Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመስከረም 9 ቀን ጀምሮ ለሁለት አመራሮች ሹመት ሰጡ

1ኛ. ዶ/ር እዮብ ተካልኝ - የብሔራዊ ባንክ ገዥ
2ኛ. ወ/ሮ እናታለም መለስ - በሚኒስትር ማዕረግ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ አድርገው ሾመዋል።
👎31
በህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ተግባር የተሰማሩ 123 ተጠርጣሪዎች የባንክ ሒሳብ ታገደ
+++++++++++
በህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ተግባር ላይ የተሰማሩ 123 ተጠሪጣሪዎች የባንክ ሂሳብ እንዲታገድ መደረጉን የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት አስታውቋል።

ህጋዊና መደበኛ የባንክ ስርዓትን ወደጎን በመተው በህገወጥና ትይዩ ገበያ የውጭ ምንዛሪ ወንጀል ላይ የተሰማሩ አካላት ላይ እርምጃ መወሰዱ እና ሌሎች ላይ ደግሞ የተጠናከረ ክትትል እየተደረገ መሆኑ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት በቅርቡ መግለፁ ይታወሳል።

በዚህም የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ለጋዜጣ ፕላስ በላከው መግለጫ እንዳመላከተው በተለያየ ደረጀ በህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ድርጊት ላይ የተሰማሩ የ123 ተጠርጣሪዎች የገንዘብ እንቅስቃሴ በዛሬው ዕለት ታግዶ የህግ ተጠያቂነት ለማረጋገጥ በሂደት ላይ ይገኛል።

አገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በርካታ ሰው የውጭ ምንዛሪ አገልግሎትን በህጋዊ መንገድ እያካሄደ በመሆኑ በእጅጉ የሚበረታታ መሆኑም ተገልጿል።

ነገር ግን አንዳንድ አካላት አሁንም ከጥቁር ገበያ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ድርጊት ለማትረፍ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆናቸውን በክትትል መረጃዎች መረጋገጡም ተገልጿል። 
 
በተጨማሪም አንዳንድ የባንክ ባለሙያዎች በጥቁር ገበያ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ድርጊት ውስጥ ተሳትፎ ያላቸው መሆኑ የክትትል መረጃው ውጤት የሚያመላክት በመሆኑ ተጨማሪ ምርመራ በመደረግ ላይ ይገኛል ብሏል።

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመደገፍ ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከሚያከናውናቸው ዋና ዋና ተግባራት መካከል ይህ የወንጀል ድርጊት አንዱና ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑ ይታወቃል።

ስለሆነም የህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ ተግባር እና ሌሎች መሰል ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 780/2005 መሠረት የወንጀል ድርጊቱ ላይ ተሳታፊ በሆኑት ላይ ተገቢው ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ አገልግሎቱ በልዩ ትኩረት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል።
7🙏1
“ሪፎርሙ ባይተገበር የግድቡ የመጠናቀቅ ዕድል ዝቅተኛ ነበር”

- ኢንጂነር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር)
++++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | ሪፎርሙ ባይተገበር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመጠናቀቅ ዕድል ዝቅተኛ ነበር ሲሉ ኢንጂነር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ኢንጂነር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) በአዲስ ዘመን ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ለውጡን ተከትሎ የተተገበረው ሪፎርም የተጓተተውንና ቅርቃር ውስጥ በመግባት መቆም ደረጃ ደርሶ የነበረውን የሕዳሴ ግድብ ለማጠናቀቅና ለውጤት ለማብቃት ዋነኛው መሰረት ሆኗል ብለዋል።

በዚህም ቴክኒካሊ የነበሩት የዲዛይን፣ የአቅርቦት እና የኤክስፖርቶች ችግሮች የተፈቱበት መሆኑን አንስተው፤ በኮንትራት አስተዳደርም አቅም ያለው የኮንትራት አስተዳደር በመለየትና ኢትዮጵያ ውስጥ ሠርተው የሚያውቁ ሦስት ኮንትራክተሮች እንዲገቡ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

የቦርድ አወቃቀርና ኃላፊነት ላይ ያሉትም ጉዳዮች እንዲሁ በሪፎርሙ ታይተው የማሻሻል ሥራ ተሠርቶ እንደገና እንዲዋቀሩ ተደርጓል ብለዋል።

