በአንድ ደቂቃ ውስጥ የአልዛይመር ቅድመ-ምልክቶችን የሚለየው ሰው ሠራሽ አስተውሎት
************************
በአሜሪካ ተመራማሪዎች ባካሄዱት ጥናት ሰው ሠራሽ አስተውሎትን በመጠቀም የአልዛይመር ሕመም ቅድመ-ምልክቶችን በአንድ ደቂቃ ውስጥ መለየት እንደሚቻል ተገልጿል።
እንደ ተመራማሪዎቹ ገለጻ፥ ቴክኖሎጂው ሰዎች በቃላት ምርጫቸው፣ በንግግር ፍሰታቸው እና በዓረፍተ ነገር አወቃቀራቸው ላይ የሚያሳዩዋቸውን ለውጦች መሠረት በማድረግ የመለየት አቅም አለው።
በተለምዷዊው መንገድ የሚካሄዱ የአልዛይመር ቅድመ-ምልክት ምርመራዎችን ይተካል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ይህ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ እጅግ ቀላል፣ ፈጣን እና ለአጠቃቀም ምቹ መሆኑም ተነግሮለታል።
እስካሁን በሕክምናው ዘርፍ ለአገልግሎት እየዋሉ ያሉ የአልዛይመር መመርመሪያ ዘዴዎች ረጅም ጊዜ የሚወስዱ ከመሆናቸውም በላይ፣ አልፎ አልፎ በባለሙያዎች የግል ምልከታ ላይ የሚመሠረቱ መሆናቸውን ጥናቱ አመልክቷል።
አልዛይመር ቀስ በቀስ የሰውን ልጅ የማስታወስና የማሰብ ችሎታ በመቀነስ የዕለት ተዕለት የሕይወት ዘይቤን የሚያዛባና በተለይም በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ የሚስተዋል ሕመም ነው።
አዲሱ ቴክኖሎጂ በሽታው አስቀድሞ እንዲታወቅ እና አስፈላጊው ሕክምና በወቅቱ እንዲጀመር ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር የሳይቴክ መረጃ ያመላክታል።
በዓለም ዙሪያ በዚህ ሕመም የሚጠቁ ሰዎች ቁጥራቸው ከፍተኛ እንደሆነ የሚገመት ሲሆን፣ በአሜሪካ ብቻ ዕድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ የሆኑ ከ7 ሚሊዮን በላይ ሕሙማን እንዳሉ ጥናቱ ጠቁሟል።
በልዩ እሸቱ
#EBC #AlzheimersDetection #AI #HealthInnovation #MedicalTechnology

❤2👍2
የአንድ ዶሮ ዕድሜ ምን ያህል ነው?
*******************
በአሜሪካ የተገኘችው ዶሮ 15 ዓመት ከ100 ቀናት ዕድሜ ላይ መገኘቷ በዓለም ላይ በሕይወት ያለች በዕድሜ ትልቋ ዶሮ አስብሏታል።
እንዲህ ያሉትን ያልተለመዱ እና አስደናቂ ጉዳዮችን የሚመዘግበው የዓለም ድንቃድንቆች መዝገብም ይህችን ዶሮ በመዝገቡ ላይ አስፍሯታል።
‘ጌርቲ’ በሚል መጠሪያ የምትታወቀው ይህች ዶሮ በአሜሪካ፣ ቴክሳስ የምትኖረው እና ‘ፐርል’ በሚል መጠሪያ የምትታወቀው ዶሮ ከዚህ ቀደም ይዛው የቆየችውን ክብረ ወሰን በ6 ወራት ማሻሻሏ ተገልጿል።
ባለፉት 15 ዓመታት አራት የዶሮ ትውልዶች ሲያልፉ፣ በቡናማና ጥቁር ነጠብጣብ ላባዎች የደመቀችው ‘ጌርቲ’ ግን ረጅም እድሜ በሕይወት መቆየት የቻለች ብቸኛዋ ዶሮ ሆናለች።
‘ጌርቲ’ አሁን ላይ እንቁላል መጣል ማቆሟን እንዲሁም ዓይኖቿ መታወራቸው በሌሎች ዶሮዎች እንድትጠቃ እንዳደረጋት የዶሮዋ ባለንብረት ፍራንክ ቱሬክ ተናግሯል።
በሀና ምንዳሁን
#GuinnessWorldRecords #oldestchicken #USA #EBC

