የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በሞሮኮ ተሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ከ23 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ማጣሪያ የመጀመርያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሞሮኮ አቻው 1 ለ 0 ተሸንፏል፡፡
ዛሬ በድሬዳዋ ስታዲየም በተደረገው የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ የሞሮኮን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ዩኑስ ኤል ባህራዊ በ29ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡
የመልሱ ጨዋታ ከአምስት ቀናት በኋላ ሕዳር 8 በሞሮኮ ይደረጋል፡፡

ማንቸስተር ዩናይትድ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖን አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቸስተር ዩናይትድ አርጀንቲናዊውን አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖን መሾሙን ይፋ አድርጓል፡፡
አሰልጣኙ በመጪው ረቡዕ በይፋ ኃላፊነታቸውን እንደሚረከቡ ክለቡ አሳውቋል፡፡
ፖቼቲኖ ከዚህ ቀደም ቶተንሃም ሆትስፐር፣ ቼልሲ እና ፒኤስጂን ጨምሮ የተለያዩ ክለቦችንና የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድንን ማሰልጠናቸው ይታወሳል፡፡
ማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ማይክል ካሪክን በትናንትናው ዕለት ከኃላፊነት ማንሳቱ የሚታወስ ነው፡፡

👍18
በጅማ ከተማ የቡና ኤክስፖ ላይ የ5 ኪ.ሜ ሩጫ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በጅማ ከተማ የተከፈተውን የቡና ኤክስፖ በማስመልከት የ5 ኪ.ሜ የሩጫ ውድድር ተካሂዷል፡፡
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ም/ቤት ፕሬዚዳንት ሰብስብ አባፊራ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ሀገራችን በዓለም ስሟ እንዲናኝ ካደረጉ ጉዳዮች መካከል በዋናነት ቡናችንና አትሌቶቻችን ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ነጋዴው ማህበረሰብና ቡና አቅራቢው ከቡና ልማት ባሻገር የአትሌቲክስ ዘርፉን በመደገፍ በጋራ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
በውድድሩ ከ1ኛ እስከ 5ኛ ደረጃ ይዘው ላጠናቀቁ ተወዳዳሪዎች ሽልማት ተበርክቷል።
በአብዱራህማን መሃመድ

👍2😢1
ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሆንግ ኮንግ እና በኔዘርላንድስ አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ በተሰጠው የሆንግ ኮንግ ግማሽ ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች አሸንፈዋል።
የ2026 ባንክ ኦፍ ቻይና ሆንግ ኮንግ-ዙሃይ-ማካዎ ግማሽ ማራቶን በወንዶቹ አትሌት አዲሱ ጎበና 1 ሰዓት ከ01 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ በመግባት 1ኛ ወጥቷል።
አትሌት አሊዪ ቃሲም ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት ታፈረ አዲሱ 8ኛ ደረጃን ይዘው ውድድራቸውን አጠናቅቀዋል።
በሴቶች አትሌት ውዴ ከፋሌ በ ሰዓት ከ09 ደቂቃ ከ04 ሰከንድ በመግባት አሸንፋለች።
በውድድሩ አትሌት ፋንቱ ወርቁ፣ አትሌት ባራኪ ረዳኢ፣ አትሌት አስማረች አንለይ ከ3 እስከ 5 ያለውን ደረጃ ይዘው ሲያጠናቅቁ፤ አትሌት ዘውዴ ውዱ 9ኛ ወጥታለች።
በኔዘርላንድስ በተካሄደ በ15 ኪ.ሜ አትሌት አሳየች አይቸው የዓለም 2ኛውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ በድንቅ ብቃት አሸንፋለች።
አትሌት አሳየች ውድድሩን 45 ደቂቃ ከ29 ሰከንድ በመግባት ነው ማሸነፍ የቻለችው።

