Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ዛሬ የኬንያ ፕሬዝደንት ዊልያም ሳሞይ ሩቶን ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ተቀብያለሁ።

ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ጥልቅ፣ ታሪካዊና ወንድማዊ ግንኙነት የሚያንፀባርቅ ነው።

በውይይታችን የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ የተለዋወጥን ሲሆን ይኽም በሰላምና መረጋጋት፣ ንግግር ብሎም በአፍሪካ መር መፍትሔዎች ላይ ያለንን የወል ጽኑ አቋም የሚያሳይ ነበር።

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
👍103
90ኛው የኢትዮጵያ አየር ኃይል የምሥረታ በዓል ዓለም አቀፍ ይዘት ባላቸው ዝግጅቶች ይከናወናል
++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | 90ኛው ዓመት የኢትዮጵያ አየር ኃይል የምሥረታ በዓል "የኢትዮጵያ አየር ኃይል የነፃነትና የአንድነት ምልክት" በሚል መሪ ቃል ከጥር 15 እስከ ጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም በተለያዩ ታላላቅ መርሃ ግብሮች እንደሚከበር ተገለጸ።

አየር ኃይሉ የምሥረታ በዓሉን አስመልክቶ በቢሾፍቱ ከተማ ዓለም አቀፍ የጎዳና ላይ ሩጫ በማካሄድ ዝግጅቱን የጀመረ ሲሆን፤ ዋናው የበዓሉ ኩነት በሚከበርባቸው ቀናትም ዓለም አቀፍ ይዘት ያላቸው ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ይከናወናሉ።

በዚሁ መሠረት "የአንበሶች ሰማይ ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ፣ የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ፣ የሩሲያ፣ የሞሮኮ እና የቼክ ሪፐብሊክ አየር ኃይሎች በጋራ የሚሳተፉበት "የጥቁር አንበሳ የአየር ትርኢት 2026" በድምቀት ይካሄዳል።

በተጨማሪም "የወደፊቱን የአቪዬሽን አቅም በጋራ እንገንባ" በሚል መሪ ቃል የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ታላላቅ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት የአቪዬሽን ቴክኖሎጂ ኤክስፖ 2026 እንደሚሰናዳ ታውቋል።

በሌላ በኩል ከ38 በላይ የአፍሪካ ሀገራት የአየር ኃይል አዛዦችና ባለሙያዎች የሚሳተፉበት 3ኛው "ፊውቸር አፍሪካ አየር ኃይሎች ፎረም" በተመሳሳይ ወቅት የሚካሄድ ሲሆን፤ ይህም ቀጣናዊ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

የተቋሙን የታሪክ ጉዞና የበዓሉን ዝርዝር መረጃዎች ለሕዝብ ተደራሽ ለማድረግ 'etaf90years.com' የተሰኘ ድረ-ገጽ የበለጸገ ሲሆን፤ ፍላጎት ያላቸው ዜጎች በድረገጹ አማካኝነት የመግቢያ ትኬት መግዛትና ኩነቶቹን መከታተል እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

በክብረአብ በላቸው
#ጋዜጣ_ፕላስ #የኢትዮጵያ_አየር_ኃይል #አቪዬሽን #ጥቁር_አንበሳ
#ኢትዮጵያ
3
በትግራይ ክልል ለተፈናቃዮች ከ257 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ሰብዓዊ እርዳታ ተሰራጨ
++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ዞን አስገደ ወረዳ "ህፃፅ" ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ257 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ሰብዓዊ እርዳታ መሰራጨቱን የኢፌድሪ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል የተፈናቃዮችን የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት በተመለከተ ባወጣው መግለጫ፤ በአሁኑ ወቅት ሰብዓዊ እርዳታ እየደረሳቸው አይደለም ተብሎ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የቀረበው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ገልጿል።

ከመስከረም እስከ ታኅሣሥ 2018 ዓ.ም ባሉት ወራት ውስጥ ለተፈናቃዮቹ ያልተቋረጠ የምግብ እርዳታ ሲደረግ መቆየቱንም ኮሚሽኑ አብራርቷል።

በዚህም መሠረት ባለፉት አራት ወራት ውስጥ 11 ሺህ 406 ኩንታል ስንዴ፣ ማሽላ፣ ጥራጥሬ እንዲሁም የምግብ ዘይት ለተፈናቃዮቹ መሰራጨቱን ኮሚሽኑ በመግለጫው ጠቁሟል።

የእርዳታ አሰጣጡም በመስከረም፣ ጥቅምት፣ ኅዳር እና ታኅሣሥ ወራት በቋሚነት በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ተደራሽ መደረጉን መግለጫው አመልክቷል።

