✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.2K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
Forwarded from Deleted Account
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን(፫)

"የማለዳ ፆለት"
የጊዚያት ባለቤት እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ
የጨለማዉን ግርማ ገፈህ
ብርሀንን እንድመለከት
ስላደረከኝ አመሰግንሃለሁ።
በምኝታየ ስለጠበከኝ ከሞት
ስለሰወርከኝ እጅ መንሳቴን
አቀርባለሁ።
ቸር እረኛየ ትጉህ የማታንቀላፋ ነህና ለሊቱን ከ እኔ ጋር ሁነህ እደጠበከኝ
ይህንንም ማለዳ ባርከህ ቀድሰህ የሰላም ዉሎ እንድዉል ቀኝህ ትርዳኝ።
መንገዴን ሁሉ ከፊት እየሆንክ ምራኝ።
ከደካማ ፍጡርነቴ የተነሳ
በኃላየ ምን ምን እንዳለ
አላዉቅምና አንተ ጠብቀኝ።
በዙሪያየ ሁሉ ጠላት ያስቀመጠብኝን እንቅፋትና መሰናክል አስወግድልኝ።
ከፈተና የተነሳ ብወድቅ እንኳን አንሳኝ እንጅ አትተወኝ።
በዚእች ቡርእክት እለትም
በስራየ፣በንግዴ በመንገዴ፣
በክብሬ፣በአገልግሎቴ ሁሉ
የጥፋት መረቡን ዘርግቴ
ሰላሜንና በረከቴን ሊያሳጣኝ
የተዘጋጀዉንና የሚያሴርብኝን
ጠላቴን(ዲያቢሎስን)እቅድና
ስራዉን አፍርሰህ ሰላሜን
አጎናፅፈኝ።
በዚህ እለት ሀጢያትን አቅጀ
በድፍረት እንዳልፈፅም በመዘናጋትም እንዳልተገብር
አድርገኝ።
ደም ከሚፈስበት ፍርድ ከሚዛባበት ድሀ ከሚበደልበት በማታለልና በማጭበርበር ከሚከበርበት
ጣኦትና ሰይጣን ከሚመለክበት ስራና ቦታ ሁሉ
ፈፅመህ ጠብቀኝ።
ደካማዉ ልጅህ እጆቸን ዘርግቸ መንገዴን እንድትመራኝ በቀረቡህ ጊዜ
ሀጢያቴንና በደሌን አይተህ
ሳትጠየፈኝ ተቀብለህ ምራኝ።
እለቱን ሁሉ ፍቃድህን ማድረግ እንድችል በቃልህ
አስተምረኝ።
መንፈስ ቅዱስ ሂወቴን ይቆጣጠር።
ትናንትን እንደጠበከኝ እንደ መገብከኝ ከክፉም እንደሰወርከኝና እንደ ፈወስከኝ ዛሬም እንደ ፈቃድህ ጠብቀኝ።
አንተ ያልከዉ ይሆን ዘንድ ግድ ነዉና በከንቱ ከመጨነቅና ተስፋ ከመቁረጥ ሰዉረኝ
ለዘልአለሙ


አሜን አሜን አሜን




🔷ይንን ጉባኤ ባርክልን ጌታችን (2)
🔷ሰላም ስጠን ፍቅር ስጠን ዛሬ ለሁላችን እኧ ... (4)
🔷ስብሀት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ (2)
🔷ይደርብን የመስቀሉ የማርያም ፍቅር እኧ ...(4)
ወ񝻈ዳንተ ስንፀልይ ባንድነት ሆነን(2)
🔷ጌታችን ሆይ ላክልን ፍቅርና ሰላም
🔷ጌታችን ሆይ ላክልን መንፈስ ቅዱስን እኧ...(4)
🔷ከደመናው በታች እንዳይቀር ፀሎቴ(2)
🔷አሳርጊው አሳርጊው ድንግል እመቤቴ
🔷አሳርጊው አሳርጊው ማርያም እናቴ እኧ...(4)
🔷እርሱ እንደንብ አውራ ፈረሱ እንዳሞራ(2)
🔷ጊዮርጊስ ሆይ ጊዮርጊስ ሆይ ኢትዮጰያን አደራ
🔷ጊዮርጊስ ሆይ ጊዮርጊስ ሆይ ተዋህዶን አደራ እኧ ...(4)


አሜን አሜን አሜን 💠💠💠
Forwarded from Deleted Account
Forwarded from Deleted Account
Forwarded from Deleted Account
*የእለቱ ስንክሳር በወንድማችን ዲ/ን ገ/እግዚአብሔር*
ለወንድማችን እግዚአብሔር ቃለሂወትን ያሰማልን።

*Ye eltu Sinkisar be wendimachin D/n G/Egziabher*
