✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.2K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
ገብር ኄር።
+×+×+×
መክሊቴ ሲቆጠር።
+×+×+×+×+×+×
ባለጠጋ ንጉሥ እጅግ የከበረ እሩቅ መንገድ ሊሄድ፣
ወዳጆቹን ጠርቶ የቤቱን ሹመኞች እንደ ራሱ ልማድ፣
አደራ ሰጣቸው ታምነው እንዲገኙ ሆነውለት ዘመድ፣
እንደየ አቅማቸው በእምነት በምግባር አትርፎ መነገድ።
+×+×+×+×
በእምነት ምግባሩ ጌታውን አክብሮ የኖረ በፀጋ፣
እላይ ታች ብሎ ለፍቶ በዚህ ዓለም አጥብቃ የተጋ፣
ነግዶ አትርፎ መክሊቱን አብዝቶ ምህረቱን ፍለጋ፣
ፀንቶ የተገኘ በዝቶ ያገኘዋል የንጉሡን ዋጋ።
+×+×+×+×
በዚህ የንጉሥ ቃል ባሮቹ ተነስተው ሳይሆኑ ቃለ በይ፣
ለሥጋ ያማረ ኃጢአትን አትርፎ ይህ ዓለም አታላይ፣
ከቶ እንዳይጥላቸው መክሊታቸውን ወስዶ የሕይወትን ሲሳይ፣
አትርፈው ነገዱ አብዝተው ዘሩና ቃሉን ልባቸው ላይ።
+×+×+×+×+×
ቃሉን ያከበሩ ተግተው በዚህ ዓለም በምግባር በሃይማኖት ፣
ታምነው በጥቂቱ ነግደው አትርፈው የንጉሡን መክሊት፣
ይዘው የተገኙ ሁለቱን በሁለት አምስቱን በአምስት፣
አባዝተው አብዝተው ተሾሙ በክብሩ በላይኛው ቤት።
+×+×+×+×+×
ትዕዛዙን ሳይሰማ ጌታውን ሳያከብር በትዕቢት የኖረ፣
ሕይወቱን የረሳ መክሊቱን አጥፍቶ ከአፈር የቀበረ፣
ኃኬተኛ አገልጋይ በተሰጠው መክሊት ራሱን ያልቀየረ፣
አሳዳሪው ጌታ ባዶ የሚያገኘው እንደ ተማረረ፣
ፀጋው ተገፎበት ያለው ተቀምቶ በሞት እጅ ታሰረ።
+×+×+×+×+×
የጭንቅ ቀን ሳይመጣ ጎድሎብኝ መክሊቴ ወጥቼ እንዳልቀር፣
ወገቤን ታጥቄ መብራቴን አብርቼ በእምነት በምግባር፣
ዘይቴን ሞልቼ ጌታዬ ሲመጣ መክሊቱ ሲቆጠር፣
ሳላተርፍ ቀርቼ እንዲሁ ስባዝን በዚህ ዓለም ለመኖር፣
ፈጥሮ እንዳልፈጠረኝ አላውቅህም ብሎኝ እንዳልወረወር፣
ሩጫዬንም ልሩጥ ትግሌንም ታግዬ የጽድቅ አክሊል ላኑር፣
በራሴ ደፍቼ ዘለዓለም ለብሼው የወንጌሉን ጥሩር።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEzwE8Rx0_ELfmMHsg
ስድስተኛ ሳምንት #ገብርኄር

እንኳን አደረሳቹ

መልካም ዕለተ ሰንበት

@embtee @embtee
@embtee @embtee
በደብተራ ኦሪት ታቦተ ጽዮንን እንዲያገለግሉ
የተመረጡት ሁለቱ ካህናት ስማቸውን ማን ይባላል አባታቸውስ ማነው???
