የትህነግ ቡድን ሕዝብን በርሃብ በመቅጣት ለፖለቲካ መሳሪያነት የመጠቀም ተግባሩን ዳግም በትግራይ ህዝብ ላይ እያሳየ ነው
+++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ - የትህነግ ቡድን ሕዝብን በርሃብ በመቅጣት ለፖለቲካ መሳሪያነት የመጠቀም ተግባሩን ዳግም በትግራይ ሕዝብ ላይ እያሳየ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለማርያም(ዶ/ር) ተናገሩ።
የትህነግ ቡድን የፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል በመጠለያ ማዕከላትና በልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብር የሚያቀርበውን ሰብዓዊ ድጋፍ ለተፈለገው ዓላማ እንዳይውል እያደረገ እንደሚገኝም የሰሞኑ የህፃፅ መጠለያ ጣቢያ ማስረጃ መሆኑን ተናግረዋል።
ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ የትህነግ ቡድን ህገወጥ ቡድን የትግራይን ሕዝብ መሠረታዊ ፍላጎቶችና ሰብዓዊ ቀውሶች ለፖለቲካ ዓላማ የመጠቀም ልማድ አዲስ ክስተት ሳይሆን የቀደመ ታሪኩና መገለጫው ነው።
የትህነግ ቡድን የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ለመሳብ በትግራይ ክልል በመጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ወገኖች የሚቀርብን ሰብዓዊ ድጋፍ በመንጠቅ ድራማዊ ፕሮፓጋንዳ እያስተጋባ መሆኑንም አስረድተዋል።
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም የፌደራል መንግስት በግልጽ መረጃና ማስረጃ የሚልከው ሰብዓዊ ድጋፍ የት እንደገባ መጠየቅ እንዳለበት እና በቡድኑ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ መደናገር እንደሌለበትም አንስተዋል።
የትህነግ ቡድን ሰብዓዊ ድጋፍ ለፖለቲካ ዓላማ ለማዋል የሚያደርገውን ጥረት ሁሉም ሊገነዘበው እንደሚገባም ጠቅሰዋል።
የፌደራል መንግስትም በትግራይ ክልል አስተማማኝና ቀጣይነት ያለው ሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ እያደረገ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
በዚህም በትግራይ ክልል ከባለፈው ጥር 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታኅሳስ ወር 2018 ዓ.ም ድረስ ሁለት ሚሊየን ኩንታል በገንዘብ ሲተምን 32 ቢሊዮን ብር የሚገመት ሰብዓዊ ድጋፍ መሰራጨቱን አስታውቀዋል።
ይህም የፌደራል መንግስት ዜጎች ሰብዓዊ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ያለውን ጠንካራ አቋም በተግባር የሚያረጋግጥ መሆኑንም ነው ያብራሩት።
የትህነግ ቡድን በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፉ ተደራሽ እንዳይሆን በማስተጓጎል፤ ድጋፉን ከችግረኛ ዜጎች በመንጠቅ ዳግም የሕዝብ ጠላትነቱን እያረጋገጠ እንደሚገኝም አብራርተዋል።
ቡድኑ ይህ አልበቃ ብሎት ለእያንዳንዱ ድጋፍ ፈላጊ ዜጋ ከሚሰጥ የፍጆታ ድርሻ ላይ መዋጮ እንደሚሰበስብም ነው የተናገሩት።
ትህነግ በሰብዓዊ ድጋፍ ስም በዜጎች ላይ የሚፈጽመው አስነዋሪ ድርጊት ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ያለውን የተላላኪነት ጥግ በተግባር ያረጋገጠ ነው ብለዋል።
በሌላ በኩል ኮሚሽኑ የድጋፍ ጥሪ ባላቀረበበት ሁኔታ በማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች በቡድንም ሆነ በተናጠል የሚደረጉ የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻ የአሰራር ስርዓትን የጣሱ ህገ-ወጥ አካሄዶች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
በዚህም የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም ሰብዓዊ ድጋፍ በማሰባሰብ ላልተገባ ዓላማ እያዋሉ የሚገኙ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባም አሳስበዋል።

❤9🤗1
THE ETHIOPIAN HERALD DECEMBER 27, 2025
https://e-paper-magazine.press.et/share/newspaper/40xaa6v0fhqkt1tc1ep0er6p47

