ኢትዮጵያ በ80ኛው የተመድ ጉባኤ ላይ ብሔራዊ ጥቅሞቿን ለማስጠበቅ ንቁ ተሳትፎ ታደርጋለች
+++++++++++++++++
ጋዜጣ_ፕላስ | በቀጣይ ሳምንት በሚካሄደው 80ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ጉባኤ ላይ ብሔራዊ ጥቅሞቿን ለማስከበር ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ እየተዘጋጀች መሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በቀጣይ ሳምንት የሚካሄደውን 80ኛ የተመድ ጉባኤን አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ሰጥቷል፡፡
መግለጫውን የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ መስራች አባል የሆነችበት የተባበሩት መንግስታት 80ኛው ጠቅላላ ጉባዔ በቀጣይ ሳምንት ይካሄዳል፡፡ በዚህም ኢትዮጵያ የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲዋን ለማጠናከር እንደምትጠቀምበት ገልጸዋል፡፡
በጉባኤው ላይ ኢትዮጵያ ለባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ መገንባት ያደረገችው አስተዋጽኦ በማንሳት ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የምታከብረው ይሆናል ብለዋል፡፡
በጉባኤው ላይ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞቿን በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ዙሪያ ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ ዝግጅት እያደረገች መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተካሄዱት የአለም ስርዓተ ምግብ ጉባኤ፣ ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤና የአፍሪካ ካሪቢያን ጉባኤ የተገኙ ውጤቶችን በ80ኛው የተመድ ጉባኤ ላይ ተካፍላለች፡፡
እንዲሁም በአረንጓዴ አሻራና በምግብ ደህንነት ለማረጋገጥ የተሰሩ ስራዎች፣ በታዳሽ ኃይል ዙሪያ ያከናወነቻቸውን ዋና ዋና ተግባራትንና ቀጣይ ለማከናወን ባቀደቻቸው ስራዎች ዙሪያ ትኩረት ሰጥታ እንደምታካፍል ጠቁመዋል፡፡
ከዋናው ጉባኤ ጎን ለጎን አጋርና ወዳጅ የሚያበራክቱ ተጓዳኝ የሁለትዮሽ ውይይቶችንና ምክክሮችን ለማድረግ ስለመዘጋጀቷም ጠቁመዋል፡፡
በሞገስ ጸጋዬ

❤9👍2🥰1👏1
የኦሮሚያ ቱሪዝም ሳምንት ከመስከረም 20 እስከ 22 ይካሄዳል
+++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | 5ኛው የኦሮሚያ ቱሪዝም ሳምንት ከመስከረም 20 እስከ 22 እንደሚካሄድ የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን አስታወቀ።
የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ነጋ ወዳጆ እንደተናገሩት፤ የመድረኩ ዋነኛ ዓለማ የኦሮሚያንና የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሀብቶች ለተቀረው ዓለም በጉልህ ማስተዋወቅ ነው።
በቱሪዝም ሳምንቱ ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት በኦሮሚያ ኢንቨስት ያድርጉ በሚል በተዘጋጀው መድረክ ተሳታፊዎች በክልሉ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ይቀርብላቸዋል ብለዋል።
በመድረኩ ከሀገር ውስጥ የዘርፉ ተዋንያን ባሻገር ከኬንያ፣ ናሚቢያ፣ ሩዋንዳ፣ ብሩንዲ፣ ዩጋንዳና ጅቡቲ የሚመጡ የቱሪዝም አንቀሳቃሾች እንደሚሳተፉ ተነግሯል።
የቱሪዝም ሳምንቱ የኦሮሚያን ሀብቶችና የመስህብ ሥፍራዎች ለማስተዋወቅ አጋዥ የሆኑ የተለያዩ መርሐግብሮች እንደሚኖሩት ገልፀዋል።
ክልሎች፣ የቱሪዝም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተሳታፊ የሚሆኑ ሲሆን፤ በመድረኩ የሚካሄዱ የፓናል ውይይቶች የፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦች የሚነሱበቸው እንደሆኑ አመልክተዋል።
በክብረአብ በላቸው