Lewendimachin Egziahbher kalehiwetn yasemaln።👆👆👂👈
Forwarded from Deleted Account
amenn enkawn adershu malkem ken all
Forwarded from Deleted Account
Forwarded from Deleted Account
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Deleted Account
እንኳን_አደረሳችሁ_የእናቴ_ልጆች_ብቻ ፨
“አንቺ ጸጋን የተሞላብሽ ሰላም ላንቺ ይሁን እግዚአበሔር ከአንቺ ጋር ነው”
“(አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ።
እምቤታችንን ማክበር፦ስለ እመቤታችን ክብር በመጽሐፍ ቅዱስ የተፃፈውን
የእመቤታች ንግግር መጥቀስ በቂ ነው እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት
ይሉኛል። ሉቃ 1፥48 እዚህ ላይ ትውልድ ሁሉ የሚለው ሐረግ ከኢየሱስ ክርስቶስ
መወለድ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም እመቤታችንን ማክበር ዓለም አቀፋዊ ባህለ
ሃይማኖት እንደሆነ ያረጋግጥልና።
በመጽሐፍ ቅዱስ እመቤታችንን ስለማክብር የተፃፉ ብዙ ጥቅሶች አሉ፣ ለምሳሌ
በእመቤታችን እናት ዕድሜ የነበረችዋ ቅድት ኤልሳቤጥ እመቤታችንን
“የጌታዬእናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? እነሆ፥ የሰላምታሽ
ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና።” ሉቃ 1፥ 43-44
አለቻት እዚህ ላይ የሚያስደንቀን ነገር ኤልሳቤጥ የእመቤታችንን ሰላምታ
በሰማች ጊዜ “መንፈስ ቅዱስ ሞላባት” የሚለው ሐረግ ነው።የእመቤታችንን
ድምፅ መስማት ብቻ ኤልሳቤጥን መንፈስ ቅዱስ እንዲሞላባት አደረጋት።
እመቤታችን ክብርን ከሰው ልጅ ብቻ የቀበለች አይደለችም ከመላዕክትም
ጭምር እንጂ፤ ይህም ቅዱስ ገብርኤል “ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ
ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ።” /ሉቃ 1፥28/ ሲላት
ተረጋግጧል፣ “ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ” የሚለውንሐረግ ኤልሳቤጥም
ለእመቤታችን ሰላምታ ስትሰጥ ደግማዋለች /ሉቃ 1፥42/ መልአኩ ቅዱስ
ገብርኤልም ከእመቤታችን ጋር በተነጋገረበት ሁኔታ ከካህኑ ከዘካርያስ ጋር
ከተነጋገረበት ሁኔታ እጅግ የተለየ እንደነበር እናስታሳለን። “ዘካርያስም ባየው
ጊዜ ደነገጠ፥ ፍርሃትም ወደቀበት።” /ሉቃ 1፥12/ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል
እመቤታችንን ባነጋገራት ጊዜ ግን በሚያስፈራ ሁኔታ አልቀረባትም ነበር ይህም
ይህም የእመቤታችን ክብር ያሳየናል።ስለ እመቤታችን የተነገሩ ብዙ ትንቢቶች
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሉ፣ እነርሱም “በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና
ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።” በድጋሚ ስለእርሷ “ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ
ክብርዋ ነው ልብስዋ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው።”
መዝ 45፥9 እና 13/ ይላል ስለዚህ እመቤታችን የንጉሥ ልጅ ንግሥት ነች፣
የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናችንም ከጌታችን በስተቀኝ ዘውድ የተቀዳጀች ንግሥት
አድርጋ የምትመስላት ለዚህ ነው። ቤተክርስቲያን በመዝሙሯ እመቤታችንን
“መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ፥ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጪያለሽ።” /ምሳ
31፥29/ በማለት ታስመሰግነናለች።* እመቤታችን የጌታችን የኢየሱስ እናት
እንደመሆኗ ለጌታችን የሚሰጡት ስሞች ሁሉ ለእርሷ ሊሰጧት ይችላሉ።*
ጌታ ኢየሱስ እውነተኛ ብርሃን ነው። /ዮሐ 1፥9/ ስለራሱም “እኔ የዓለም ብርሃን
ነኝ” /ዮሐ 8፥12/ አለ፣ ስለዚህ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም የእውነተኛ
ብርሃን እናት (እመብርሃን) ነች።* ክርስቶስ አዳኝ እንደመሆኑ ለእረኞች “ዛሬ
በዳዊት ከተማ መድሐኒት ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋና” /ሉቃ 2፥11/
ተብሎ ተነገረ። ኢየሱስ ማለት መድሐኒት ማለት ነው፣ መድሐኒት የተባለበት
ምክንያት ሕዝቡን ከኃጢያታቸው ስለሚያድናቸው ነው፣ እመቤታችን ቅድስት
ድንግል ማርያም ደግሞየመደኀኒያለም (የመድሐኒት) እናት ነች።
* ክርስቶስ እግዚአብሔር እንደመሆኑ /ዮሐ 20፥28 ሮሜ 9፥5 1ኛ ዮሐ 2፥23/
እመቤታችንም የእግዚአብሔር እናት /ወላዲተአምላክ/ ነች።* ኤልሳቤጥ
እመቤታችንን “የጌታዬ እናት” /ሉቃ 1፥43/ እንዳለቻት እመቤታችን የጌታችን
እናት ነች። በተጨማሪም የአማኑኤል እናት ነች፣ /ማቴ 1፥24/ ሥጋ የሆነ ቃል /
የሥግው ቃል/ እናት ነች። /ዮሐ 1፥14/* ድንግል ማርያም የክርስቶስ እናት
ከሆነች የሁሉም ክርስቲያኖች መንፈሳዊት እናት መሆኗ አያጠያይቅም። ይህንንም
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀልላይ ሳለ አረጋግጦልታል። ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ ለተወደደው ደቀመዝሙሩ “እናትህ እነኋት”
አለው። /ዮሐ 19፥27/ እመቤታችን ለቅዱስ ዮሐንስ እናቱ ከሆነች ቅዱስ
ዮሐንስ “ልጆቼ ሆይ” /1ኛ ዮሐ 2፥1/ ለሚለን ለእኛ ለሁላችን ቅድስት ድንግል
ማርያም እናታችን ነች ማለት ነው። ስለዚህ “እኅታችን” የሚለው መጠሪያ
ተቀባይነት የለውም፣ አቤት የሚል ምላሽም አያስገኝም።* በስሙ ለምናምንና
ልጆቹ ለሆንን ለኛስ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናት እንዴት ብላ እኅታችን
ትሆናለች? ለእኛስ የእርሱ ልጆች የእርሷ ወንድምና እኅቶች መሆን እንዴት
ይቻለናል?* እናትን ማክበር ታላቅ ተስፋ ያዘለ ትዕዛዝ ከሆነ /ዘጸ 20፥12 ዘዳ
5፥16 ኤፌ 6፥2/ የጌታችንና የሐዋርያቱን እናት፣ መልአክ፦ “መንፈስ ቅዱስ
በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል” /ሉቃ 1፥35/ ብሎ
