Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
300 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለምስራቅ አፍሪካ ትልቅ የታሪክ እጥፋት የፈጠረ መሆኑ ተገለጸ
++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ለምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ትስስር ትልቅ የታሪክ እጥፋት የፈጠረ፣ ለኢትዮጵያውያን የጋራ አንድነት ማረጋገጫ የሰጠና የታሪካዊ ድሎች ትልቅ ማሳያ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አስታወቁ።

"ሕዳሴ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል መሪ ሃሳብ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያዘጋጀው "የስለ ኢትዮጵያ" መድረክ በጉባ እየተካሄደ ይገኛል።

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በመድረኩ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት፤ ግድቡ የሕብረ ብሔራዊ አብሮነት ማጠናከሪያ፣ የብልጽግና አይቀሬነት ማሳያና የኢትዮጵያ የማንሰራራት ምልክት ነው።

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ከመሠረት ድንጋይ አቀማመጥ ጀምሮ በርካታ የውስጥና የውጭ ፈተናዎችን ማለፉን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነትና በሕዝቡ የተቀናጀ ዲፕሎማሲያዊና የልማት ርብርብ ፕሮጀክቱ እውን መሆኑን ገልጸዋል።

ግድቡ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው አቅም ታላላቅ ሥራዎችን መሥራት እንደሚችሉ ለዓለም ያረጋገጡበት "የመሻገር ተምሳሌት" መሆኑንም አክለዋል።

በሌላ በኩል በግድቡ አማካኝነት የተፈጠረው "የንጋት ሐይቅ" ለክልሉ ተጨማሪ የቱሪስትና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ይዞ መምጣቱን ርዕሰ መስተዳደር አሻድሊ ጠቁመዋል።

ክልሉ ዘርፈ ብዙ የተፈጥሮ ሀብት ያለው በመሆኑ ባለሀብቶች ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በዚህ ስፍራ እንዲህ አይነት ፕሮግራም ማዘጋጀቱም ሁለት ጠቀሜታ እንዳለው የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በአንድ በኩል ክልሉን ለማሳደግ ትልቅ አቅም አለው፣ በሌላ በኩል ደግሞ ስለህዳሴ ግድብ አዳዲስ ሀሳቦች እንዲመነጩ እድል ይፈጥራል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ መሳፍንት ተፈራ በበኩላቸው፤ ድርጅቱ ባለፉት ሦስት ዓመታት ከ22 በላይ "የስለ ኢትዮጵያ" መድረኮችን በማዘጋጀት በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ የሐሳብ ልውውጥ እንዲደረግ ማድረጉን ገልጸዋል።

በዛሬው የጉባ መድረክም በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በርካታ ጥናታዊ ጽሑፎችና የውይይት ሐሳቦች እንደሚቀርቡ አስታውቀዋል።

#ጋዜጣ_ፕላስ #ሕዳሴ_ግድብ #ጉባ #ቤኒሻንጉል_ጉምዝ #ኢትዮጵያ #ስለ_ኢትዮጵያ
7
“ዓባይ ማደሪያው ጉባ መሆኑ በተግባር የታየበት የታሪክ ምዕራፍ ተፈጥሯል”

- አቶ ፍቃዱ ፀጋ
የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር
++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | “ዓባይ ማደሪያ የለውም” የሚለው የቀድሞ ትርክት ተቀይሮ የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዓባይ ማደሪያው ጉባ መሆኑን ያረጋገጠበት የታሪክ እጥፋት መፈጠሩን የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ጸጋዬ ተናገሩ።

በጉባ እየተካሄደ ባለው የ"ስለ ኢትዮጵያ" መድረክ ላይ የውይይት መሪ የነበሩት የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፍቃዱ ጸጋዬ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በሕዳሴው ግድብ አማካኝነት በዓባይ ወንዝ ላይ የነበሩ የቆዩና ተስፋ አስቆራጭ ትርክቶችን መቀየር ችላለች።

ዓባይ ማደሪያው ጉባ መሆኑ በተግባር የታየበት የታሪክ ምዕራፍ ተፈጥሯል ያሉት ዳይሬክተሩ፤ ግድቡ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ምልክት መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ "የውኃ ማማ" ናት የሚለው ትርክት ሆን ተብሎ የተፈጠረና ሀገሪቱ ያላትን የዝናብ ውኃ ወዲያው ወደ ታች እንደሚፈስ የማይገልጽ መሆኑን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

