ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
〽️ 15ኛ፦

〽️ ሐዋ 1፤ 9-11፦

ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲያርግ ሁሉም ደቀመዛሙርትና ሴቶች ማርያምም ጭምር በደብረ ዘይት ተራራ ዕርገቱን ሲመለከቱ ሁለቱ መላእክት በአጠገባቸው ቆመው < ለማርያም ብቻ> ወይም < በማርያም በኩል> ሳይሆን ለሁሉም በእኩል አይን <<የገሊላ ሰዎች ሆይ...>> በማለት ለምን ተናገሩ⁉️ ማርያም <የገሊላ ሰዎች ሆይ> በሚለው ውስጥ መካተቷ ከሌሎች የተለየች አለመሆኗን አያሳይምን⁉️

〽️ ሐዋ 1፤ 12-14፦

ከክርስቶስ እርገት ቡሀላ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሱ ማርያም ከሐዋሪያቶቹ ጋር ሌሎችም በርካታ ሴቶች ያለምንም ልዩነት ለአንድነት ለጸሎት ይተጉ ነበር። ይህ በግልጽ ማርያም ከፍጡራን የተለየች ወይም ወጣ ያለች እንዳልነበረች አያሳይምን⁉️

〽️ ሐዋ 1፥15፦

የጸሎቱም መሪ ሐዋሪያው ጴጥሮስ ነበር እንጂ ማርያም ከጉባኤው ጋር ምእመን ከመሆን ውጪ የአምልኮው መሪ እንኳን አልነበረችም። ይህ እንዴት ከፍጡራን የተለየች ናት እንድንል ያስደፍራል⁉️

〽️ ሐዋ 1፥16፦

ማርያም ባለችበት ጉባኤ ተነስቶ <<ወንድሞች ሆይ>> በማለት በቀጥታ ንግግሩን ከመጀመር ይልቅ በመካከላቸው ለነበረችው ማርያም ስግደት ወይም የተለየ አክብሮት ለምን አላቀረበም⁉️ ይህን አለማድረጉም ከእነሱ የተለየች እንዳልነበረች አያሳይምን⁉️

〽️ ሐዋ 1፥25፦

በዚህ ጉባዔ ማርያም ባለችበት <<ሲጸልዩም የሁሉንም ልብ የምታውቅ አንተ ጌታ ሆይ>> ብለው ለምን ቀጥታ ወደ ጌታ ጸለዩ⁉️ እሷ ከፍጡራን በላይ ስለሆነች ወደ ማርያም ወይም በማርያም ስም ለምን አልጸለዩም⁉️

〽️ ሐዋ 2፤ 3-4፦

መንፈስቅዱስም ሲወርድ ሁሉም ላይ እንዴት እኩል ወረደ⁉️ ከፍጡራን በላይ ነች ለምትባለው ለማርያም የተለየ ጸጋ(መንፈስ) ለምን አልተሰጠም⁉️ አለመሰጠቱ በእግዚአብሄር ፊት ያው እንደማንኛውም ክርስቲያን እኩል እንደሆነች አያሳይምን⁉️

〽️ ሐዋ 2፤ 5-10፦

ማርያም ከሴቶች ሁሉ የተለየች፣ ከፍጡራን በላይ የሆነች ብትሆን ኖሮ በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩት አይሁዶች በሁሉም ላይ ከወረደው ከመንፈስ ቅዱስ የተነሳ በገዛ ቋንቋዎቻቸው ሲናገሩ በሰሙአቸው ጊዜ በሁሉም ተገረሙ ከማለት ይልቅ ከእነሱ ሁሉ ለላቀችውና ለተለየችው ለማርያም እንዴት የተለየ አትኩሮት አልሰጡም⁉️ ይልቁንም በሁሉም ተገረሙ ማለቱ እንደነሱ እኩል ማንነትና ጸጋ ስለነበራት አይደለምን⁉️

〽️ ሐዋ 2፤ 14-18፣ 17-20

መንፈስቅዱስም የመጣው ማርያም ስላለች ሳይሆን በነብዩ በኢዩኤል የተተነበየው ይፈጸም ዘንድ ነው። ስለዚህ የማርያም በአካል መኖር የተለየ ነገር እንዳልነበረው ይህም ከሌሎች የተለየች እንዳልሆነች አያሳይምን⁉️ ማርያምም <<ስጋ በለበሰ ሁሉ ላይ>> በተባለው ትንቢት ውስጥ መካተቷ እሷም ስጋ ከለበሱት ጋር እኩል መቆጠሯ ፈጽሞ ከሌላው የተለየች እንዳልሆነች አያሳያምን⁉️ ይህ ካልሆነ ታድያ <<ስጋ በለበሱት ሁሉ ላይ>> በሚለው ትንቢት ውስጥ ለምን ተካተተች⁉️