ሰላም የቻናላችን ተከታታዮች በቻናላችን ያሎትን አስተያየት

0⃣ይጨመር
1⃣ይቀነስ
2⃣ቢስተካከል
3⃣አብረን እንስራ ለምትሉን
4⃣ለቻናላችን የተሻለ ሀሳብ አለን ለምትሉ
4⃣ለማንኛውም አስተያየት ለመላክ 👇👇👇
ዲ/ናት ፣ ካህናትና ጳጳሳት ብቻ የሚገቡት የቤተክርስቲያን ክፍል ምን ይባላል ??
እንደምታደርጉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ከዚህ ወራት አስቀድሞ
ቴዎዳስ። እኔ ታላቅ ነኝ ብሎ ተነሥቶ ነበርና፥ አራት መቶ የሚያህሉ ሰዎችም
ከእርሱ ጋር ተባበሩ፤ እርሱም ጠፋ የሰሙትም ሁሉ ተበተኑ እንደ ምናምንም ሆኑ።
ከዚህ በኋላ ሰዎች በተጻፉበት ዘመን የገሊላው ይሁዳ ተነሣ ብዙ ሰዎችንም
አሸፍቶ አስከተለ፤ እርሱም ጠፋ የሰሙትም ሁሉ ተበታተኑ። አሁንም እላችኋለሁ።
ከእነዚህ ሰዎች ተለዩ ተዉአቸውም፤ ይህ አሳብ ወይም ይህ ሥራ ከሰው እንደ
ሆነ ይጠፋልና፤ ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ ግን ታጠፉአቸው ዘንድ አይቻላችሁም፥
በእርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ ምናልባት እንዳትገኙ።ሰሙትም፥
ሐዋርያትንም ወደ እነርሱ ጠርተው ገረፉአቸው፥ በኢየሱስም ስም እንዳይናገሩ
አዝዘው ፈቱአቸው።እነርሱም ስለ ስሙ ይናቁ ዘንድ የተገባቸው ሆነው ስለ
ተቈጠሩ ከሸንጎው ፊት ደስ እያላቸው ወጡ፤ ዕለት ዕለትም በመቅደስና
በቤታቸው ስለ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ማስተማርንና መስበክን
አይተዉም ነበር።
እግዚአብሔር አብርሃምን የጠራው ከምንድን ነው
የተጠራውስ ከየትኛው ሃገር ነው???
ለምን እንሰግዳለን ?

ለምንስ እንዘምራለን ?

ዲያቆን ሸዋፈራው አለነ
ይህንን ፅሁፍ ልጽፍ የቻልኩበት አብይ ምክንያት ‹‹ተሐድሶ ለኦርቶዶክስ››
በተሰኘው ጉሩፕ ውስጥ በፌስ ቡክ ስሙ በግሪክኛ (በፅርዕ)ቋንቋ ‹‹መለኮታዊ
ቃል ወይም ሎጎስ›› የተባለው ሰው ‹‹መልስ ለዲያቆን ሸዋፈራሁ›› በሚል
‹‹ለምን አንሰግድም? ለምንስ አንዘምርም ?››በሚል ርእስ ለቅዱሳኑ
‹‹የማይዘምሩበት›› እና ‹‹የማይሰግዱበትን ›› አመክንዮአዊ መከራከሪያ
በማቅረቡ እኔ ደሞ ‹‹ለምን እንሰግዳለን ለምንስ እንዘምራለን ››በሚል
ለቅዱሳኑ ‹‹የምንሰግድበትን››እና ‹‹የምንዘምርበትን ›› መጽሐፍ ቅዱሳዊ
ምክንያት መንፈስ ቅዱስን አስቀድሜ አንድ በአንድ ለመከራከሪያነት ያነሳውን
ሐሳብ መልስ ልሰጥበት ነው ፡፡
ልጁ በጽሁፉ መግቢያ ላይ ‹‹በትኩረት ይነበብ!!!!›› የሚል ማሳሰቢያ
ስላስገባበት እኔም ደግሞ ፅሁፉን በትኩረት ለማንበብ እንደው ከሌሎቹ
ፕሮቴስታንቶች የተሻለ ጽሁፍ ያቀርብ ይሆን ብዬ ወደፅሁፉ ገባሁ፡፡‹‹ወንድም
ሸዋፈራሁ ከወራት በኋላ ስለተገናኘን ደስ ብሎኛል፡፡ከሙስሊሞች ወዳንተ ዘወር
ያልኩት በዚህ ግሩፕ ፖስት ያደረግካት አንዲት የስህተት ትምህርት ግርምትን
አጭራብኝ ነው፡፡ እኛ የወንጌላውያን አማኞች ከጌታ በቀር ለማንም አንሰግድም ፣ @embtee
አንዘምርም ማለታችንን ከምንፍቅና መቁጠርህ እንዲያው በጨበጣ የሚቆምር
አስመስሎሀል፡፡ ›› ከወራት በፊት የት እንዴት እንደተገናኘን ባላስታውስም !