👏5
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሞዛምቢክ ሽንፈት አስተናገደ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2027ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ 4ኛ የምድብ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሞዛምቢክ 1 ለ 0 ተሸንፏል፡፡
ቀን 10 ሰዓት ላይ በባሕር ዳር ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የሞዛምቢክን ብቸኛ ግብ ስታንሊ ራቲፎ አስቆጥሯል፡፡

ለማለፍ የነበረንን የተሻለ እድል አባክነናል፤ የቀሩንን እድሎች ለመጠቀም እንሞክራለን - አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ወደ አፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ የነበረንን የተሻለ እድል አበላሽተናል፤ የቀሩንን እድሎች ለመጠቀም እንሞክራለን አሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ 4ኛ ጨዋታ በባህር ዳር ስታዲየም ከሞዛምቢክ ጋር ባደረገው ጨዋታ 1 ለ 0 ተሸንፏል።
ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኞች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ከጨዋታው በፊት ማሸነፍ እንዳለብን ተነጋግረን ነበር፤ በመጀመሪያው አጋማሽ በሰራናቸው ስህተቶች ተሸንፈናል ብለዋል።
ጨዋታውን እንደ ጥሎ ማለፍ መርሐ ግብር አስበን ነበር ወደ ሜዳ የገባነው፤ በመጀመሪያው አጋማሽ ብልጫ ተወስዶብናል ነው ያሉት፡፡
በሁለተኛው አጋማሽ ያገኘናቸውን አጋጣሚዎች አለመጠቀማችን ዋጋ አስከፍሎናል ያሉት አሰልጣኙ፤ ለማለፍ የተሻለውን እድል ብናባክንም በቀሪ ሁለት ጨዋታዎች የማለፍ ያለንን የማለፍ እድል ለመጠቀም እንሞክራለን ሲሉ ተደምጠዋል።
የሞዛምቢክ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ችኩኒሆ ኩንዴ በበኩላቸው፤ ከመጀመሪያው ጨዋታ ስህተታችን ተምረን የዛሬውን ጨዋታ አሸንፈናል ብለዋል።
ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች በቀጣይ የምድብ ጨዋታዎች የሱዳን እና የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድኖችን ይገጥማሉ።
ምድቤን ሴኔጋል በ10 ነጥቦች ስትመራ ሞዛምቢክ በ7 ነጥብ ሁለተኛ፤ እንዲሁም ሱዳን እና ኢትዮጵያ በተመሳሳይ ሦስት ነጥብ 3ኛ እና 4ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
በእንዳልካቸው ወዳጄ

👎12👍3🙏2
ማንቸስተር ሲቲ ከፉልሃም ጋር አቻ ተለያየ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ማንቸስተር ሲቲ ከፉልሃም ጋር 1 ለ 1 አቻ ተለያይቷል።
በጨዋታው የማንቸስተር ሲቲን ግብ ኤሊዮት አንደርሰን እንዲሁም የፉልሃምን ግብ ሮድሪጎ ሙኒዝ አስቆጥረዋል፡፡
ሊጉ ሲቀጥል ቼልሲ ከሊድስ ዩናይትድ፣ አስቶን ቪላ ከሰንደርላንድ፣ ቦርንመዝ ከኖቲንግሃም ፎረስት፣ ኮቨንትሪ ሲቲ ከክሪስታል ፓላስ፣ ቶተንሃም ሆትስፐር ከኢፕስዊች ታውን በተመሳሳይ 12 ሰዓት ላይ ይገናኛሉ፡፡
የሊጉ መሪ አርሰናል ወደ ሴንት ጀምስ ፓርክ አቅንቶ ምሽት 2 ሰዓት ከ30 ኒውካስል ዩናይትድን የሚገጥምበት ጨዋታ ይጠበቃል።

