✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞ via @like
በሰሙነ ሕማማት የሚፈጸሙ ሥርዓቶች
@embtee
1.ስግደት:-በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት
እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል::
2. ጸሎት:- በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት
ይገኛሉ እነዚህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት
እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው::
በነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት
ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ::
3.ጾም:-በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት /አዘውትረን የምንመገባቸው
ምግቦች/ አይበሉም:: በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት እንድንጾም;
ይኸውም ቆሎ;ዳቦ;ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ
ይገኛል::
4.አለመሳሳም:-አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና
ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም:: መስቀልም
በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር
ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ገላ. 3:13
ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29
5.አክፍሎት:-እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ
አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው::
6.ጉልባን:-ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ
ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው::
7.ጥብጠባ:-ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን
እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው::
ይህም የጌታ ምሳሌ ነው::
8.ቄጠማ:-ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ
አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን::
እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም
ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም::
@embtee _ @embtee

…..3ኛ. ማክሰኞ…..
.
በዚህ ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሥልጣኑ ተጠይቋል፡፡ @embtee
የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሌዎች ‹‹በምን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ?
ይህንንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ? አሉት››፡፡ ጥያቄአቸው የፈተና ስለነበር
ጥያቄአቸውን በጥያቄ መልሶ አሳፍሯቸዋል፡፡ በዚህም መነሻነት በቤተመቅደስ
ውስጥ ረጅም ትምህርት አስተምሯል፡፡
.
ጥያቄውም ሆነ ረጅም ትምህርቱ በሦስቱ ወንጌላውያን በሚከተሉት ጥቅሶች
ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡
1. ማቴ.21÷23-46
2. 2.ማር.11÷27-33
3. ሉቃ.20÷1-26
በዚሁ ዕለት በቤተክርስቲያን በየሰዓቱ የሚሰበከው ምስባክ፤
.
በአንድ ሰዓት (መዝ.35÷4-5) በሦስት ሰዓት (መዝ.119÷154-155) በስድስት
ሰዓት (መዝ.18÷17-18) በዘጠኝ ሰዓት (መዝ.25÷1-2) በ11 ሰዓት
(መዝ.45÷6-7)
.
ዛሬም ቢሆን መልካም ሥራ በሠራን ቁጥር አሳለፈው ሲሰጡን የሚፈልጉ ሰዎች
ተፈታታኝ ጥያቄ እንደሚያቀርቡልን ከወዲሁ ልንገነዘብ ይገባል፡፡ እንዲያውም
ፈታኝ ጥያቄዎች የመከራ ዋዜማ ናቸው ለማለት ይቻላል፡፡ ይህን አስቀድመን
ካወቅን በመከራ ሰዓት እንኳ በልበ ሙሉነት እውነትን በመናገር ለሚጠየቀው
ጥያቄ ሁሉ ተገቢውን መልስ በመስጠት ሥራችንን መሥራት እንችላለን፡፡
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ውሉደ ብርሃን ሰንበት ትምህርት
ቤት
@embtee @embtee @embtee

✞ሐሙስ✞
* ከስቅለትና ከትንሣኤ በፊት ያለው ሐሙስ በቤተክርስቲያናችን የተለያዩ ስያሜዎች አሉት።
1. ሕጽበተ እግር ይባላል።
ይህ ስያሜ የተሰጠው ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀመዛሙርቱን እግር
በማጠቡ ምክንያት ነው። ይህም የሚያሳየው የዓለምን ኃጢአት
ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው። ይህንን ለማስታወስ ዛሬ ካህናት
በተለይም ሊቃነ ጳጳሳት በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝቡን
