Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በዓለም ከፍተኛ የሰሊጥ አምራች ሀገራት
++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | በዓለም አቀፍ ደረጃ የሰሊጥ ዘር ኢንደስትሪ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ ሲሆን ሀንድ፣ ቻይና፣ሱዳን፣ ማይናማር፣ታንዛኒያና ኢትዮጵያ ከፍተኛ የገበያ ድርሻ ያላቸው ሀገራት ናቸው።

ኢትዮጵያ ስድስት በመቶ የሚሆነው የዓለም የሰሊጥ ዘር ገበያ ድርሻ ይዛ ምርቷን ወደ አፍሪካ፣ ኤዢያና ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት በስፋት የምትልክ ሲሆን ሰሊጥ ሀገሪቷ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ከምታገኝባቸ የግብርና ምርት ዝርዝሮች ዉስጥ ይካተታል።

በመስከረም ሰይፉ
+++++++++++
Gazzete plus ጋዜጣ ፕላስ
#ግብርና #ሰሊጥ
6👍2
አየር መንገዱ ባለሙያዎችን እያስኮበለሉ ላስቸገሩት ሀገራት ቴክኒሽያኖችን አሠልጥኖ ሊሰጥ ነው
+++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለሙያዎችን እያስኮበለሉ ላስቸገሩት ሀገራት ቴክኒሽያኖችን አሠልጥኖ ሊሰጥ መሆኑን ገለጸ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በኢፕድ ከምትዘጋጀው ዘመን ኢኮኖሚ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ በተለይ የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቴክኒሽያኖችን በገንዘብ እያስኮበለሉ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድን ቴክኒሽያኖች በጣም ብዙ ገንዘብ እየከፈሉ የሚወስዱ የመካከለኛው ምስራቅ አካባቢ አየር መንገዶች እንዳሉ ጠቅሰው፤ የቴክኒሽያኖቹ መኮብለል በአየር መንገዱ ላይ ፈተና ፈጥሯል ብለዋል፡፡

የቴክኒሽያኖችን ኩብለላ ለማስቀረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ እያስኮበለሉ ከሚወስዷቸው ሀገራት አየር መንገዶች ጋር ንግግር መጀመሩን ተናግረዋል። በዚህም አስኮብላዮቹ የሚፈልጉትን ያህል ቴክኒሽያን አሰልጥነን እንሰጣለን ብለዋል፡፡

በተለይም ለመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት አየር መንገዶች ወደ 1000 የሚሆኑ ባለሙያዎችን አስተምሮ ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን አብራርተዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ አየር መንገዱ ከሁለት ሺህ 500 በላይ ቴክኒሽያኖች እንዳሉትም አያይዘው ገልጸዋል፡፡

#አየርመንገድ #ስልጠና
12👍1👏1😁1
በሚቀጥሉት ቀናት በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል
+++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | በሚቀጥሉት ቀናት በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢኒስቲትዩት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢኒስቲትዩት ከመስከረም 11 ቀን እስከ መሥከረም 20 ቀን 2018 ዓ.ም የሚኖረውን የአየር ሁኔታ አዝማሚያ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በላከው መግለጫ አስታውቋል።

በዚህም በሚቀጥሉት ቀናት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ቀጣይነት እንደሚኖራቸው ተመላክቷል፡፡

በመሆኑም በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ እንዲሁም በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል።

በተጨማሪም በፀሐይ ሀይል ታግዞ ከሚጠናከሩ የደመና ክምችቶች ላይ በመነሳት በምዕራብ፣ በመካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ አልፎ አልፎ በሚኖሩት ቀናት በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው ተጠቁሟል።

በሌላ በኩል በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከቀን ወደ ቀን የደመና ሽፋን እንደሚጨምር ይጠበቃል።

በዚህም በአብዛኛዎቹ የበጋ ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

በሄለን ወንድምነው
++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ #ሚቲዎሮሎጂ #ትንበያ #Ethiopia
6👍2🔥1
የባሕር በር ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ጠንካራ የዲፕሎማሲ ሥራ መሥራት ይገባል
++++++++++++