👍11
አርሰናል ከቦሩሺያ ዶርትመንድ - የሻምፒየንስ ሊግ ተጠባቂ ጨዋታዎች
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ 5ኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ ዘጠኝ ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
አርሰናል በውድድር ዓመቱ በሻምፒየንስ ሊጉ ያለመሸነፍ ጉዞውን ለማስቀጠል ምሽት 5 ሰዓት ላይ በሜዳው ቦሩሺያ ዶርትመንድን ያስተናግዳል፡፡
ሁለቱ ክለቦች በመድረኩ እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች አርሰናል ሦስቱን ሲያሸንፍ፤ ዶርትመንድ በሁለቱ ድል ቀንቶታል፡፡
በሌላ የምሽቱ ጨዋታ በፕሪሚየር ሊጉ ካለፉት አራት ጨዋታዎች በአንዱም ማሸነፍ ያልቻለው ማንቸስተር ሲቲ ናፖሊን ያስተናግዳል፡፡
ሁለቱ ክለቦች በመድረኩ እርስ በርስ ካደረጓቸው አምስት ጨዋታዎች ሲቲ በሦስቱ ሲያሸንፍ፤ በአንዱ አቻ ተለያይተው በቀሪው አንድ ጨዋታ ናፖሊ አሸንፏል፡፡
ሪያል ማድሪድ ከፒኤስቪ፣ ፌይኖርድ ከፖርቶ፣ ስሎቫን ብራቲስላቫ ከሪያል ቤቲስ፣ አርቢ ሌፕዚግ ከሎንስ፣ ኮሞ ከኤኢኬ አቴንስ በተመሳሳይ ምሽት 5 ሰዓት የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው፡፡
ከእነዚህ ጨዋታዎች ቀደም ብሎ ጋላታሳራይ ከአስቶን ቪላ እንዲሁም ቦዶ ግሊምት ከላስክ ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

👍1
ማንቸስተር ዩናይትድ ዛሬ ወደ አሸናፊነት ይመለስ ይሆን?
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ 5ኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ ዘጠኝ ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
ማንቸስተር ዩናይትድ ወደ ፖርቹጋል አቅንቶ በአዲሱ አሰልጣኙ ማውሪሲዮ ፓቼቲኖ እየተመራ ምሽት 5 ሰዓት ላይ በስታዲዮ ጆዜ አልቫላዴ ስፖርቲንግ ሊዝበንን ይገጥማል፡፡
ስፖርቲንግ በመድረኩ ካደረጋቸው አራት ጨዋታዎች ሦስቱን አሸንፎ በአንዱ ሽንፈት ሲያስተናግድ፤ ማንቸስተር ዩናይትድ በአንጻሩ ሁለት አሸንፎ በሁለቱ ተሸንፏል፡፡
ሊቨርፑል በአንፊልድ በማንቸስተር ዩናይትድ ላይ ከተቀዳጀው ድል መልስ በተመሳሳይ ምሽት 5 ሰዓት ላይ የቤልጂየሙን ክለብ ብሩጅ ከሜዳው ውጭ ይገጥማል፡፡
የአምናው ሻምፒዮን ፒኤስጂ ከሮማ፣ ኢንተር ሚላን ከስቱትጋርት፣ አትሌቲኮ ማድሪድ ከቫይኪንግ፣ ሊል ከባየርን ሙኒክ፣ ሻካታር ዶኔስክ ከፌነርባቼ በተመሳሳይ ምሽት 5 ሰዓት ላይ የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው፡፡
ከእነዚህ ጨዋታዎች ቀደም ብሎ ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ሳባህ ከባርሴሎና እንዲሁም ስላቪያ ፕራግ ከቪያሪያል ይገናኛሉ፡፡