ሙስሊሞችን እና ፕሮቴስታንቶችን ለይቼ አላያቸውም ምክንያቱም ሙስሊሞች
ጌታችን ኢየሱስን ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና ፍጡር ተራ ነብይ
ሲሉት ፕሮቴስታንቶችም በቃል ብቻ በሚለይ መንገድ ከባህሪ አባቱ ከአብ
ከባህሪ ህይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ አሳንሰው ሁሉን ቻይነቱን ክደው አማላጅ
(ለማኝ) ሲሉት ይታያሉ እና ነው !! እንደው ከሰው ስህተት ከብረት ዝገት
አይጠፋምና ‹‹የስህተት ትምህርት ፖስት አደረክ ›› ሲለኝ ‹‹የስህተት ትምህርቴን
››ላርም እኔም ልታረም አስቤ ነበር ፡፡ደግሞ ‹‹ግርምት አጭራብኝ ››ሲል !!
ሊገረም እንጂ ሊያርመኝ እንዳልተነሳ መልሶ ገባኝ !! ‹‹እኛ ወንጌላውያን ››ሲል
እንደው ይሔ ‹‹ወንጌላዊነት›› በየቦታው የሚጣል ስመ ግብር ሆነ እንዴ ብዬ
ተደመምኩ፡፡ግማሹ ጥቂት እንኳን ሳይተነብይ ‹‹የሞባይላችሁ ቁጥር 09…….
ነው (ከአንዱ ጠይቆ አልያም አንድ ቀን ነግረነው ሊሆን ይችላል እኮ ) ››ሲል በቃ
ነብይ ነው ልክ ነው ይባላል ፡፡አንዱ የሐዋርያነት ግብር ሳይኖረው ‹‹ሑሩ
ወመሃሩ››የሚለውን የጌታ ትእዛዝ ሳይፈጽም ‹‹ሐዋርያ ነኝ ›› ይላል ፡፡
ያልዋለበትን ያልደረሰበትን ስመ ግብር ይዞ እናገኘዋለን ፡፡ወንጌልን በቅጡ
የማታምን ቤተ እምነትም ‹‹ወንጌላዊት ››ተሰኝታለች ፡፡ይደንቃል!! ‹‹ከጌታ በቀር
ለማንም አንሰግድም ለማንም አንዘምርም ማለታችን ምንፍቅና አድርገህ
መቁጠርህ እንደው በጨበጣ የሚቆምር አስመስሎሐል ››ስትለኝ ደነገጥኩ !
እንደው እኔ እስከማምነው ወንጌል እየሰበኩ እምነቴን እየገለጥኩ ነበር እንጂ
እየቆመርኩ አልነበረም !! ለካ እናንተ እቆመራችሁ ኖሯል?ለካ ወንጌል ለእናንተ
ቁማር ነው !!ይህን መቼ አውቄ!