በአስተዋይነት፣ በጠንካራ የዲፕሎማሲ ሥራ፣ በሰጥቶ መቀበልና ሌሎች ሰላማዊ አማራጮችን በመከተል የባሕር በር ጥያቄ ተገቢ ምላሽ እንዲያገኝ መሥራት እንደሚገባ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህርና ተመራማሪ ዱጋሳ ሙሉጌታ (ዶ/ር) ገለጹ።

https://am-digital-content.press.et/share/am-stories/4v3jfdbstsem07zf3tjjg4gmc7
👍117🥰1
ወደ ሀገር ከሚገቡ ተሽከርካሪዎች 95 በመቶ የሚሆኑትን የኤሌክትሪክ ለማድረግ እየተሠራ ነው
+++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | በመጪዎቹ 10 ዓመታት ወደ ሀገር ውስጥ ከሚገቡ ተሽከርካሪዎች መካከል 95 በመቶ የሚሆኑት ተሽከርካሪዎች የኤሌክትሪክ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሀሰን ለዘመን ኢኮኖሚ እንደገለጹት፤ የኤሌክትሪክ መኪና በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተስፋፋ ባለበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያም ከ100 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎችን ወደ ገበያው ማስገባት ችላለች።

መንግሥት የኤሌክትሪክ መኪና ምርትን ለማፋጠን፣ የነዳጅ ወጪን ለመቀነስና አረንጓዴ ከባቢን ለመገንባት አቅዶ እየሠራ ሲሆን፤ በቀጣይ 10 ዓመት ጊዜ ውስጥም ከ500 ሺህ በላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሥራ ለማስገባት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑ ገልጸዋል።

እንደ ሚኒስትር ዴኤታዉ ገለጻም በመጪዎቹ 10 ዓመታት ወደ ሀገር ውስጥ ከሚገቡ ተሽከርካሪዎች መካከል 95 በመቶ የሚሆኑት ተሽከርካሪዎች የኤሌክትሪክ እንዲኆኑ ለማድረግ ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ ነው።

ፍሬህይወት አወቀ
++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ #GazettePlus
#ትራንስፖርት #ኤሌትሪክመኪና
5
በአፍሪካ ከፍተኛ ጥራት ያለው ቡና አምራች ሀገራት
#ቡና #ኢትዮጵያ #coffeearabica #coffee
1
"ብርሃን ፈንጣቂው ዐባይ" መጽሐፍ ወደ ፊልም ተቀይሮ ለህዝብ ሊቀርብ ይገባል"

- ኡስታዝ ጀማል በሽር
የኪንግስ ኦፍ ዓባይ ሚዲያ ሥራ አስኪያጅ
++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ተዘጋጅቶ ለምረቃ የበቃው "ብርሃን ፈንጣቂው ዐባይ" ወደ ፊልም ተቀይሮ ለህዝብ ሊቀርብ እንደሚገባ የኪንግስ ኦፍ ዓባይ ሚዲያ ሥራ አስኪያጅ ኡስታዝ ጀማል በሽር ገለጹ።

በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የተዘጋጀው "ብርሃን ፈንጣቂው ዐባይ" የመጽሐፍ ምረቃ መርሃግብርና የፓናል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

ኡስታዝ ጀማል በሽር በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ መጽሐፉ ስለ ህዳሴ ግድብ በርካታ መረጃ የያዘ በመሆኑ ወደ ፊልም እና በድራማ መልክ ተቀይሮ ለህዝብ ሊቀርብ ይገባል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከብዙ መከራ በኋላ ለምርቃት በመብቃቱ ልዩ ደስታ እንደፈጠረባቸው ገልጸው፤ በመጽሐፍ መልክ መሰነዱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል።

በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ የህዳሴ ግድብ የግንባታ ሂደቱን በማጠልሸት ቅቡልነት ለማግኘት ግብጾች ሲሰሩ እንደቆዩም ኡስታዝ ጀማል ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ስለ ግድቡ ይዘት በመጽሐፍ ደረጃ ሰንዶ ለአንባቢያን እንዲበቃ በማድረጉ ያመሰገኑት ኡስታዝ ጀማል፤ በቀጣይም ኢትዮጵያዊያን ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ በጋራ መቆም ያስፈልጋል ብለዋል።

በአማን ረሺድ
9
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ጋዜጣ_ፕላስ- በጉራጌ የመስቀል የእርድ በዓል አከባበር‼️
9
ከአለም አቀፍ የአቶሚክ ፎረም ጎን ለጎን ከቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ጋር በሁለትዮሽና አለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል።

በተጨማሪም የግብርና ሜካናይዜሽንን ጨምሮ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ጉዳዮች ላይ በጋራ የምንሰራበት ሁኔታን  ተመልክተናል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
10👎1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዓለም የአቶሚክ ሳምንት (World Atomic Week) ጉባኤ ለመሳተፍ ሩሲያ ገብተዋል። #PMOEthiopia
4