❤5
“ለብሪክስ የሥነ ጽሁፍ ሽልማት እጩ በመሆን የሀገሬን ስም ማስጠራቴ አስደስቶኛል”
- ደራሲ አበረ አዳሙ
+++++++++++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | ለብሪክስ የሥነ ጽሁፍ ሽልማት እጩ በመሆን የሀገሬ ስም ማስጠራቴ በጣም አስደስቶኛል ሲሉ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ፕሬዝዳንት ደራሲ አበረ አዳሙ ገለጹ፡፡
ደራሲ አበረ በብሪክስ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት በፈጠራ ስራ በተለይም ባህላዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በኢትዮጵያ ውስጥ እስካሁን በሰሯቸው የስነጽሁፍ ስራዎች እጩ የተደረጉ መሆኑን ለጋዜጣ ፕላስ አስታውቀዋል፡፡
በሽልማቱ ላይ ኢትዮጵያን በመወከል ብቸኛው እጩ ሲሆኑ፤ በእጩነት ያቀረባቸውን የብሪክስ ኪነጥበባት ማህበር አመስግነው፤ የሀገሬ ስም በእኔ ምክንያት መጠራቱ በጣም አስደስቶኛል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጥረትና መስዋትነት በመክፈል የብሪክስ ሀገር አባል መሆን የቻለች መሆኑን አንስተው፤ በዚህ ውስጥ መሳተፍ የሀገሪቱን ኪነጥበብ በዓለምአቀፍ ደረጃ ተሰሚነቱ እየጨመረ መምጣቱ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ለብሪክስ የሥነ ጽሁፍ ሽልማት በሀገር ደረጃ በስነጽሁፍ እጩ የሆንበት ዓለም አቀፍ መድረክ መሆኑን ጠቅሰው፤ በሀገርኛ ቋንቋ የሚጽፉ ደራሲያንን በዓለም አቀፍ ደረጃ እጩ አድርጎ ማቅረብ ለሀገራቱና ደራሲያን ትልቅ ትርጉም ያለው ነው ብለዋል፡፡
መድረኩ በተጨማሪም ሀገራችን ጥልቅና ጥንታዊ የስነጽሁፍ ሀብት እንዳላት ዓለም የበለጠ እንዲያውቀው በር የሚከፍት ብሎም በስነጽሁፍ ተወዳዳሪ እንዲሆን የሚያግዝ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በመሆኑም የኢትዮጵያ ህዝብ በመድረኩ ላይ የቀረበው አበረን አዳሙን ሳይሆን ኢትዮጵያ እንደሆነች ግምት ውስጥ በማስገባት ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርግ በአክብሮት እጠይቃለሁ ብለዋል፡፡
መገናኛ ብዙሀንም ያላቸውን ትልቅ አቅም በስነጽሁፉ ላይም ተጽእኖ ማሳደር አለባቸው ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ፕሬዝዳንት እና ደራሲ አበረ አዳሙ በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የህግ አገልግሎት መምሪያ ስራ አስፈጻሚ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።
በማህሌት ብዙነህ

❤3👎2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመስከረም 9 ቀን ጀምሮ ለሁለት አመራሮች ሹመት ሰጡ
1ኛ. ዶ/ር እዮብ ተካልኝ - የብሔራዊ ባንክ ገዥ
2ኛ. ወ/ሮ እናታለም መለስ - በሚኒስትር ማዕረግ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ አድርገው ሾመዋል።

