄን እስክምትመልሽልኝ ድረስ ልጅሽን እኔ ከእጅሽ ላይ እወስደዋለው አለች። ከዚያም ማርያም የታቀፈችው ልጇን {"ክርስቶስን ለማለት ነው"} ሰጠቻት፤ ሴትዮዋም ወደቤት ወሰደችው። ማርያምም ወደ ቤቷ መጥታ ጅብ ነጥቆ የወሰደብሽ ልጅሽን ውሰጂ ልጄን ስጪኝ ብላ ተቀበለቻት[5]>>

〽️ ሐ. ምስሎቿ #ሕይወት እንዳላቸው በማስመሰል ማስፈራራት፦

<<አፍርንጊያውም ስእሏን ይወስዳት ዘንድ እንዳልተቻለው ባወቀ ጊዜ ሾተል ይዞ እጁን በመስኮት አዝልቆ ከስእሉ የሥጋ ቁራጭ ያክል ቆረጠ። ያን ጊዜ ከስዕሉ ደም ወጣ። እርሱም የስጋ ቁራጭ ያክል ይዞ ወጥቶ ተሰወረ። ያን ጊዜም ሰዎች አውቀው ፈልገው በጭንቅ አግኝተው ያዙት ፤ይገድሉት ዘንድም ወደዱ። ያን ጊዜ እኔ ስለመውደዱ ክብር ሊሆነው ወስዷል እንጅ ይህን በክፋት አላደረገውምና ተውት አትግደሉት፤ የሚል ቃል ከስዕሉ ተነገረ ነገር ግን የተቆረጠውን ስጋ ከሱ ወስዳቹ ከተቆረጠበት ቦታ ግጠሙት። ያን ጊዜውን አኖሩትና ተጣብቆ ቀድሞ እንደነበረ ሆነ[6]>>

<<ያች ስዕል ስጋን የለበሰች ትመስላለች ከእርሷም እንባና ወዝ ይወጣ ነበር። ከወዙም የተቀቡት ከሚያስጨንቅ ደዌያቸው ይፈወሱ ነበር[7]>>

〽️ መ. በምስሎቿ ፊት #ያልሰገደ #የሞት_ቅጣት እንደሚያስከትል በማወጅ ማስፈራራት፦

<<በስፍሏም ፊት ስገዱ ለስዕሏ ያልሰገዱ ግን ከቆመበት ቦታ ይጥፋ ስም አጠራሩም አይታወቅ[8]>>

<<ለእመቤታችን ስዕል ስላልሰገደ ሞተ[9]>>

<<ወእሰግድ ካዕበ ለድንግልናኪ ክልኤ
ወእሰግድ ሰልሰ ለሥዕልኪ ቅድመ ጉባዔ
ዘኢሰገድ ለስዕልኪ አስሪጾ ምማኤ
በሥጋሁ ወበነፍሱ ኢይርከብ ትንሳኤ>>

ትርጉሙም፦

<<በሁለት በኩል ድንግል ነሽና እሰግድልሻለው
ለሥዕልሽም በጉባኤ ፊት ሶስት ጊዜ እሰግዳለሁ
ለሥዕልሽ ከመስገድ ወደ ኋላ ያለ
በነፍሱም በስጋውም ትንሳኤ አያግኝ[10]>>