የተናገረላትና ከጌታ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት /ሉቃ
1፥45/ ብላ ቅድስት ኤልሳቤጥ የተናገረችላትን እናታችን ቅድስት ድንግል
ማርያም ማክበር የለብንምን?እመቤታችን በዓለም ካሉ ሴቶች ትበልጣለች
ቤተክርሰቲያንም ይህንን ክብሯን እያሰበች (መልዕልተ ፍጡራን መትሕተ ፈጣሪ)
ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታችትላታለች።
በተጨማሪም በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤልና በቅድስት ኤልሳቤጥ “ከሴቶች
መካክል የተባረክሽ ነሽ” ተብሎ ተነግሮላታል፣ ምክንያቱም ምንም
ሴትእመቤታችን የነበራትን ንፅህና አልነበራትምና ነው፣ ይህም የእርሷን ውዳሴና
ከፍ ያለ ክብር ያሳያል፤ ስለዚህም ነው ነቢየ ኢሳያስ ስለ ግብፅ የተነገረሸክም
በተሰኘው ትንቢቱ “ደመና” ብሎ የሰየማት። /ኢሳ 19፥1/* በሥጋዌ ጊዜ
በእመቤታችን ማህፀን ማደሩን በተመለከት ቤተክርስቲያን እመቤታችንን
(ዳግማዊት ሰማይ) ሁለተኛ ሰማይ እና የሙሴ ጽላት ብላ ትጠራለች።*
በተጨማሪም ቤተክርስቲያን እመቤታችንን “የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፥ በአንቺ
የተከበረ ነገር ይባላል ... እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት።” /መዝ86/
ትላታለች።· ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምና እንደሚመሰል ተናገረ፣ ምክንያቱም
እርሱ ከሰማይ የወረደ የሕይወት እንጀራ ነውና። /ዮሐ 6፥58/ ስለዚህ
ቤተክርስቲያን እመቤታችንን “የመና ሙዳይ” ብላ ትጠራታለች። ስለ
ድንግልናዋም “የለመለመች የአሮን በትር” /ዘኁ 17፥8/ ብላ ትጠራታለች።·
እመቤታችን በታቦት ትመሰላለች /ዘጸ 25፥ 10-22/ ምክንቱም መጀመሪያ ታቦቱ
በውስጥና በውጭ በወርቅ ተለብጧልና፣ በንፅህናዋና በክብሯ ይመሰላል፣
ሁለተኛ ሁለተኛም ታቦቱ በማይነቀዝ የግራር እንጨት ተሰርቷልና በቅድስናዋ
ይመሰላል፣ ሶስተኛም ታቦቱ መና ይቀመጥበታለና እርሱም ከሰማይ የወረደ
የእይወት እንጀራ በሆነ በክርሰቶስ ይመሰላል፣ እሷ ደግሞ በታቦቱ፣ በመጨረሻም
ታቦቱ ሁለቱን የህግ ጽላቶች ይዟል፣ እነርሱም፦ የእግዚአብሔር ቃል የክርስቶስ
ምሳሌዎች ናቸው። /1ኛ ዮሐ 1፥1/· ሰማያዊውን አምላክ ስለተሸከችውና
ስለወለደች ያዕቆብ በህልሙ ከሰማይ እስከ ምድር ያያትን መሰላል
ትመስላለች፣ ምክንያቱም በክርስቶስ ሥጋዌ የሰማይና የምድር መገናኘት በእርሷ
ተደርጓልና። መንፍስ ቅዱስ ከመለኮታዊ እሳቱ ጋር በእርሷ ባደረ ጊዜ
አላቃጠላትምና ሙሴ ሳይቃጠል ባያት ቁጥቋጦ ትመሰላለች /ዘጸ 3፥ 2-4/
የክርስቶስ ሥጋና መለኮት መዋሐድ የእሳትና የከሰልን መዋሐድ ይመስላል፣
ስለዚህም ቅድስት ማርያም ይህንን ውህደት የተሸከመች ማዕጠንትን
ትመስላለች፣ በመሆኑም የአሮን የወርቅ ማዕጠንት ትባላለች፣ ይህም ክብሯን
ያሳያል።በተጨማሪም ቤተክርስቲያን
Forwarded from Deleted Account
ርግበ ሰናይት /መልካሟ ርግብ/ ብላ
ትጠራታለች። ምክንያቱም፦1. በትህትናዋ ርግብን ትመስላለችና፣2. በርግብ
አምሳል የታየ መንፈስ ቅዱስ /ማቴ 3፥16/ በእርሷ ላይ ወርዷልና፣3. ለሰው
