Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
300 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በአዲስ አበባ የደመራ በዓል የታደሙ የውጭ ሀገራት ዜጎች‼️
6
"በቢሾፍቱ የአየር ማረፊያ ግንባታ የተነሱ ገበሬዎች የመኖሪያ ቤት ግንባታ በያዝነው ወር ይጠናቀቃል"

- አቶ መስፍን ጣሰው
+++++++++++++++++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | በቢሾፍቱ የአየር ማረፊያ ግንባታ የተነሱ ገበሬዎች የመኖሪያ ቤት ግንባታ በዚህ ወር ይጠናቀቃል ሲሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ገለፁ።

አቶ መስፍን ጣሰው ከዘመን ኢኮኖሚ ጋር ባደረጉት ቆይታ አዲሱ ኤርፖርት ሊገነባ የሚችልበትን ቦታ በፈረንሳይ ኩባንያ እንዲጠና ተደርጓል።

ጥናቱም ቢሾፍቱ አጠገብ አቡሴራ የሚባል ቦታ ከሁሉም የተሻለ ቦታ እንደሆነ የጠቆመ ሲሆን፤ የመጀመሪያ ደረጃ ማስተር ፕላንና ያዋጭነት ጥናትም ተሰርቶለታል ብለዋል።

አዋጭነቱ ከተረጋገጠ በኋላ በኮቪድ ምክንያት ፕሮጀክቱ መቀዛቀዙን ገልጸው፤ ከዚያ ግን ጥናቶቹ ተከልሰው ወደ ስራ ተገብቷል ነው ያሉት።

እንደ አቶ መስፍን ገለፃ ግንባታው በሚከናወንበት አካባቢ ያሉ ገበሬዎች ሲነሱ ዳግም ማቋቋም እንደሚገባ በማመን ከቢሾፍቱ አስተዳደር ጋር በመነጋገር ምን አይነት ቤት እና ሥራ ይገባቸዋል ተብሎ ግንባታ ተጀምሯል። ግንባታውም በያዝነው መስከረም ወር ይጠናቀቃል።

ሰዎቹም ወደ አዲሱ መኖሪያቸውና አዲሱ ሥራቸው የሚዘዋወሩ መሆኑን ገልፀዋል።

የኤርፖርት ግንባታ የሚካሄድበትን ቦታ ከክልሉ መንግሥት መረከባቸውንና ገበሬዎች አዝመራቸውን እንዳነሱ ሕዳር መጨረሻ አካባቢ አዲሱ ኤርፖርት ግንባታው እንደሚጀመርም ጠቁመዋል።
+++++++++++++++++++++++

@ጋዜጣ_ፕላስ
#የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ
21
የማዕድን አልሚዎችን የነዳጅ እጥረት ለመቅረፍ የሚያስችል አሠራር ሊዘረጋ ነው
+++++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | ማዕድን አልሚዎች ያለባቸውን የነዳጅ እጥረት ለመቅረፍ በቀጥታ ነዳጅ እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሠራ እንደሚገኝ ማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ።

ጉዳዩ በተለይ ልዩ አነስተኛ ማዕድን አልሚዎችን የሚመለከት መሆኑም ተነግሯል።

የማዕድን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ በ2017 በጀት ዓመት ከፍተኛ የማዕድን ምርት የተገኘው ከልዩ አነስተኛ ማዕድን አልሚዎች ነው።

ይህንን ለማበረታታት በተያዘው ዓመት አልሚዎቹ ያለባቸውን የነዳጅ እጥረት ለመቅረፍ አሠራር ይዘረጋል ብለዋል።

አሠራሩ አምራቾቹ በቀጥታ ነዳጅ እንዲያገኙ የሚያስችል እንደሚሆን ገልጸዋል።

ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሠራ እንደሚገኝ ጠቁመው፤ በውጤቱ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚገቡ ማዕድናት በሀገር ውስጥ መተካት እና የውጭ ምንዛሪ ማዳን እንደሚቻል አመላክተዋል።

በዓመለወርቅ ከበደ

+++++++++++++++++

Gazette Plus ጋዜጣ ፕላስ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ማዕድን #ኢንዱስትሪ
4
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና አደም ፋራህን ጨምሮ ከከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር ጂግጂጋ ከተማ ገብተዋል። በጉብኝታቸውም በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ይጎበኛሉ። #PMOEthiopia
12👍4👎2