❤11👍6🤣5
ሪያል ማድሪድ ጆዜ ሞሪንሆን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ
****************
ፖርቹጋላዊው አወዛጋቢ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ሪያል ማድሪድን በድጋሚ ለማሰልጠን ተስማምተዋል።
አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ሪያል ማድሪድን ለሚቀጥሉት ለሶስት አመታት ለማሰልጠን ፊርማቸውን አኑረዋል።
ጆዜ ሞሪንሆን አ ከዚህ ቀደም ከ 2010 እስከ 2013 ሪያል ማድሪድን ማሰልጠናቸው የሚታወስ ሲሆን በ2012 የላሊጋ ዋንጫን ከሪያል ማድሪድ ጋር ማሳካት ችለዋል።
@EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት #ሞሪንሆ #ማድሪድ

❤20👍5😁5
በእግር ኳስ ሜዳ ላይ አስደናቂ ብቃቱን ያሳየው የ3 ዓመት ታዳጊ በፖሊስ ከሜዳ እንዲወጣ መደረጉ መነጋገሪያ ሆኗል
****************
በአሜሪካ ፍሎሪዳ ግዛት ዊንተር ፓርክ በተካሄደ የህፃናት የእግር ኳስ ውድድር ላይ፣ የ3 ዓመቱ ጥቁር አሜሪካዊ ታዳጊ "ኔቫዳ" ባሳየው አስደናቂ የእግር ኳስ ክህሎት ምክንያት ውዝግብ ተነስቶ ፖሊስ እስከመጠራት ደርሷል።
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሚሊዮኖች የተመለከቱት ቪዲዮ እንደሚያሳየው፣ ታዳጊው ኔቫዳ ከእሱ በእድሜ ከፍ ያሉ ተጫዋቾችን በቀላሉ እያለፈ ድንቅ ግቦችን ያስቆጥራል።
የወላጆቹ ገለጻ እንደሚያመላክተው ልጃቸው ከውድድሩ እንዲወጣ የተደረገው በእግር ኳስ ጨዋታ በጣም ጎበዝ በመሆኑ፣ ሌሎችን ልጆች በመብለጡ እና ጥቁር በመሆኑ ምክንያት ብቻ ነው።
የታዳጊው ድንቅ የአጨዋወት ስልት ቪዲዮዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከተለቀቁ በኋላ ትልቅ ትኩረት ስበዋል። በታዳጊው ወላጆች የተለቀቁት ቪዲዮዎች እንደሚያሳዩት አስገራሚው ታዳጊ ተቃራኒ ተጫዋቾችን ምንም ኳስ ሳያስነካ በቀላሉ እያለፈ ጎል ሲያስቆጥር ነው። ነገር ግን ቪዲዮ ላይ ነቫዳ ሌሎችን ልጆች ሲገፈትር አይታይም።
እንደ የወላጆቹ ገለጻ ከሆነ፣ “አዘጋጆቹ በመጀመሪያ ኳስ አያቀብልም አሉ። ነገር ግን ኳሱን ሲያቀብል የሚቀበለው ሰው አልነበረም” ይህ ችሎታው ውድድሩን ባዘጋጁት አካላት ዘንድ ቅሬታን ፈጥሮ ህግ አስከባሪዎችን እስከመጥራት እንዲደርሱ አድርጓቸዋል።
በሌላ በኩል ውድድሩን ያዘጋጀው «አይ 9 ስፖርትስ» ተወካይ በፖሊስ የሰውነት ላይ ካሜራ (Body camera) ቀረጻ ላይ ሲናገር እንደተሰማው፣ የህፃኑን ችሎታ አምኖ መቀበሉን ገልጾ “ልጁ በጣም ጎበዝ ነው፤ ነገር ግን ሌሎች ልጆችን ስለሚገፈትር እንዳይገፋፋ ብንነግረውም ወላጆቹ ሁከት ፈጥረዋል” ብሏል።

❤5😱2