👍2
የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማት የመጨረሻ እጩዎች ይፋ ሆኑ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የ2026 ምርጥ ተጫዋች ሽልማት የመጨረሻ እጩዎችን ይፋ አድርጓል፡፡
በአዋቂዎች የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ለመባል ሳዲዮ ማኔ እና ፓፕ ጊዬ ከሴኔጋል እንዲሁም ኢስማኤል ሳይባሪ፣ አሽራፍ ሃኪሚ እና ኢብራሂም ዲያዝ ከሞሮኮ የመጨረሻ እጩ ሆነው ቀርበዋል።
በዓመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂነት ቮዚኒሃ ከኬፕ ቨርዴ፣ ያሲን ቦኑ ከሞሮኮ እና ኤድዋርድ ሜንዲ ከሴኔጋል የመጨረሻ እጩ ሆነዋል፡፡
በዓመቱ ምርጥ አዳጊ ተጫዋቾች ዘርፍ ኮትዲቯራዊው ዮን ዲዮማንዴ፣ ሞሮኳዊው አዩብ ቡአዲ እና ሴኔጋላዊው ኢብራሂም ምባዬ የመጨረሻ ሦስት እጩ ሆነው ቀርበዋል።
የዓመቱ ምርጥ ብሔራዊ ቡድን የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊው የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድንና የፍጻሜ ተፋላሚው የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን እንዲሁም በዓለም ዋንጫው ጥሩ ጉዞ ያደረገው ኬፕ ቨርዴ የመጨረሻ እጩ ሆነዋል።
የዓመቱ ምርጥ ክለብ የአልጄሪያው ኤምሲ አልጀር፣ የሞሮኮው ፋር ራባት እና የደቡብ አፍሪካው ማሚሎ ዲ ሰንዳውንስ የመጨረሻ እጩ መሆናቸውን ካፍ አስታውቋል፡፡
የዓመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ለመባል የኬፕ ቨርዴው አሰልጣኝ ቡቡሲታ፣ የሞሮኮው አሰልጣኝ ሞሃመድ ኦውሃቢ እና ሴኔጋላዊው አሰልጣኝ ፓፔ ቲያው ተመርጠዋል።
የ2026 የካፍ የዓመቱ ምርጥ ሽልማት በመጪው ሳምንት ረቡዕ በናይጄሪያ ሌጎስ ይካሄዳል፡፡

ራሂም ስተርሊንግ በቅጣት ገደብ የ12 ወራት እስራት ተፈረደበት
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ራሂም ስተርሊንግ በአደገኛ ሁኔታ መኪና በማሽከርከር ወንጀል በ18 ወራት የቅጣት ገደብ ተፈጻሚ የሚሆን የአንድ ዓመት እስር ተፈረደበት፡፡
የቀድሞው የሊቨርፑል፣ የማንቼስተር ሲቲ፣ ቼልሲ እና አርሰናል የመስመር አጥቂ ናይትረስ ኦክሳይድ የተባለ ያልተፈቀደ ዕፅ እየሳበ በማሽከርከር ጥፋተኛ መሆኑን አምኗል፡፡
የ31 ዓመቱ እንግሊዛዊ ባለፈው ግንቦት በደቡባዊ እንግሊዝ መኪናውን በከፍተኛ ፍጥነት ሲያሽከረክር በነበረበት ወቅት አደጋ አጋጥሞት እንደነበር ይታወሳል፡፡
ፖሊስ ከአደጋው በኋላ በተጋጨው መኪና የፊት ወንበር ላይ ሁለት የናይትረስ ኦክሳይድ ዕጽ መያዣዎችን ማግኘቱን ገልጾ ነበር፡፡
ስተርሊንግ በዛሬው ዕለት በእንግሊዝ በሚገኝ ፍርድ ቤት በመቅረብ በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ መሆኑን ያመነ ሲሆን፤ በ18 ወራት የቅጣት ገደብ ተፈጻሚ የሚሆን የአንድ ዓመት እስር ተፈርዶበታል፡፡
በዚህም መሰረት ተጫዋቹ በመጪዎቹ 18 ወራት ውስጥ ሌላ ወንጀል ካልፈጸመ ወይም የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ካልጣሰ በስተቀር እስራቱ ተፈጻሚ እንደማይሆን ነው የተገለጸው፡፡
በቴዎድሮስ ሳህለ

😢4