አሁንም ቢሆን የኤሌክትሪክ ተደራሽነታችን 54 በመቶ ብቻ መሆኑን በመጥቀስ፣ 100 በመቶ ተደራሽነት ካላት ግብፅ ጋር ሲነጻጸር ግድቡ ለሀገራዊ ፍላጎታችን ያለውን ወሳኝነት አስገንዝበዋል።

ዓባይ ለኢትዮጵያ ከኃይል ማመንጫነት ባለፈ በቱሪዝም፣ በኢንዱስትሪና በምግብ ዋስትና ዘርፍ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እንዳለው የገለጹት አቶ ፍቃዱ፤ በአሁኑ ወቅት በግድቡ አማካኝነት በተፈጠረው "የንጋት ሐይቅ" በቀን እስከ 14 ሺህ ኪሎ ግራም ዓሣ እየተመረተ መሆኑን እንደ አንድ ትልቅ ስኬት ጠቅሰዋል።

ይህም ሀገሪቱ ከነበረችበት የፈተና እና የጫና ወቅት ወጥታ በቁርጠኛ መሪዎችና በሕዝብ ትብብር ውጤት ማስመዝገቧን የሚያሳይ ነው ብለዋል።

በጋዜጣ ፕላስ ሪፖርተር
#ጋዜጣ_ፕላስ #ታላቁ_የሕዳሴ_ግድብ #ዐባይ #ጉባ #ፖሊሲ_ጥናት #ኢትዮጵያ #ንጋት_ሐይቅ #ስለኢትዮጵያ
የትህነግ ቡድን ሕዝብን በርሃብ በመቅጣት ለፖለቲካ መሳሪያነት የመጠቀም ተግባሩን ዳግም በትግራይ ህዝብ ላይ እያሳየ ነው
+++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ - የትህነግ ቡድን ሕዝብን በርሃብ በመቅጣት ለፖለቲካ መሳሪያነት የመጠቀም ተግባሩን ዳግም በትግራይ ሕዝብ ላይ እያሳየ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለማርያም(ዶ/ር) ተናገሩ።

የትህነግ ቡድን የፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል በመጠለያ ማዕከላትና በልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብር የሚያቀርበውን ሰብዓዊ ድጋፍ ለተፈለገው ዓላማ እንዳይውል እያደረገ እንደሚገኝም የሰሞኑ የህፃፅ መጠለያ ጣቢያ ማስረጃ መሆኑን ተናግረዋል።

ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ የትህነግ ቡድን ህገወጥ ቡድን የትግራይን ሕዝብ መሠረታዊ ፍላጎቶችና ሰብዓዊ ቀውሶች ለፖለቲካ ዓላማ የመጠቀም ልማድ አዲስ ክስተት ሳይሆን የቀደመ ታሪኩና መገለጫው ነው።

የትህነግ ቡድን የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ለመሳብ በትግራይ ክልል በመጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ወገኖች የሚቀርብን ሰብዓዊ ድጋፍ በመንጠቅ ድራማዊ ፕሮፓጋንዳ እያስተጋባ መሆኑንም አስረድተዋል።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም የፌደራል መንግስት በግልጽ መረጃና ማስረጃ የሚልከው ሰብዓዊ ድጋፍ የት እንደገባ መጠየቅ እንዳለበት እና በቡድኑ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ መደናገር እንደሌለበትም አንስተዋል።

የትህነግ ቡድን ሰብዓዊ ድጋፍ ለፖለቲካ ዓላማ ለማዋል የሚያደርገውን ጥረት ሁሉም ሊገነዘበው እንደሚገባም ጠቅሰዋል።

የፌደራል መንግስትም በትግራይ ክልል አስተማማኝና ቀጣይነት ያለው ሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ እያደረገ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

በዚህም በትግራይ ክልል ከባለፈው ጥር 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታኅሳስ ወር 2018 ዓ.ም ድረስ ሁለት ሚሊየን ኩንታል በገንዘብ ሲተምን 32 ቢሊዮን ብር የሚገመት ሰብዓዊ ድጋፍ መሰራጨቱን አስታውቀዋል።