‹‹በመሰረቱ ለአንድ ሰው <መናፍቅ > የሚል ስያሜን ለመስጠት መጠናት
ያለበት መሰረታዊ ነገር በክርስቶስ ላይ ያለው እምነት ፤ (ማለትም አምላክነቱን ፣
የእግዚአብሔር ልጅነቱን ፣ መሰቀሉንና ከሞት ተነስቶ ማረጉን ፣ በደሙ ሰዎችን
ከእግዚአብሔር ማስታረቁን ፣ዳግመኛም ለፍርድ መምጣቱን ) የመሳሰሉት
ነገሮች ላይ ያለው ምልከታ እንጂ ለማርያም ለምን አልዘመርክም በሚል
folklore ተነስቶ ሰውን መናፍቅ ማለት በራሱ ምንፍቅና መሆኑን ላሳስብህ
እወዳለሁ፡፡ አሁን ወደጉዳዬ ልግባ ፦፦፦›› ላልከው ፡፡ በተወሰነ ደረጃ እውነትነት
ቢኖረውም ስለ ክርስቶስ ስለ ሥላሴ ……..አንድ ሰው /ቤተእምነት / ያለው
እምነቱ መናፍቅ ከሀዲ አህዛብ የሚያሰኘው ቢሆንም ፡፡መፅሐፍ ቅዱስ
የሚለውን የሚቀንስ ብሎም የማይፈጽም መናፍቅ ተብሎ ይጠራል ፡፡ምክንያቱም
መናፍቅ ማለት ከፍሎ አማኝ ማለት ስለሆነ ፡፡ስለዚህ ለቅዱሳን የሚገባውን የጸጋ
ስግደት እና የጸጋ ዝማሬ የሚቃወም ብሎም የማይፈጽም መናፍቅ ተብሎ
ይጠራል ምክንያቱም መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ለቅዱሳን የዘመሩ ቅዱሳንን
በሚገባቸው መንገድ ያከበሩ ስላሉና መፅሐፍ ቅዱሱም በሚገባቸው መንገድ
እንድናከብር ስለሚያዘን ፡፡እኔም ወደጉዳዬ ልግባ !!
‹‹➊ለምን ለፍጡራን አንሰግድም?.... ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ሩቅ መጓዝ
ሳያስፈልገን የመፅሀፍ ቅዱሳችንን የመጨረሻ ገፅ በመግለጥ መረዳት ይቻላል፡፡
" እርሱም። እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር
የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ
አለኝ።"
(የዮሐንስ ራእይ 22:9) በዚህ ክፍል የተፃፈው ነገር ለሌሎች <ቅዱሳን>
ፍጡራን እንዳንሰግድ ያስጠነቅቀናል፡፡ እስቲ ጥቂት አመክንዮ ላክልልህ ፦
1ኛ)ዮሀንስ የኢየሱስ ሀዋርያ በመሆኑ የሚሰራውን ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ስለዚህ
ለመልአኩ የሰገደው የአምልኮ ስግደትን ሳይሆን እናንተ <የአክብሮት>
የምትሉትን አይነት ነው፡፡ @embtee
2ኛ) መልአኩ ቅዱስ መልአክ እንደመሆኑ ዮሀንስ የአምልኮ ስግደትን
እንዳልሰገደለት ጠንቅቆ ያውቃል፡፡
ይህም ሆኖ ግን መልአኩ ለሱ ይህ የአምልኮ ያልሆነ ስግደት
እንደማይገባውና የመፅሀፉን ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሮ ባሪያ እንደሆነ ተናግሮ
ሀዋርያውን አስጠነቀቀው፡፡ ታዲያ ያንተ <ቅዱሳን> ከዮሀንስ እና ከመልአኩ
በልጠው የዚህ ቃል ባሪያዎች ከመሆን ያለፉ ናቸውን? ፍርዱን እውነትን ለሚሹ
ትቼዋለሁ፡፡ እኛ ግን በዚህ ምክንያት ለፍጡራን አንሰግድም፡፡ ››