ኃጢአት እጠብ ሲሉ ሲሉ በቤተ ክርስቲያናችን የተገኙትን ምእመናን
እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ሲያጥቡ ያረፍዳሉ። / ዮሐ.13:4-15/
2. የጸሎት ሐሙስ ይባላል።
የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ የሚደክም ሥጋን የተዋሐደ
አምላክ ፍፁም ሰው መሆኑን ለመግለጽና ለአርአያነት ጠላቶቹ
መጥተው እስኪይዙት ድረስ በጌቴሴማኒ ሲጸልይ በመቆየቱ ነው /ማቴ
26:36 ፤ ዮሐ 17:1/
3. የምስጢር ቀንም ይባላል።
ከሰባቱ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን አንዱ በዚህ ዕለት ተመስርቷል።
ይኸውም ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ስጋዬ ነው፤
እንካችሁ ብሉ ጽዋውንም አንስቶ አመሰገነ ይህ ስለ እናንተ ነገ
በመስቀል ላይ የሚፈስ ደሜ ነው፤ ከእርሱም ጠጡ በማለት እኛ
ከእርሱ ጋር አንድ የምንሆንበትን መንገድ ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ
ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመሆኑ የተሰጠ ስያሜ ነው።
~ በዚህ ዕለት ቅዳሴ ይቀደሳል። የሚቀደሰውን በለሆሳስ /በዝግታ/
ሲሆን እንደ ቃጭል በመሆን የሚያገለግለውም ጽናጽል ነው። ይህም
አይሁድ ጌታችንን ለመያዝ ሲመጡ ድምፃቸውን ዝግ አድርገው
በለሆሳስ እየተነጋገሩ መምጣታቸውን ለማሰብ ነው።
~ በቅዳሴውም ኑዛዜ አይደረግም። ሥርአተ ቁርባን ግን
ይፈጸምበታል። ይህም ጌታችን የሰጠውን ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን
ለማሰብ ነው። በዚህ ዕለት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በንስሀ ታጥቦ
ተዘጋጅቶ ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል ይኖርበታል።
4. የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል።
ምክንያቱም መስዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንሰሳ ደም የሚቀርበው
መስዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኀነቱ ዓለም ራሱን የተወደደ
መስዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ ነው። /ሉቃ 22:18-20/
ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው ደሜ የሚሆን የአዲስ ኪዳን ነው።
ከእርሱም ጠጡ በማለቱ ይታወቃል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘላለማዊ ቃል ኪዳን በራሱ ደም
የፈጸመበት ዕለት መሆኑን በማሰብ የቃል ኪዳኑ ፈጻሚዎች ጠባቂዎች
መሆን እንደሚገባን እንማራለን።
5. የነጻነት ሐሙስ ይባላል።
ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባርያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ፤ የሰው ልጅ
ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው። ራሱም
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጅ ነፃነት ሲናገር
ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባሪያ ጌታው የሚደርገውን
አያውቅምና፤ ወዳጆቼ ግን ብያችኋለሁ በማለቱ /ዮሐ 15:15/
ከባርነት ነፃ የወጣንበት ቀን መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ
ያስረዳል። ስለዚህ እያንዳንዱ ክርስቲያን ከኃጢአት ባርነት በመራቅ
ከእግዚአብሔር ሕይወቱን በቅድስና መምራት ይኖርበታል። እርሱ
ጠላቶቹ ስንሆን ወዳጆቹ አድርጎናል። /ማቴ 26:17-19/
6. አረንጓዴው ሐሙስ ይባላል።
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአትክልት ቦታ ስለ ጸለየ።
@embtee @embtee

..7ኛ. ቅዳሜ….
.
ከስቅለት በኋላ ያለው ይህ ቅዳሜ በተለያየ ስያሜ ይጠራል፡፡ ይኽውም ‹‹ቀዳም
ስዑር›› ዐቢይ ሰንበት ቅዱስ ቅዳሜ እየተባለ ነው፡፡
.
1. ቀዳም ስዑር ይባላል፡፡ ይህ ስያሜ ሰንበት በአይሁድ መሻሩን ያመለክታል፡፡
2. ዐቢይ ሰንበት ይባላል፡፡ ሰንበት ዕረፍት ማለት ስለሆነ ይህም ቀን ጌታችን
ሁሉንም ሥራ ፈጽሞ በመቃብር አርፎበታልና ትልቁ ሰንበት ለማለት ዐቢይ
ሰንበት ተብሏል፡፡
3. ቅዱ ቅዳሜ ይሉታል፡፡ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ጌታን በመቃብር ያኖሩት በማዘጋጀቱ
ቀን ዓርብ
.
ማታ ሰንበት ሲጀምር ሲል ነበር፡፡ ቅዳሜም ከገባ በኋላ እንደ ትዕዛዛቱ ሰንበት
ስለሆነ አረፉ፡፡ (ሉቃ.23÷56)
.
ሐዋርያት ጌታችን ከተያዘ ጊዜ ጀምሮ እስከ ትንሣኤ ድረስ እህል አልበሉም
በዚሀም መሰረት በቤተክርስቲያናችን ከዓርብ ጀምሮ እስከ ትንሣኤ ድረስ እህል
አይበላም፡፡ ይህም አክፍሎት ተብሎ ይጠራል፡፡ ሕዝቡ ከጾመው ምግብ በካህኑ
በኩል ለድሆች ማካፈል እንደሚገባው ያመለክታል፡፡ ጌታችን ‹‹ሙሽራው
የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል ያን ጊዜ ይጾማሉ›› ብሎ አስቀድሞ ተናግሯል፡፡
(ማቴ9÷15)
.