❤1👍1
የህንድና ኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ አጋርነት አሁን ካለው ‘ጂኦፖለቲካዊ’ እውነታ ጋር የሚጣጣም ነው
++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | የህንድና የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ አጋርነት አሁን ካለው ጂኦፖለቲካዊ እውነታ ጋር የሚጣጣምና በሁለቱ ሀገራት መካከል አዲስ የትብብር ምዕራፍ የከፈተ መሆኑን ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ ገለጹ።
የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ብሩክ ለጋዜጣ ፕላስ በሰጡት ማብራሪያ፤ የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኢትዮጵያ ባደረጉት ጉብኝት ወቅት የተላለፈው ውሳኔ ከፍተኛ ጂኦፖለቲካዊ ክብደት ያለው መሆኑን አስረድተዋል።
ፕሮፌሰር ብሩክ እንደገለጹት፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ከ2 ሺህ ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ጥልቅ ታሪካዊ ትስስር የነበረ ሲሆን፣ በህንድ ውስጥ የተገኙ የኢትዮጵያ ሳንቲሞችና ጥንታዊ የንግድ መዝገቦች ለዚህ ዋነኛ ማሳያ ናቸው።
ኢትዮጵያውያን በደቡባዊና መካከለኛው ህንድ በወታደራዊና በፖለቲካው ዘርፍ ጉልህ ሚና እንደነበራቸው የጠቀሱት ተመራማሪው፤ አንዳንዶቹም በተወሰኑ አካባቢዎች ገዢዎች እስከመሆን ደርሰው እንደነበር ገልጸዋል።
አሁን የታደሰው ስትራቴጂካዊ አጋርነት በእነዚህ ጠንካራ ታሪካዊ መሠረቶች ላይ የተገነባ መሆኑን የገለጹት ፕሮፌሰር ብሩክ፤ ስምምነቱ አሁን ካለው ዓለም አቀፋዊ የኃይል አሰላለፍና ጂኦፖለቲካዊ እውነታ ጋር ፍጹም የሚጣጣም መሆኑን ጠቁመዋል።
ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል አዲስ የሁለትዮሽ ትብብር ምዕራፍ መጀመሩን የሚያመላክት መሆኑን ተናግረዋል።
በማርቆስ በላይ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ኢትዮጵያ #ህንድ #ስትራቴጂካዊ_አጋርነት #ጂኦ_ፖለቲካ #ታሪክ

❤3👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"የኢትዮጵያ 30 በመቶ የውጭ ምንዛሪ ገቢ የሚገኘው ከቡና ነው"-ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | ቡና ለኢትዮጵያ የጀርባ አጥንት መሆኑንና 30 በመቶ የውጭ ምንዛሪ ገቢ የሚገኝበት መሆኑን ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ።
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በቻይና ሁናን ግዛት ጁጆ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘውን የኢትዮጵያን ቡና የማስተዋወቅ ኮንፈረንስ አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።
ፕሬዝዳንቱ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት፣ ኮንፍረንሱ የሁለቱን ሀገራትን የረዥም ጊዜ አጋርነትና የጋራ ትብብርን የሚያንጸባርቅ ነው።
ቡና ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት እንደሆነና 25 በመቶ የሥራ ዘርፍ መሆኑን ጠቅሰው፣ 30 በመቶ የሚሆነው የውጭ ምንዛሪ ገቢ የሚገኘው ከቡና መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ለኢትዮጵያ የቡና ምርት የገበያ እድሎችን ለማስፋት የሚያስችሉ መሰል መድረኮች ወሳኝ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ እና ቻይና በቻይና-አፍሪካ የትብብር ማዕቀፍ መሠረት በግብርና፣ የገጠር አረንጓዴ ልማት፣ ንግድ፣ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ዘርፎች በጋራ እየሰሩ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያና ቻይና ትብብር ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት መሸጋገሩን ጠቅሰው ኮንፍረንሱ ለቻይና-አፍሪካ ንግድ አርአያ ሆኖ ያገለግላል።
በማርቆስ በላይ
#ጋዜጣ_ፕላስ #gazette_plus #ቡና #ቻይና #ኢትዮጵያ

❤2😁2