ይህም የፌደራል መንግስት ዜጎች ሰብዓዊ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ያለውን ጠንካራ አቋም በተግባር የሚያረጋግጥ መሆኑንም ነው ያብራሩት።

የትህነግ ቡድን በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፉ ተደራሽ እንዳይሆን በማስተጓጎል፤ ድጋፉን ከችግረኛ ዜጎች በመንጠቅ ዳግም የሕዝብ ጠላትነቱን እያረጋገጠ እንደሚገኝም አብራርተዋል።

ቡድኑ ይህ አልበቃ ብሎት ለእያንዳንዱ ድጋፍ ፈላጊ ዜጋ ከሚሰጥ የፍጆታ ድርሻ ላይ መዋጮ እንደሚሰበስብም ነው የተናገሩት።

ትህነግ በሰብዓዊ ድጋፍ ስም በዜጎች ላይ የሚፈጽመው አስነዋሪ ድርጊት ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ያለውን የተላላኪነት ጥግ በተግባር ያረጋገጠ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል ኮሚሽኑ የድጋፍ ጥሪ ባላቀረበበት ሁኔታ በማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች በቡድንም ሆነ በተናጠል የሚደረጉ የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻ የአሰራር ስርዓትን የጣሱ ህገ-ወጥ አካሄዶች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

በዚህም የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም ሰብዓዊ ድጋፍ በማሰባሰብ ላልተገባ ዓላማ እያዋሉ የሚገኙ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባም አሳስበዋል።
9🤗1
#የስራ_ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
2
የህንድና ኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ አጋርነት አሁን ካለው ‘ጂኦፖለቲካዊ’ እውነታ ጋር የሚጣጣም ነው
++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | የህንድና የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ አጋርነት አሁን ካለው ጂኦፖለቲካዊ እውነታ ጋር የሚጣጣምና በሁለቱ ሀገራት መካከል አዲስ የትብብር ምዕራፍ የከፈተ መሆኑን ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ ገለጹ።

የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ብሩክ ለጋዜጣ ፕላስ በሰጡት ማብራሪያ፤ የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኢትዮጵያ ባደረጉት ጉብኝት ወቅት የተላለፈው ውሳኔ ከፍተኛ ጂኦፖለቲካዊ ክብደት ያለው መሆኑን አስረድተዋል።

ፕሮፌሰር ብሩክ እንደገለጹት፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ከ2 ሺህ ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ጥልቅ ታሪካዊ ትስስር የነበረ ሲሆን፣ በህንድ ውስጥ የተገኙ የኢትዮጵያ ሳንቲሞችና ጥንታዊ የንግድ መዝገቦች ለዚህ ዋነኛ ማሳያ ናቸው።

ኢትዮጵያውያን በደቡባዊና መካከለኛው ህንድ በወታደራዊና በፖለቲካው ዘርፍ ጉልህ ሚና እንደነበራቸው የጠቀሱት ተመራማሪው፤ አንዳንዶቹም በተወሰኑ አካባቢዎች ገዢዎች እስከመሆን ደርሰው እንደነበር ገልጸዋል።

አሁን የታደሰው ስትራቴጂካዊ አጋርነት በእነዚህ ጠንካራ ታሪካዊ መሠረቶች ላይ የተገነባ መሆኑን የገለጹት ፕሮፌሰር ብሩክ፤ ስምምነቱ አሁን ካለው ዓለም አቀፋዊ የኃይል አሰላለፍና ጂኦፖለቲካዊ እውነታ ጋር ፍጹም የሚጣጣም መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል አዲስ የሁለትዮሽ ትብብር ምዕራፍ መጀመሩን የሚያመላክት መሆኑን ተናግረዋል።

በማርቆስ በላይ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ኢትዮጵያ #ህንድ #ስትራቴጂካዊ_አጋርነት #ጂኦ_ፖለቲካ #ታሪክ
2👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በቻይና መካሄድ የጀመረውን የኢትዮጵያን ቡና የማስተዋወቅ ኮንፈረንስ አስመልክተው ያስተላለፉት መልዕክት‼️
#Ethiopia #China #coffee