በዚህ ዕለት ሞተ ወልደ እግዚአብሔርን የምናስብበት ብርሃነ ትንሣኤውን
የምንናፍቅበት ቀን መሆኑን አንዘንጋ፡፡

በትንሣኤ በዓል እርድ መከናወን ያለበት መቼ ነው?
ብዙ ሰዎች የቀዳም ስዑር ምሽት ዶሮ፣ በግ፣....ወዘተ ያርዳሉ። በዚህ ዕለት ማረድ በልማድ ተያይዞ የመጣ እንጂ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንም ሆነ ትውፊቱ አያዝም። በቀዳም ስዑር ለምን እንደሚያርዱም ሲጠየቁ "ለበዓሉ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ፣ ሌሊት ከቤተ ክርስቲያን አስቀድሰው ሲመለሱ ለመግደፍና ነዳያንን ለማፈሰክ ነው" በማለት ይመልሳሉ። ሊቃውንቱ ሲያትቱ ግን ዝግጅት የሚያስፈልጋቸው የሚባሉት በባህርያቸው የሞቱ ለምንላቸው ምግቦች ነው። ማለትም እንጀራ፣ ዳቦ...ወዘተ። ምክንያቱም እነዚህን ለማዘጋጀት ብዙ ጊዜ የሚፈልግ ነውና። እንስሳት ግን ደመ ነፍስ ናችው። እንስሳን ለማረድ ዝግጅት አይጠይቅም፤ ወዲያው የሚታረዱ ናቸው። ነዳያንን ማስፈሰክ ለተባለውም ተንሥኣ እሙታን ከሚባልበት ከመንፈቀ ሌሊት በኋላ ተሠርቶ የሚደርስ ነው።
በዓሉን በማስመልከት ባለን ዐቅም እርድ የምናርደው የደስታ፣ የምሥራች መግለጫ ነው። ደስታችንን የምንገልጸው ደግሞ ጌታችን ከተነሣ በኋላ ነው። የትንሣኤያችን የምሥራች የተሰበከልን በጌታችን ትንሳኤ ምክንያት ነውና። ስለዚህ <<ወተንሥአ እሙታን፤ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፤>> ተብሎ ዐዋጅ ሳይታወጅ መታረድ የለበትም። በቀዳም ስዑር ማረድ ዐዋጅ ሳይታወጅ ከማረዳችንም በላይ የትንሣኤን በዓል አላከበርንም እንደ ማለት ነው። የጌታችን ትንሣኤ የምሥራች እስከ ሚነገርበት ሰዓት ድረስ ስመ ሥላሴ አይጠራም። ታድያ በቅዳሜ ምሽት በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ሳይባል፣ በመስቀል ሳይባረክ ማረድ በዘመነ ኦሪት እንደታረደ ፣/እንደተሠዋ/ ነው የሚቆጠረው። ምክንያቱም "ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን" አልተባለምና።
እንደ ሊቃውንቱ አገላለጽ ሌሊት ከቅዳሴ መልስ በየቤታችን ልንመገበው የሚገባ ከጥሉላት ምግቦች ርቀን ከመቆየታችን አንጻር ጤንነታችንን የማይጎዳ ማር፣ ተልባ፣ ወተት በእርጎ ተደርጎ ነው የሚበላው። እርድ መፈጸም ያለበት ጠዋት ወይም ደግሞ ከሌሊቱ 6፡00 በኋላ ነው። ያኔ መስቀል ይዞራልና። አንዳንድ ሰዎች ሲናገሩ ቀዳም ስዑር ጾም መሆኑን አምናለሁ። ነገር ግን ከምሽቱ 11፡00 /ከዋዜማው/ ጀምሮ ወደ ሚቀጥለው ቀን /እሑድ/ ስለሚቆጠር ማረድ ይቻላል ይላሉ። ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ለዚህ ሲመልሱ፦ ፍትሐ ነገሥቱ በአቀጸ ጾም ላይ "ክብርት በምትሆን በ፵ ጾም በመጀመሪያው ሱባኤ እስከ 12 ሰዓት፣ ከቅድስት ጀምሮ እስከ ኒቆዲሞስ ዓርብ እስከ 11 ሰዓት፣ በሰሙነ ሕማማት እስከ 13 ሰዓት /ከሌሊቱ አንድ ሰዓት ጨምሮ ወይም እስከ ፀአተ ኮከብ -ኮከብ በሰማይ መልቶ እስኪታይ/ ጹሙ" ይላል። ቅዱሳት መጻሕፍትም ለጾም ማድላት እንዳለብን ይመክሩናል። ከምሽቱ 11፡00 ጀምሮ ወደ ሚቀጥለው ቀን /ወደ ማግሥቱ/ ነው የሚቆጠረው የሚባለው ለምስጋና ሲሆን ነው። ለምሳሌ፦ በዋዜማ ምሥጋና ለነገ የበዓሉ መዳረሻ /መግለጫ/ እንዲሆን ማለት ነው። ጾም ግን ወዲያውኑ በተግባር /በድርጊት/ የሚፈጸም ነው። ወደ ማግሥቱ ይቆጠራል አንልም፤ ምክንያቱም ጾም ተግባር ነውና። @embtee