ኮሚሽኑ ለተፈናቃዮች የሚላከው እርዳታ ለታለመለት ዓላማ መዋሉን የማረጋገጥ ኃላፊነት የክልሉና የአካባቢው ጊዜያዊ አስተዳደር መሆኑን አሳስቦ፤ ተጨማሪ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ የሚያስፈልግ ከሆነ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

በልጅዓለም ፍቅሬ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ትግራይ #ሰብዓዊ_እርዳታ #አደጋ_ሥጋት
#ኢትዮጵያ #ህፃፅ
8
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለመላው ዓለም ክርስቲያኖች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ሚድያቸው ባስተላለፉት መልዕክት መልካም የገና በዓል ለዓለም አቀፍ ቤተሰቦቻችን ብለዋል።

ይህ ወቅት የሚያስታውሰን መልካምነት ድንበር ተሻጋሪ መሆኑን እና ተስፋን በጋራ መገንባት እንደምንችል ነው ሲሉም አስፍረዋል።

Gazette Plus ጋዜጣ ፕላስ
👍4
የኢትዮጵያ ወደቀይ ባሕር መውጣት ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ
+++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | የኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባሕር መውጣት ለአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ሰላምና መረጋጋት ወሳኝ መሆኑን የማኅበራዊና ፖለቲካዊ ተግባቦት ተመራማሪና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአማካሪ ኮሚቴ አባል ከማል ሃሺ ሞሐሙድ ገለጹ።

ከማል ሃሺ ሞሐሙድ እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤት መሆን የቀጠናው ሀገራት በአብሮነት የመልማት ፍላጎታቸውን ከማጠናከሩ ባሻገር ጸጥታውን ለማረጋገጥ ያለው ሚና ከፍተኛ ነው።

ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ከድንበር ባለፈ ሕዝብን፣ ቋንቋንና ባህልን እንደምትጋራ ጠቁመው፤ በመሆኑም ያለውን ሀብት በስምምነት በመጠቀም ቀጠናውን ማልማት እንጂ በንትርክ ውስጥ መግባት አካባቢውን ከማደህየት ውጪ ፋይዳ እንደሌለው ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ያላት ወታደራዊ ልምድ ለቀጠናው ሰላም መረጋገጥ ትልቅ አቅም መሆኑን የጠቀሱት ተመራማሪው፣ የባሕር ኃይል በማሰማራት የቀጠናውን ደኅንነት መጠበቅ ለሀገሪቱ አዲስ ነገር አለመሆኑን አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ በባሕር በር ላይ መገኘት ለቀጠናው መፍትሔ መሆን እንደሚችል አመላክተዋል።

ያደጉና ግዙፍ ኃይል ያላቸው ሀገራት ማኅበር ፈጥረው ጫናን እየቀነሱ ባሉበት በዚህ ወቅት የአፍሪካ ቀንድ ሀገራትም አንድ ሊሆኑ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የባሕር በር የኢኮኖሚንና የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር ወሳኝ መሆኑን የገለጹት ከማል ሃሺ ሞሐሙድ፤ የኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባሕር መውጣት ለአካባቢው በረከት እንጂ ቁጣ አለመሆኑንና ታሪክም ኢትዮጵያ ጠንካራ የጸጥታ መዋቅር ያላት የጀግኖች ሀገር መሆኑን እንደሚመሰክር አክለው ገልጸዋል።

በልጅዓለም ፍቅሬ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ቀይ_ባሕር #ኢትዮጵያ #አፍሪካ_ቀንድ #ሰላምና_ረጋጋት
10
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለምስራቅ አፍሪካ ትልቅ የታሪክ እጥፋት የፈጠረ መሆኑ ተገለጸ
++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ለምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ትስስር ትልቅ የታሪክ እጥፋት የፈጠረ፣ ለኢትዮጵያውያን የጋራ አንድነት ማረጋገጫ የሰጠና የታሪካዊ ድሎች ትልቅ ማሳያ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አስታወቁ።

"ሕዳሴ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል መሪ ሃሳብ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያዘጋጀው "የስለ ኢትዮጵያ" መድረክ በጉባ እየተካሄደ ይገኛል።

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በመድረኩ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት፤ ግድቡ የሕብረ ብሔራዊ አብሮነት ማጠናከሪያ፣ የብልጽግና አይቀሬነት ማሳያና የኢትዮጵያ የማንሰራራት ምልክት ነው።

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ከመሠረት ድንጋይ አቀማመጥ ጀምሮ በርካታ የውስጥና የውጭ ፈተናዎችን ማለፉን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነትና በሕዝቡ የተቀናጀ ዲፕሎማሲያዊና የልማት ርብርብ ፕሮጀክቱ እውን መሆኑን ገልጸዋል።