〽️ ሐዋ 2፤ 22-35፦

ማርያም ከፍጡራን ሁሉ በላይ ከሰው ሁሉ የተለየች እስከሆነች ድረስ ሐዋርያት በመንፈስ ቅዱስ ሆነው በመካከላቸው ማርያም ብትኖርም <<የናዝሬቱን ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሄር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበር>> በሚል ቃል ለምን ክርስቶስን ብቻ ማዕከል ያደረገ ስብከት ሰጡ⁉️ ስለማርያም ያሉት አንድ ነገር እንኳን ለምን አልነበረም⁉️

〽️ ሐዋ 2፤ 37-38፦

የሐዋርያትን ስብከት የሰሙት ህዝቦች ሐዋርያትን ምን እናድርግ ብለው ሲጠይቋቸው በመካከላችን እናቱ ማርያም ስላለች በእርሷ እመኑ ወደ እርሷ ወይም በእርሷ በኩል ቅረቡ፣ እርሷን ተስፋ አድርጉ ለምን አላሉም⁉️ ይልቁንም ንስሃ ገብታችሁ በኢየሱስ ስም ተጠመቁ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ የሚል ክርስቶስን ብቻ የገለጸ መልስ ለምን ሰጡ⁉️

〽️ ሐዋ 2፥47፦

ሁሉም በአንድነት እግዚአብሔርን ብቻ በቀጥታ ከማመስገን ይልቅ አንዴም እንኳን ወደ ማርያም ለምን አልጸልዩም፣ ምስጋና አላቀረቡም⁉️ የማርያምስ በመካከላቸው መኖር ምን የተለየ ጥቅም ሰጣቸው ታድያ⁉️

〽️ 16ኛ፦ <<ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች>> የሚለው ብሂል የሚሠራው ወይም ከፍጡራን ሁሉ በልጣ እንድትታይ ሲደረግ የነበረው ማርያምን ነው። ፍጡራን በሚለው ውስጥ ደግሞ #ሰማዕታት#ጻድቃን#ነቢያት#ሐዋርያት#ደናግላንና #መነኮሳት ይገኙበታልና ከእነዚህ ሁሉ #የላቀችና #የበለጠች ስለሆነች ከእነሱ ሁሉ ይልቅ ወደ ማርያም #መጠጋታችን፣ ወደ እሷ #መጸለያችን፣ እሷን #አማላጅን #ለምኝለን ማለታችን.... ተገቢ ነው ይባላል።
የድርሳነ ኢያቄም ወሐና አዘጋጅ ግን በዚህ የሚስማማ አይደለምና <ደስተኛ ከሆኑ ከማህበረ በኩር ከሰማዕታት ከጻድቃን ከነቢያት ከሐዋርያት ከደናግል ከመነኮሳት ማህበር ይልቅ አስቀድማችሁ መታሰቢያዋን አድርጉ> በማለት ለማርያም የነበረው ከፍታ ላይ ወስዶ ሌላ ሰው ያስቀምጣል (ገጽ 45-46)።
ፀሐፊው ይህን ሥፍራ ሲሰጥ ሐናን ከማርያም እኩል ሥፍራ ሰጥቷት እንደሆነ ግልጽ ነው። ሐሳቡን በተሻለ የሚገልጽለትንም መልዕክት <ቅድስት ሐናን ከልባችሁ አስቧት፣ ልጅ ያለ አባት ይከብራልን? ብልቴናስ ያለ እናት ታከብራለችን? እናንተም እናታችን ሐናን እንደ ልጇ እንደ አግዝትነ ማርያም አድርጋችሁ አክብሯት ክብረ በዓልም አድርጉላት...> በሚል አስቀምጧል። ስለዚህ <ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ> የሚለው አባባል ለማርያም ብቻ የሚቀፀል ሳይሆን ለሐናም ነው ማለት ነው⁉️

@gedlatnadersanat
(7🌐☑️) ይቀጥላል...