በተጨማሪም ቅዱሳት መጻሕፍትም የሚያዙት "የሚቻላችሁ ከሆነ ከዚህ አብልጣችሁ ጹሙ" ነው የሚሉን። ይልቁንም የጾማችንን ጊዜ ከዕለት ወደ ዕለት ከፍ እያደረግን ልንሄድ ይገባናል እንጂ በየምክንያቱ ከነበርንበት ልንቀንስ አይገባም። የሰው ልጅ በረከት፣ ስርየተ ኃጢአት፣ ድኅነት፣ የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት ራሱን ለሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መገዛት ማስገዛት ካልቻለ ከፈጣሪው ጋር አንድነት አይኖረውም። ፈቃደ ነፍስን ለመፈጸም የምታበረታታ ደገኛ ሕግ ደግሞ ጾም ናት።" በአጠቃላይ በቀዳም ስዑር ማረድ የጾም ክፍል በኾነው ሰዓት ከማረዳችን በተጨማሪ የትንሣኤን ምሥራች አይሰብክም። ምክንያቱም ጌታችን እስኪነሣ ድረስ በኅዘን ነው ያለነው፤ እንደ ሥርዓቱ ከሆነ ሲታረድ ካህኑ ቢላዋውን ይባርክለታል ፥ አራጁ ያርዳል፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሙስና መቃብር አጥፍቶ ተነሥቷልና፤ "ክርስቶስ ተንሥኣ እሙታን" ተብሎ ዐዋጅ ተነግሯልና። ስለሆነም በቀዳም ስዑር ምሽት ማረድ በልማድ የመጣ እንጂ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት አይደለም።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን ይቆየን

Forwarded from ✿✟ የ҈ ዳ҈ ዊ҈ ት҈ ዜ҈ ማ҈ ✟✿
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን አሜን ።🌹💐🌼🌷🌸🌹🌺
" አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:20)
🌺🌹💐🌷🌼🌸💐🌹🌺
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዓብይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አጋአዞ ለአዳም
ሠላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍሥሐ ወሠላም
በዓሉ የተጣሉ የሚታረቁበት የታመሙ የሚድኑበት የታሰሩ የሚፈቱበት .... ለሀገራችን ለወገናችን ለመላው ዓለም ሁሉ ፍቅር ሰላም አንድነት የሚሰፍንበት በዓል ያረግልን ዘንድ የቅዱሳን አምላክ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን አሜን ።
ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ
ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ
ምደር ጸዳች ሐሴት አደረገች
በክርስቶስ ደም በእውነት ታጠበች
መ 💐 ል 🌹 ካ 🌷 ም
በ 🌷 አ 🌹 ል
🌹💐🌺🌷🌹💐🌺🌼🌸🌼🌺💐🌹🌷
@embtee @embtee
@embtee @embtee 👈👈

Watch "የዶ/ር ቀሲስ ዘበነ ለማ አዲስ ስብከት+++በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና (2ኛ ቆሮንቶስ 2:11) Dr. Kesis Zebene" on YouTube
https://youtu.be/yvREe1Cpyog
https://youtu.be/yvREe1Cpyog
YouTube
የዶ/ር ቀሲስ ዘበነ ለማ አዲስ ስብከት+++በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና (2ኛ ቆሮንቶስ 2:11) Dr. Kesis Zebene
የዶ/ር ቀሲስ ዘበነ ለማ አዲስ ስብከት+++በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና (2ኛ ወደ ቆሮንቶስ 2:11) Dr. Memher Kesis Zebene