በሪፎርሙ የገንዘብና ሀብት ማሰባሰብ እንቅስቃሴው በከፍተኛ ደረጃ እንዲንቀሳቀስ የሕዝብ ተሳትፎ እንዲጎለብት ማድረግ የተቻለበት መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ሪፎርሙ ባይተገበር ግድቡ የመጠናቀቅ ዕድሉ እጅግ በጣም ዝቅተኛ እንደነበር አንስተው፤ በአጠቃላይ የሪፎርም ሥራው የነበሩትን ደካማ አሠራሮች በማስተካከል የተሠራና ውጤት ያመጣ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ተስፋ ፈሩ
+++++++
Gazzette Plus ጋዜጣ ፕላስ
#ህዳሴግድብ #ሪፎርም
👍73
የከምባታ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል መሳላ በዱራሜ ከተማ በድምቀት ተከበረ
+++++++++++++

የከምባታ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል የኢትዮጵያውያን ኩራት ታላቁ ህዳሴ ግድብ በተጠናቀቀበት ዓመት መከበሩ መሆኑ የተለየ ያደርገዋል ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አንተነህ ፍቃዱ ገለፁ።

የከምባታ ብሔረሰብ የማንነት ፣ የአብሮነት የመደጋገፍ መገለጫ የመሠላ ዘመን መለወጫ በዓል በዱራሜ ሁለገብ ስታዲየም በድምቀት ተከብሯል።

የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ለአመታት ውጫዊና ውስጣዊ ተፅዕኖዎችን ተቋቁሞ ታላቁ ህዳሴ ግድብን በስኬት ባጠናቀቁበት ማግስት በኩራት የምናከብርበት ዕለት መሆኑ የዘንድሮውን በዓል የተለየ ያደርገዋል ብለዋል።

የከምባታ ብሔረሰብ የአብሮነት የመተሳሳብ የመደጋገፍ ማሳያ የሆነው የመሳላ ዘመን መለወጫ በዓል በአለም ቅርስነት እንዲመዘገብ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር  አቶ አረጋ እሸቱ  ተናግረዋል።

የቱሪዝም ሚኒስትር ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ በበኩላቸዉ እንደመሳላ ያሉ በዓላት የቱሪዝም መሰህብ እንዲሆኑ ለማድረግ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

መንግስት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በማድረግ ለቱሪዝም እድገት የተለየ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በማህሌት አብዱል
6👎1
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ለጦር መኮንኖች ሹመት ሰጡ
++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ| በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅራቢነት ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መስከረም 10 ቀን 2018 ዓ.ም የሚከተሉትን የጦር መኮንኖችን ሹመዋል።

👉 በጄነራልነት ማዕረግ፤

1 ሌ/ጄኔራል አለምሸት ደግፌ
2 ሌ/ጄኔራል ደስታ አብቼ
3 ሌ/ጄኔራል ይመር መኮንን
4 ሌ/ጄኔራል ድሪባ መኮንን

👉 በሌ/ጄኔራል ማዕረግ፤

1 ሜ/ጄኔራል ከፍያለዉ አምዴ ተሰማ
2 ሜ/ጄኔራል ክንዱ ገዙ ተገኝ

👉 በሜ/ጄኔራል ማዕረግ፤

1 ብ/ጄኔራል ታደሰ አመሎ ሲኤሳ
2 ብ/ጄኔራል ቡልቲ ታደሰ ክቲላ
3 ብ/ጄኔራል ኃይሉ እንደሻዉ አቶምሳ
4 ብ/ጄኔራል ዋኘዉ አለሜ አያሌዉ
5 ብ/ጄኔራል ነገራ ሌሊሳ ሙለታ
6 ብ/ጄኔራል ተስፋዬ ረጋሳ አመንቴ
7 ብ/ጄኔራል ደረጀ መገርሳ እሰታ
8 ብ/ጄኔራል በርሄ ገ/መድህን ደመወዝ
9 ብ/ጄኔራል ያሲን ሙሃመድ ሲሳይ
10 ብ/ጄኔራል ዘዉዱ ሰጥአርጌ ደመቀ
11 ብ/ጄኔራል ሚልኬሳ ረጋሳ ኢተፋ
12 ብ/ጄኔራል መለስ መንግስቴ ንረይ
13 ብ/ጄኔራል ተሾመ አናጋዉ አየለ
14 ብ/ጄኔራል አማረ ባህታ በርሄ
15 ብ/ጄኔራል አበባዉ ሰኢድ ይመር
16 ብ/ጄኔራል ደስታ ተመስገን አራጋዉ
17 ብ/ጄኔራል ከማል ኤቢሶ