ግድቡ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው አቅም ታላላቅ ሥራዎችን መሥራት እንደሚችሉ ለዓለም ያረጋገጡበት "የመሻገር ተምሳሌት" መሆኑንም አክለዋል።

በሌላ በኩል በግድቡ አማካኝነት የተፈጠረው "የንጋት ሐይቅ" ለክልሉ ተጨማሪ የቱሪስትና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ይዞ መምጣቱን ርዕሰ መስተዳደር አሻድሊ ጠቁመዋል።

ክልሉ ዘርፈ ብዙ የተፈጥሮ ሀብት ያለው በመሆኑ ባለሀብቶች ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በዚህ ስፍራ እንዲህ አይነት ፕሮግራም ማዘጋጀቱም ሁለት ጠቀሜታ እንዳለው የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በአንድ በኩል ክልሉን ለማሳደግ ትልቅ አቅም አለው፣ በሌላ በኩል ደግሞ ስለህዳሴ ግድብ አዳዲስ ሀሳቦች እንዲመነጩ እድል ይፈጥራል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ መሳፍንት ተፈራ በበኩላቸው፤ ድርጅቱ ባለፉት ሦስት ዓመታት ከ22 በላይ "የስለ ኢትዮጵያ" መድረኮችን በማዘጋጀት በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ የሐሳብ ልውውጥ እንዲደረግ ማድረጉን ገልጸዋል።

በዛሬው የጉባ መድረክም በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በርካታ ጥናታዊ ጽሑፎችና የውይይት ሐሳቦች እንደሚቀርቡ አስታውቀዋል።

#ጋዜጣ_ፕላስ #ሕዳሴ_ግድብ #ጉባ #ቤኒሻንጉል_ጉምዝ #ኢትዮጵያ #ስለ_ኢትዮጵያ
8
“ዓባይ ማደሪያው ጉባ መሆኑ በተግባር የታየበት የታሪክ ምዕራፍ ተፈጥሯል”

- አቶ ፍቃዱ ፀጋ
የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር
++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | “ዓባይ ማደሪያ የለውም” የሚለው የቀድሞ ትርክት ተቀይሮ የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዓባይ ማደሪያው ጉባ መሆኑን ያረጋገጠበት የታሪክ እጥፋት መፈጠሩን የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ጸጋዬ ተናገሩ።

በጉባ እየተካሄደ ባለው የ"ስለ ኢትዮጵያ" መድረክ ላይ የውይይት መሪ የነበሩት የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፍቃዱ ጸጋዬ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በሕዳሴው ግድብ አማካኝነት በዓባይ ወንዝ ላይ የነበሩ የቆዩና ተስፋ አስቆራጭ ትርክቶችን መቀየር ችላለች።

ዓባይ ማደሪያው ጉባ መሆኑ በተግባር የታየበት የታሪክ ምዕራፍ ተፈጥሯል ያሉት ዳይሬክተሩ፤ ግድቡ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ምልክት መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ "የውኃ ማማ" ናት የሚለው ትርክት ሆን ተብሎ የተፈጠረና ሀገሪቱ ያላትን የዝናብ ውኃ ወዲያው ወደ ታች እንደሚፈስ የማይገልጽ መሆኑን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

አሁንም ቢሆን የኤሌክትሪክ ተደራሽነታችን 54 በመቶ ብቻ መሆኑን በመጥቀስ፣ 100 በመቶ ተደራሽነት ካላት ግብፅ ጋር ሲነጻጸር ግድቡ ለሀገራዊ ፍላጎታችን ያለውን ወሳኝነት አስገንዝበዋል።

ዓባይ ለኢትዮጵያ ከኃይል ማመንጫነት ባለፈ በቱሪዝም፣ በኢንዱስትሪና በምግብ ዋስትና ዘርፍ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እንዳለው የገለጹት አቶ ፍቃዱ፤ በአሁኑ ወቅት በግድቡ አማካኝነት በተፈጠረው "የንጋት ሐይቅ" በቀን እስከ 14 ሺህ ኪሎ ግራም ዓሣ እየተመረተ መሆኑን እንደ አንድ ትልቅ ስኬት ጠቅሰዋል።

ይህም ሀገሪቱ ከነበረችበት የፈተና እና የጫና ወቅት ወጥታ በቁርጠኛ መሪዎችና በሕዝብ ትብብር ውጤት ማስመዝገቧን የሚያሳይ ነው ብለዋል።

በጋዜጣ ፕላስ ሪፖርተር
#ጋዜጣ_ፕላስ #ታላቁ_የሕዳሴ_ግድብ #ዐባይ #ጉባ #ፖሊሲ_ጥናት #ኢትዮጵያ #ንጋት_ሐይቅ #ስለኢትዮጵያ