👎3❤1
በህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ተግባር የተሰማሩ 123 ተጠርጣሪዎች የባንክ ሒሳብ ታገደ
+++++++++++
በህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ተግባር ላይ የተሰማሩ 123 ተጠሪጣሪዎች የባንክ ሂሳብ እንዲታገድ መደረጉን የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት አስታውቋል።
ህጋዊና መደበኛ የባንክ ስርዓትን ወደጎን በመተው በህገወጥና ትይዩ ገበያ የውጭ ምንዛሪ ወንጀል ላይ የተሰማሩ አካላት ላይ እርምጃ መወሰዱ እና ሌሎች ላይ ደግሞ የተጠናከረ ክትትል እየተደረገ መሆኑ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት በቅርቡ መግለፁ ይታወሳል።
በዚህም የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ለጋዜጣ ፕላስ በላከው መግለጫ እንዳመላከተው በተለያየ ደረጀ በህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ድርጊት ላይ የተሰማሩ የ123 ተጠርጣሪዎች የገንዘብ እንቅስቃሴ በዛሬው ዕለት ታግዶ የህግ ተጠያቂነት ለማረጋገጥ በሂደት ላይ ይገኛል።
አገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በርካታ ሰው የውጭ ምንዛሪ አገልግሎትን በህጋዊ መንገድ እያካሄደ በመሆኑ በእጅጉ የሚበረታታ መሆኑም ተገልጿል።
ነገር ግን አንዳንድ አካላት አሁንም ከጥቁር ገበያ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ድርጊት ለማትረፍ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆናቸውን በክትትል መረጃዎች መረጋገጡም ተገልጿል።
በተጨማሪም አንዳንድ የባንክ ባለሙያዎች በጥቁር ገበያ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ድርጊት ውስጥ ተሳትፎ ያላቸው መሆኑ የክትትል መረጃው ውጤት የሚያመላክት በመሆኑ ተጨማሪ ምርመራ በመደረግ ላይ ይገኛል ብሏል።
የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመደገፍ ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከሚያከናውናቸው ዋና ዋና ተግባራት መካከል ይህ የወንጀል ድርጊት አንዱና ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑ ይታወቃል።
ስለሆነም የህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ ተግባር እና ሌሎች መሰል ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 780/2005 መሠረት የወንጀል ድርጊቱ ላይ ተሳታፊ በሆኑት ላይ ተገቢው ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ አገልግሎቱ በልዩ ትኩረት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል።

❤7🙏1
“ሪፎርሙ ባይተገበር የግድቡ የመጠናቀቅ ዕድል ዝቅተኛ ነበር”
- ኢንጂነር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር)
++++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | ሪፎርሙ ባይተገበር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመጠናቀቅ ዕድል ዝቅተኛ ነበር ሲሉ ኢንጂነር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ኢንጂነር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) በአዲስ ዘመን ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ለውጡን ተከትሎ የተተገበረው ሪፎርም የተጓተተውንና ቅርቃር ውስጥ በመግባት መቆም ደረጃ ደርሶ የነበረውን የሕዳሴ ግድብ ለማጠናቀቅና ለውጤት ለማብቃት ዋነኛው መሰረት ሆኗል ብለዋል።
በዚህም ቴክኒካሊ የነበሩት የዲዛይን፣ የአቅርቦት እና የኤክስፖርቶች ችግሮች የተፈቱበት መሆኑን አንስተው፤ በኮንትራት አስተዳደርም አቅም ያለው የኮንትራት አስተዳደር በመለየትና ኢትዮጵያ ውስጥ ሠርተው የሚያውቁ ሦስት ኮንትራክተሮች እንዲገቡ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
የቦርድ አወቃቀርና ኃላፊነት ላይ ያሉትም ጉዳዮች እንዲሁ በሪፎርሙ ታይተው የማሻሻል ሥራ ተሠርቶ እንደገና እንዲዋቀሩ ተደርጓል ብለዋል።
በሪፎርሙ የገንዘብና ሀብት ማሰባሰብ እንቅስቃሴው በከፍተኛ ደረጃ እንዲንቀሳቀስ የሕዝብ ተሳትፎ እንዲጎለብት ማድረግ የተቻለበት መሆኑንም አንስተዋል፡፡
ሪፎርሙ ባይተገበር ግድቡ የመጠናቀቅ ዕድሉ እጅግ በጣም ዝቅተኛ እንደነበር አንስተው፤ በአጠቃላይ የሪፎርም ሥራው የነበሩትን ደካማ አሠራሮች በማስተካከል የተሠራና ውጤት ያመጣ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ተስፋ ፈሩ
+++++++
Gazzette Plus ጋዜጣ ፕላስ
#ህዳሴግድብ #ሪፎርም