👉 በብ/ጄኔራልነት ማዕረግ፤

1 ኮ/ል ግርማ ፌዬ ከበደ
2 ኮ/ል ደመቀ መንግስቱ ጽዱ
3 ኮ/ል ተመስገን አስማማው አስናቄ
4 ኮ/ል ሰጠኝ ሊክሳ ኒካ
5 ኮ/ል ጌትነት አዳነ ካሳ
6 ኮ/ል  ዮሃንስ መኮንን እጄታ
7 ኮ/ል አባቡ ተሸመ ለገሰ
8 ኮ/ል  መኮንን መንግስተ ተበጀ
9 ኮ/ል አሰፋ ደበሌ ነጋዎ
10 ኮ/ል አለሙ ቂጣታ ወረታ
11 ኮ/ል ሙላው በየነ አማኑ
12 ኮ/ል ደጀነ ፀጋዬ ተሻለ
13 ኮ/ል ቾምቤ ወርቁ እሬሶ
14 ኮ/ል አባተ አሰፋ ካሴ
15 ኮ/ል ተሾመ ባጫ ጎሹ
16 ኮ/ል አዲሱ ትርፌሳ በየነ
17 ኮ/ል ዩሃንስ ትኬሳ አያንሳ
18 ኮ/ል ዳኛቸው አያሌው እንግዳ
19 ኮ/ል ፍቃዱ ታደሰ ሰጠኝ
20 ኮ/ል አስናቀ አይተነው መንግስቴ
21 ኮ/ል የሺጥላ ተስፋዬ ደመቀ
22 ኮ/ል መልካሙ ቶማ በየነ
23 ኮ/ል ፈይሳ አየለ ገብረየስ
24 ኮ/ል ጀማል ከድር በዳሳ
25 ኮ/ል ቸርነት መንገሻ ገብሬ
26 ኮ/ል አዘነ ሽመልስ ታደሰ
27 ኮ/ል ጥላሁን ዱጋሳ ጌቱ
28 ኮ/ል ንጉሴ ለውጤ መንግስቱ
29 ኮ/ል ገነት ይማም ታደሰ
30 ኮ/ል ጥላሁን ደምሴ ይርሳው
31 ኮ/ል መሀመድ አህመድ መሀመድ
32 ኮ/ል መስፍን በየነ ኃይሌ
33 ኮ/ል ቡሩክ ሰይፉ ሰርበቶ
34 ኮ/ል መሰረት ጌታቸው የሱነህ
35 ኮ/ል ሁሴን መሃመድ አሕመድ
36 ኮ/ል ግርማ አየለ ጉርሙ
37 ኮ/ል ጣሂር ሳሌህ አሊ
38 ኮ/ል ቦጃ አጋ በዳኔ
39 ኮ/ል አካሉ ካሳ ቦኬ
40 ኮ/ል አዲሱ በድሩ መሃመድ
41 ኮ/ል ቢራራ አበበ ተክሉ
42 ኮ/ል ረሺድ ኢብራሂም አሊይ
43 ኮ/ል ደምሴው አንተነህ ደመላሽ
18👍6👏3
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከሰኞ ጀምሮ ለጎብኚዎች  ክፍት እንደሚሆን ተገለፀ
+++++++++++++++
ጋዜጣ_ፕላስ |ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን መጎብኘትለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ከፊታችን ሰኞ መስከረም 12 ጀምሮ በመመዝገብ መጎብኘት እንደሚችሉ የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።

የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊ ካሳ የአለም የቱሪዝም ቀንን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንደገለፁት፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመተባባር ለጉብኝት ክፍት ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል።

ህዳሴን መጎብኘት የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል ተመዝገበው መጎብኘት ይችላሉ።

አየር መንገዱ በሳምንት ሁለት ጊዜ ወደ ጉባ በራራ እንደሚያደርግ የገለፁት ሚኒስትሯ በእያንዳንዱ በረራም 50 ጎብኚዎችን ያስተናግዳል ብለዋል።

ኢንቨስት ማድረግ ለሚፈልጉ ባለሃብቶችና የቱሪዝም ዘርፍ ተዋናዮች ግድቡ ከፍተኛ የቱሪዝም መደረሻ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንዲያበረክቱ እድል የሚፈጥር መሆኑንም አስገንዝበዋል።

በዚህ መነሻ ግድቡን መጎብኘት የሚፈልጉ ተቋማት፣ ግለሰቦች ከፊታችን ሰኞ መስከረም 12 ጀምሮ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በተከታዮቹ አድራሻዎች BiruckL@ethiopianairlines.com፤ 0911516125 ወይም SurafelMe@ethiopianairlines.com +2519-04 05 03 22 መመዝገብ እንደሚችሉ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ አስታውቀዋል።

በቅርቡ የተመረቀው ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚሆን መግለጹ ይታወሳል፡፡