ለምን ለቅዱሳን እንሰግዳለን ? ይህንን ጥያቄ ለመመለስ አንዳንተ ሌላውን
የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ችላ ብለን እና ትተን ወደመጨረሻው የመፅሐፍ ቅዱስ
ክፍል መሄድ ብቻ ሳይሆን የሚጠበቅብን ሙላውን ማየት ይኖርብናል ፡፡ እኛ
ኦርቶዶክሳውያን ለቅዱሳን የምናቀርበው የጸጋ ስግደት መጽሐፍ ቅዱስን አብነት
አድርገን ነው ፡፡በኦርቶዶክሳውያን ዘንድ ለመላእክትና ለቅዱሳን የሚደረግ
ስግደት፣ ለቅዱሳኑ ካለን ፍቅርና አክብሮት የሚመነጭ ነው፡፡ ለእግዚአብሔር
የአምልኮት ስግደት እንሰግዳለን፤ ለቅዱሳንና ለመላእክት የጸጋ፣ የአክብሮት
ስግደት እንሰግዳለን፡፡ ስንሰግድም ምን ዓይነት ስግደት እንደምናቀርብላቸው
በልባችን በህሊናችን እናውቃለን፤ ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም
አንቺ ፈጣሪዬ ነሽ፤ አምላኬ ነሽ እያለ የሚሰግድ ኦርቶዶክሳዊ የለም፡፡ ይህ
ፍጹም ስህተት ነው፤ ኃጢያትም ነው፡፡ የመድኃኔዓለም እናት ድንግል ማርያም፤
አንቺ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ እያልን በቅዱስ ገብርኤልና በቅድስት
ኤልሳቤጥ ምስጋና እያመሰገናት ግን እንሰግድላታለን፡፡ ቅዱሳን መላእክትና
ጻድቃንንም እንደየ ማዕረጋቸው እንዲሁ ለነርሱ ያለንን ፍቅርና አክብሮት
እየገለጽን እንሰግድላቸዋለን፡፡‹‹ ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ።
በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ
ተደፋሁ፤ እርሱም እንዳታደርገው ተጠንቀቅ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህ ከነቢያት
ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁት ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፡፡ ለግዚአብሔር
ስገድ አለኝ ፡፡ ››ራእ.22፡9 አንተ እንደምትለው ይሄ ጥቅስ ለቅዱሳን የጸጋ
ስግደት እንዳንሰግድ ማስረጃ ሆኖ የሚቀርብ አይደለም፡፡ያቀረብከው አመክንዮ @embtee
(ሎጂክ) የሚያስኬድም አይደለም!!አን
ድ ቁጥር አድርገህ ያስቀመጥከው
መከራከሪያ ሀሳብ ‹‹1ኛ)ዮሀንስ የኢየሱስ ሀዋርያ በመሆኑ የሚሰራውን ጠንቅቆ
ያውቃል፡፡ ስለዚህ ለመልአኩ የሰገደው የአምልኮ ስግደትን ሳይሆን እናንተ
<የአክብሮት> የምትሉትን አይነት ነው፡፡ ››ላልከው አዎ ልክ ነው የአምልኮ
ስግደትን ሳይሆን የአክብሮት ስግደትን እንደሰገደ ዮሐንስ ጠንቅቆ ያውቃል ፡፡
እንዳንተ አባባል ቅዱስ ዮሐንስ ያቀረበው ስግደት ከእኛ ጋር የሚመሳሰል ብሎም
አንድ የሆነ የጸጋ ወይም የአክብሮት ስግደት ነው ማለት ነው ፡፡ዮሐንስም