👍7❤3
የከምባታ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል መሳላ በዱራሜ ከተማ በድምቀት ተከበረ
+++++++++++++
የከምባታ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል የኢትዮጵያውያን ኩራት ታላቁ ህዳሴ ግድብ በተጠናቀቀበት ዓመት መከበሩ መሆኑ የተለየ ያደርገዋል ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አንተነህ ፍቃዱ ገለፁ።
የከምባታ ብሔረሰብ የማንነት ፣ የአብሮነት የመደጋገፍ መገለጫ የመሠላ ዘመን መለወጫ በዓል በዱራሜ ሁለገብ ስታዲየም በድምቀት ተከብሯል።
የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ለአመታት ውጫዊና ውስጣዊ ተፅዕኖዎችን ተቋቁሞ ታላቁ ህዳሴ ግድብን በስኬት ባጠናቀቁበት ማግስት በኩራት የምናከብርበት ዕለት መሆኑ የዘንድሮውን በዓል የተለየ ያደርገዋል ብለዋል።
የከምባታ ብሔረሰብ የአብሮነት የመተሳሳብ የመደጋገፍ ማሳያ የሆነው የመሳላ ዘመን መለወጫ በዓል በአለም ቅርስነት እንዲመዘገብ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር አቶ አረጋ እሸቱ ተናግረዋል።
የቱሪዝም ሚኒስትር ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ በበኩላቸዉ እንደመሳላ ያሉ በዓላት የቱሪዝም መሰህብ እንዲሆኑ ለማድረግ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
መንግስት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በማድረግ ለቱሪዝም እድገት የተለየ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በማህሌት አብዱል

❤6👎1
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ለጦር መኮንኖች ሹመት ሰጡ
++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ| በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅራቢነት ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መስከረም 10 ቀን 2018 ዓ.ም የሚከተሉትን የጦር መኮንኖችን ሹመዋል።
👉 በጄነራልነት ማዕረግ፤
1 ሌ/ጄኔራል አለምሸት ደግፌ
2 ሌ/ጄኔራል ደስታ አብቼ
3 ሌ/ጄኔራል ይመር መኮንን
4 ሌ/ጄኔራል ድሪባ መኮንን
👉 በሌ/ጄኔራል ማዕረግ፤
1 ሜ/ጄኔራል ከፍያለዉ አምዴ ተሰማ
2 ሜ/ጄኔራል ክንዱ ገዙ ተገኝ
👉 በሜ/ጄኔራል ማዕረግ፤
1 ብ/ጄኔራል ታደሰ አመሎ ሲኤሳ
2 ብ/ጄኔራል ቡልቲ ታደሰ ክቲላ
3 ብ/ጄኔራል ኃይሉ እንደሻዉ አቶምሳ
4 ብ/ጄኔራል ዋኘዉ አለሜ አያሌዉ
5 ብ/ጄኔራል ነገራ ሌሊሳ ሙለታ
6 ብ/ጄኔራል ተስፋዬ ረጋሳ አመንቴ
7 ብ/ጄኔራል ደረጀ መገርሳ እሰታ
8 ብ/ጄኔራል በርሄ ገ/መድህን ደመወዝ
9 ብ/ጄኔራል ያሲን ሙሃመድ ሲሳይ
10 ብ/ጄኔራል ዘዉዱ ሰጥአርጌ ደመቀ
11 ብ/ጄኔራል ሚልኬሳ ረጋሳ ኢተፋ
12 ብ/ጄኔራል መለስ መንግስቴ ንረይ
13 ብ/ጄኔራል ተሾመ አናጋዉ አየለ
14 ብ/ጄኔራል አማረ ባህታ በርሄ
15 ብ/ጄኔራል አበባዉ ሰኢድ ይመር
16 ብ/ጄኔራል ደስታ ተመስገን አራጋዉ
17 ብ/ጄኔራል ከማል ኤቢሶ
👉 በብ/ጄኔራልነት ማዕረግ፤
1 ኮ/ል ግርማ ፌዬ ከበደ
2 ኮ/ል ደመቀ መንግስቱ ጽዱ
3 ኮ/ል ተመስገን አስማማው አስናቄ
4 ኮ/ል ሰጠኝ ሊክሳ ኒካ
5 ኮ/ል ጌትነት አዳነ ካሳ
6 ኮ/ል ዮሃንስ መኮንን እጄታ
7 ኮ/ል አባቡ ተሸመ ለገሰ
8 ኮ/ል መኮንን መንግስተ ተበጀ
9 ኮ/ል አሰፋ ደበሌ ነጋዎ
10 ኮ/ል አለሙ ቂጣታ ወረታ
11 ኮ/ል ሙላው በየነ አማኑ
12 ኮ/ል ደጀነ ፀጋዬ ተሻለ
13 ኮ/ል ቾምቤ ወርቁ እሬሶ
14 ኮ/ል አባተ አሰፋ ካሴ
15 ኮ/ል ተሾመ ባጫ ጎሹ
16 ኮ/ል አዲሱ ትርፌሳ በየነ
17 ኮ/ል ዩሃንስ ትኬሳ አያንሳ
18 ኮ/ል ዳኛቸው አያሌው እንግዳ
19 ኮ/ል ፍቃዱ ታደሰ ሰጠኝ
20 ኮ/ል አስናቀ አይተነው መንግስቴ
21 ኮ/ል የሺጥላ ተስፋዬ ደመቀ
22 ኮ/ል መልካሙ ቶማ በየነ
23 ኮ/ል ፈይሳ አየለ ገብረየስ
24 ኮ/ል ጀማል ከድር በዳሳ
25 ኮ/ል ቸርነት መንገሻ ገብሬ
26 ኮ/ል አዘነ ሽመልስ ታደሰ
27 ኮ/ል ጥላሁን ዱጋሳ ጌቱ
28 ኮ/ል ንጉሴ ለውጤ መንግስቱ
29 ኮ/ል ገነት ይማም ታደሰ
30 ኮ/ል ጥላሁን ደምሴ ይርሳው
31 ኮ/ል መሀመድ አህመድ መሀመድ
32 ኮ/ል መስፍን በየነ ኃይሌ
33 ኮ/ል ቡሩክ ሰይፉ ሰርበቶ
34 ኮ/ል መሰረት ጌታቸው የሱነህ
35 ኮ/ል ሁሴን መሃመድ አሕመድ
36 ኮ/ል ግርማ አየለ ጉርሙ
37 ኮ/ል ጣሂር ሳሌህ አሊ
38 ኮ/ል ቦጃ አጋ በዳኔ
39 ኮ/ል አካሉ ካሳ ቦኬ
40 ኮ/ል አዲሱ በድሩ መሃመድ
41 ኮ/ል ቢራራ አበበ ተክሉ
42 ኮ/ል ረሺድ ኢብራሂም አሊይ
43 ኮ/ል ደምሴው አንተነህ ደመላሽ