በማህሌት አብዱል
8👍7
ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ
🥰21
የውጭ ባንኮች መግባት የተሻለ የውጭ ምንዛሬ ዕድገት እንዲኖር ያስችላል
++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | የውጭ ባንኮች ወደ ሀገር ውስጥ መግባት የተሻለ የውጭ ምንዛሬ ዕድገት እንዲኖር እንደሚያስችል ተገለፀ።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የንግድ ሥራ ኮሌጅ መምህርና የፋይናንስ ባለሙያ የሆኑት ዳኪቶ ዓለሙ (ዶ/ር) ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለፁት፤ የውጭ ባንኮች ወደ ሀገር ውስጥ መግባት በሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ዕድገት እንዲኖር አስተዋጽኦ ይኖረዋል፤ ነገር ግን የአሰራር ሂደተቻው የራሱ የሆነ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል።

የሀገር ውስጥ ባንኮች ለሚጠብቃቸው ፉክክር ከአሁኑ መዘጋጀት አለባቸው ያሉት ባለሙያው፤ የካፒታል መጠናቸውን ከፍ ማድረግ፣ እራሳቸውን በቴክኖሎጂ መብቃትና የአስተዳደር ስርዓታቸውን ማዘመን ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

ብሔራዊ ባንክ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ባንኮችን የሚለይበት ሂደትና አሰራራቸውን የሚቆጣጠርበት መንገድ ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ሊሆን እንደሚገባ ገልፀዋል።

በሌላ በኩል በረዥም ጊዜ ባንኮቹ ትርፋቸውን በውጭ ምንዛሬ ስለሚወስዱ ይዞት የሚመጣው ጫና ሊኖር እንደሚችል አመልክተዋል።

የሀገር ውስጥ ባንኮች በአስተዳደርና በሚሰጡት አገልግሎት ላይ ውስንነት ይታያል። የማበደር አቅማቸውም አነስተኛ ነው ይህንን ለመሻሻል መሥራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የግል ባንኮች የማበደር አቅም አነስተኛ ነው፤ ነገር ግን ትልልቅ ፋብሪካዎችን ለመቋቋም ከታሰበ ከፍተኛ የፋይናንስ አቅርቦት ልኖር ይገባል፤ የውጭ ባንኮች የደረጀ ካፒታል ይዘው ስለሚመጡ የተሻለ የብድር አቅርቦት በመመቻቸት ለኢኮኖሚያዊ እድገቱ በጎ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ተናግረዋል።

የባንኮቹ መግባት የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖር ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል፤ ነገር ግን የእነርሱ መግባት የኢትዮጵያን የፋይናንስ አስተዳደር ለዓለም ገበያ ክፍት ስለሚያደርግ በየትኛውም የዓለም ሀገር የሚፈጠረው የፋይናንስ ቀውስ በቀላሉ ወደእኛ መዛመቱ ስለማይቀር ሂደቱን ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ መካሄድ እንደሚገባ አብራርተዋል።

በክብረአብ በላቸው
#ጋዜጣ_ፕላስ #ጋዜጣ #gazette_plus #ኢትዮጵያ
9👍3
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገቢ ከ10 ዓመት በኋላ 25 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል
+++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | ከ10 ዓመት በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገቢ 25 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ገለጹ፡፡

አቶ መስፍን ከዘመን ኢኮኖሚ ዝግጅት ክፍል ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ አየር መንገዱ እአአ በ2035 ላይ 209 ዓለም አቀፍ እና 31 የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች፣ 271 አውሮፕላኖች የሚኖሩ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

67 ነጥበ 2 ሚሊዮን መንገደኞችንም በማጓጓዝ ከ10 ዓመት በኋላ ገቢውንም 25 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ መታቀዱን ገልጸዋል፡፡

ለዚህም አዳዲስ መዳረሻዎችን በማስፋት ትስስሩን ይበልጥ ማጠናከር እና አዳዲስ መዳረሻዎችን መክፈት የሚያስፈልግ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ለዚህም አሁን በረራ ከሚደረግባቸው አምስቱ ክፍለ አኅጉሮች ተጨማሪ አውስትራሊያንም የሚጨመር መሆኑን ጠቅሰው፤ በብዙ ሀገሮች አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሁለትም ሶስትም አራትም ጊዜ በረራ ከማድረግ መታቀዱን ገልጸዋል፡፡

ያረጁትን አውሮፕላኖችን በመለወጥ አዳዲስ ዘመናዊ አውሮፕላኖች የሚመጡ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ጥሩ ሥነምግባር እና ተነሳሽነት ያለው ሠራተኛ መገንት መቀጠል አለበት ያሉት አቶ መስፍን፤ በየዓመቱ 300 ፓይለት ለማሰልጠን እቅድ መያዙንም አስታውቀዋል፡፡