ለጆች የመዳን /የድህነት/ ብስራትን አምጥታልናለችና፣ በምድር ጥፋት ላይ
የሕይወት መመለስን ባበሰረችው ርግብ ትመሰላለች። /ዘፍ 8፥ 10-11/
ለእመቤታችንና ለቤተክርስቲያን ለሁለቱም በተመሳሳይ ሁኔታ ብዙ ትንቢቶች
ስለተነገሩ እመቤታችን በቤተክርስቲያን ትመሰላለች፣በቅዱሳን መጻሐፍትና
በንዋየ ቅዱሳት ትመሰላለች፣ የእመቤታችን ምሳሌዎች እጅግ በጣም ብዙ
ናቸው
Forwarded from Deleted Account
የጌታየ እናት ድንግል ማርያም ሆይ ላመሰግንሽ ልቤ ይነሳሳል አንደበቴ ግን
ይሰንፋል፤ ህሊናየ በፍቅርሽ ደስታ ተነሳስቷል አፌ ግን ቃል ያንሰዋል፤ እናቴ
ሆይ፦ ክርስቶስ ምንኛ ወደደን? አዛኝ እናቱን አንቺን ሰጥቶናልና ሃጥያታችን እጅግ
ብዙ ቢሆን የአንቺ የፀሎትሽ ሃይልም ብዙ ነው በየቀኑ እንበድላለን በየቀኑም
ንስሃ እንድንገባ አንቺን በህሊናችን እንመለከታለን የዚህ አለም ውበት በእጅጉ
ይስበናል የአንቺና የልጅሽ ፍቅርም በእጅጉ ይማርከናል ወደሃጢአት እናመራለን
ወደ አንቺና ወደ ልጅሽም እንመለሳለን የልጅሽ ምህረቱ ብዙ ነው ያንቺ ፀሎትም
ልዩ ነውና እንደጠፋን አንቀርም እንዳወዳደቃችንም አንሰበርም፡፡
ድንግል ሆይ ድኩማን መሆናችን እጅግ እንዳደከመሽ አስባለሁ የዘወትር
በደላችንም አሰልቺ ነው አንቺና ልጅሽ ግን በእኛ ተስፋ አትቆርጡም፡፡ ድንግል
ሆይ፦ ይህ የልጅሽ ፍቅር ከአእምሮ በላይ መሆኑ ድንቅ ነው የአንቺም የእናትነት
ፍቅር ብርቱ መሆኑ ልዩ ነው፡፡ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ሆይ፦ ስለዚህ
እወድሻለሁ ከፍ ከፍም አደርግሻለሁ ከልጅሽ ጋር ሆነሽ ከእኔ እንዳትለይ
አውቃለሁ ይህም ለልቤ ደስታ ነው፡፡
አሜን ፀጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን
Forwarded from Deleted Account
*ተነሣ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ አለው ማቴ 2 ÷ 13*
በመጋቤ ሐዲስ ቀሲስ አበበ
ለመምህራችን ቃለ ህይወት ያሰማልን
*ማኅበረ ተዋህዶ ዘኦርቶዶክስ*
*26 : 11*
*Tenesa Hetsanunena Enatunm Yizeh Wede Gebts Shishe Eskenegerhem Dres Beziya Tekemte Alew*
*Matiewos 2÷13*
Be Megabie Hadis Kesis Abebe
Lememherachin Kale Hiywot Yasemalen
*MAHBERE TEWAHDO ZE ORTHODOX*
👆👂👂👈
Forwarded from Deleted Account
Forwarded from Deleted Account
Forwarded from Deleted Account
*ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል ሉቃ 1 ÷48*
በመጋቤ አእላፍ ቀሲስ ገብረ ዮሐንስ
ለመምህራችን ቃለ ህይወት ያሰማልን
*ማኅበረ ተዋህዶ ዘኦርቶዶክስ*
*55 : 33*
*Kezarie Jemero Tweld Hulu Betse'et Yelugnal*
*Lukas 1 ÷ 48*
*Be Megabie Aelaf Kesis Gebre Yohanes*
Lememherachin Kale Hiywot Yasemalen
*MAHBERE TEWAHDO ZE ORTHODOX*
👆👂👂👈
Forwarded from Deleted Account
Forwarded from Deleted Account