❤18👍6👏3
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከሰኞ ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚሆን ተገለፀ
+++++++++++++++
ጋዜጣ_ፕላስ |ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን መጎብኘትለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ከፊታችን ሰኞ መስከረም 12 ጀምሮ በመመዝገብ መጎብኘት እንደሚችሉ የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።
የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊ ካሳ የአለም የቱሪዝም ቀንን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንደገለፁት፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመተባባር ለጉብኝት ክፍት ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል።
ህዳሴን መጎብኘት የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል ተመዝገበው መጎብኘት ይችላሉ።
አየር መንገዱ በሳምንት ሁለት ጊዜ ወደ ጉባ በራራ እንደሚያደርግ የገለፁት ሚኒስትሯ በእያንዳንዱ በረራም 50 ጎብኚዎችን ያስተናግዳል ብለዋል።
ኢንቨስት ማድረግ ለሚፈልጉ ባለሃብቶችና የቱሪዝም ዘርፍ ተዋናዮች ግድቡ ከፍተኛ የቱሪዝም መደረሻ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንዲያበረክቱ እድል የሚፈጥር መሆኑንም አስገንዝበዋል።
በዚህ መነሻ ግድቡን መጎብኘት የሚፈልጉ ተቋማት፣ ግለሰቦች ከፊታችን ሰኞ መስከረም 12 ጀምሮ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በተከታዮቹ አድራሻዎች BiruckL@ethiopianairlines.com፤ 0911516125 ወይም SurafelMe@ethiopianairlines.com +2519-04 05 03 22 መመዝገብ እንደሚችሉ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ አስታውቀዋል።
በቅርቡ የተመረቀው ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚሆን መግለጹ ይታወሳል፡፡

❤8👍7