ከአምስት ዓመት በኋላ (እአአ በ2029) ሙሉ በሙሉ ወደ አዲሱ ኤርፖርት የሚገባ መሆኑን ገልጸው፤ አዲሱ ኤርፖርት በጥራትም በስፋትም ከአፍሪካ አንደኛ በመሆን የአፍሪካን የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ከሌላው ዓለም ደረጃ ላይ እናደርሳለን ብለዋል።
3👍1
በዓለም ከፍተኛ የሰሊጥ አምራች ሀገራት
++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | በዓለም አቀፍ ደረጃ የሰሊጥ ዘር ኢንደስትሪ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ ሲሆን ሀንድ፣ ቻይና፣ሱዳን፣ ማይናማር፣ታንዛኒያና ኢትዮጵያ ከፍተኛ የገበያ ድርሻ ያላቸው ሀገራት ናቸው።

ኢትዮጵያ ስድስት በመቶ የሚሆነው የዓለም የሰሊጥ ዘር ገበያ ድርሻ ይዛ ምርቷን ወደ አፍሪካ፣ ኤዢያና ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት በስፋት የምትልክ ሲሆን ሰሊጥ ሀገሪቷ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ከምታገኝባቸ የግብርና ምርት ዝርዝሮች ዉስጥ ይካተታል።

በመስከረም ሰይፉ
+++++++++++
Gazzete plus ጋዜጣ ፕላስ
#ግብርና #ሰሊጥ
6👍2
አየር መንገዱ ባለሙያዎችን እያስኮበለሉ ላስቸገሩት ሀገራት ቴክኒሽያኖችን አሠልጥኖ ሊሰጥ ነው
+++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለሙያዎችን እያስኮበለሉ ላስቸገሩት ሀገራት ቴክኒሽያኖችን አሠልጥኖ ሊሰጥ መሆኑን ገለጸ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በኢፕድ ከምትዘጋጀው ዘመን ኢኮኖሚ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ በተለይ የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቴክኒሽያኖችን በገንዘብ እያስኮበለሉ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድን ቴክኒሽያኖች በጣም ብዙ ገንዘብ እየከፈሉ የሚወስዱ የመካከለኛው ምስራቅ አካባቢ አየር መንገዶች እንዳሉ ጠቅሰው፤ የቴክኒሽያኖቹ መኮብለል በአየር መንገዱ ላይ ፈተና ፈጥሯል ብለዋል፡፡

የቴክኒሽያኖችን ኩብለላ ለማስቀረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ እያስኮበለሉ ከሚወስዷቸው ሀገራት አየር መንገዶች ጋር ንግግር መጀመሩን ተናግረዋል። በዚህም አስኮብላዮቹ የሚፈልጉትን ያህል ቴክኒሽያን አሰልጥነን እንሰጣለን ብለዋል፡፡

በተለይም ለመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት አየር መንገዶች ወደ 1000 የሚሆኑ ባለሙያዎችን አስተምሮ ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን አብራርተዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ አየር መንገዱ ከሁለት ሺህ 500 በላይ ቴክኒሽያኖች እንዳሉትም አያይዘው ገልጸዋል፡፡

#አየርመንገድ #ስልጠና
12👍1👏1😁1
በሚቀጥሉት ቀናት በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል
+++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | በሚቀጥሉት ቀናት በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢኒስቲትዩት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢኒስቲትዩት ከመስከረም 11 ቀን እስከ መሥከረም 20 ቀን 2018 ዓ.ም የሚኖረውን የአየር ሁኔታ አዝማሚያ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በላከው መግለጫ አስታውቋል።

በዚህም በሚቀጥሉት ቀናት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ቀጣይነት እንደሚኖራቸው ተመላክቷል፡፡

በመሆኑም በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ እንዲሁም በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል።

በተጨማሪም በፀሐይ ሀይል ታግዞ ከሚጠናከሩ የደመና ክምችቶች ላይ በመነሳት በምዕራብ፣ በመካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ አልፎ አልፎ በሚኖሩት ቀናት በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው ተጠቁሟል።

በሌላ በኩል በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከቀን ወደ ቀን የደመና ሽፋን እንደሚጨምር ይጠበቃል።

በዚህም በአብዛኛዎቹ የበጋ ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

በሄለን ወንድምነው
++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ #ሚቲዎሮሎጂ #ትንበያ #Ethiopia
6👍2🔥1