#ገበታ ለትውልድ - ደንቢ ኢኮ ሎጅ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገበታ ለትውልድ ሥራ የመጀመሪያው መዳረሻ የሆነውና በ36.7 ሄክታር የጥብቅ ደንና የተፈጥሮ ኃብት ስጦታ የተዘረጋው ደንቢ ኢኮ ሎጅ በይፋ ተመርቋል።
ኢኮ ሎጁ የሀገራችን የቱሪዝም ዘርፍ ባለፉት ሰባት አመታት ዘላቂነትን፣ የቅርስ ኃብትንና ለዘመናት የሚዘልቅ አለምአቀፍ ደረጃን የመጠበቅ እድል መፍጠርን በማዋሃድ ምን ያህል እንደተለወጠ ማሳያ ነው።
የገበታ ለትውልድ ሥራ አለምአቀፍ ደረጃን የጠበቁ መዳረሻዎችን በማልማት የሀገራችንን እምቅ አቅም ለማውጣት የሚደረገው የሰፊው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ስትራቴጂ አካል ነው።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተጀመረው ይኽ ሥራ በስኬት ከተተገበሩት የገበታ ለሸገርና ገበታ ለሀገር መርሃ ግብሮች የቀጠለና ሥራዎቹን ወደአዳዲስ አካባቢዎች የወሰደ ሲሆን የተፈጥሮ ውበትን፣ የባሕል ቅርስንና ዘላቂ ልምድን በማቀናጀት የተከናወነም ነው።
እነዚህ ሥራዎች የከተማ እና ተፈጥሯዊ መዳረሻዎችን ወደ ሳቢ የቱሪዝም ማዕከልነት የለወጡ ናቸው።
#DineForGenerations #ገበታለትውልድ #PMOEthiopia

❤2👍1
ሀገርዎትን ይወቁ.....
ሶስት የጠቅላይ ሚኒስትር የሥራ ፈለጎች- ገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ። እጅግ ብዙ ሥራ የጀመሩ እና በመጠናቀቅ ላይ ያሉ የአዳዲስ መዳረሻዎች ልማት። ሁሉም የኢትዮጵያን እጅግ ልዩ የተፈጥሮ እና የባሕል ሀብት የሚያሳዩ ስፍራዎች። ይኽቺ ድንቅ ሀገር ለጎብኝዎች አሳይተው የማይጨርሱት የተትረፈረፈ ሀብት ባለቤት ናት። #ሰባትአመታት
#LandOfOrigins #VisitEthiopia #DineForGenerations #ገበታለትውልድ #PMOEthiopia