ለመልአኩ ሲሰግድ መልአኩን እያመለከው ሳይሆን ከግርማው የተነሳ
እያከበረው ነው ፡፡
‹‹2ኛ) መልአኩ ቅዱስ መልአክ እንደመሆኑ ዮሀንስ የአምልኮ ስግደትን
እንዳልሰገደለት ጠንቅቆ ያውቃል፡፡
ይህም ሆኖ ግን መልአኩ ለሱ ይህ የአምልኮ ያልሆነ ስግደት
እንደማይገባውና የመፅሀፉን ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሮ ባሪያ እንደሆነ ተናግሮ
ሀዋርያውን አስጠነቀቀው፡፡ ታዲያ ያንተ <ቅዱሳን> ከዮሀንስ እና ከመልአኩ
በልጠው የዚህ ቃል ባሪያዎች ከመሆን ያለፉ ናቸውን? ፍርዱን እውነትን ለሚሹ
ትቼዋለሁ፡፡ እኛ ግን በዚህ ምክንያት ለፍጡራን አንሰግድም፡፡ ››ይህቺ ሐሳብህ
ግን የተምታታች ናት ምክንያቱም ቅዱስ ዮሐንስ የአክብሮት ስግደት
እንደሚገባው ለመልአኩ አውቆ ሰገደ ብለህ ስግደቱ የአምልኮ ሳይሆን
የአክብሮት ወይንም የጸጋ መሆኑን ተቀብለሀል ፡፡መልአኩም ዮሀንስ ያቀረበለት
ስግደት የአምልኮ ሳይሆን የአክብሮት እንደሆነ እንደሚያውቅ ተናግረሀል ፡፡
ስለዚህ በዚህ ሀሳብህ ለቅዱሳን የማትሰግድበት ምክንያት ሊሰገድላቸው
የሚገባ ሳይሆኑ ቀርተው ሳይሆን አብረው ከአንተ ጋር ‹‹ባርያ››ስለሆኑ ብቻ ነው
የማትሰግደው ማለት ነው ፡፡መልአኩ ‹‹የቃሉ ባርያ ነኝ ››ሲል ‹‹የቃሉ አገልጋይ ነኝ
››ማለቱ ነው ፡፡በአገልግሎት ውስጥ ደግሞ የተለያየ ጸጋ አለ ፡፡ጸጋ ለሁሉም
አንድ አይነት እና በእኩል ደረጃ አይሰጥም ፡፡1ቆሮ12፡4-28፤ 1ቆሮ3፡10
ለቅዱስ ዮሐንስ የተሰጠው ጸጋ መጠን ግን ከመልአኩ ክብር እኩል እንደሆነ
ልንገምት እንችላለን ምክንያቱም የመልአኩን ምክንያት ከራሱ አንደበት ስንሰማ፣ @embtee
ከአንተ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ ነው ያለው፡፡ መልአኩ የዮሐንስን ክብር ከራሱ ክብር
ጋር ማነጻጸሩን ልብ ይሏል፡፡ ኃጢያት ስለሆነ፣ ሳላወክ፣ ስለተሳሳትክ፣
ወዘተ…..ማብራሪያ ከመልአኩ ምክንያት ምን ያህል የራቀ እንደሆነ ልብ ይሏል!፡፡
ይህ ጥቅስ የትኛውም የቅድስና ማዕረግ ላይ ያሉ ቅዱሳን በመካከላቸው
ያለውን መከባበርና ፍቅር ያሳየናል፡፡ በተለይም መልአኩ እኔም ከአንተ ጋር አብሬ
ባሪያ ነኝ አትስገድልኝ ያሰኘው የዮሐንስ ክብር እንዴት ታላቅ ቢሆን ነው ብለን
እንደመማለን፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ለመላእክት የሰገዱ በርካታ ናቸው፡፡ ዳንኤልም
እንደ ዮሐንስ መልአክ ተገልጾለት ስለመጨረሻው ዘመን በራእይ ተገልጾለታል፤
ለመልአኩም በሰገደለት ጊዜ ግን አይዞህ ብሎ አነሳው እንጂ አትስገድልኝ
አላለውም፡፡ ዳን8፡17 በዚሁ አንጻር መልአኩ ለኢያሱ ተገልጦ በሰገደለት ጊዜ
መልአኩ አልተቃወመውም ኢያ5፡14 ሎትም ሲሰግድ እንደዚሁ መላእክቱ
አልተቃወሙትም ፤ዘፍ19፡1እንዳንተ አባባል ከሆነ መላእክቱ ሎጥ እና ኢያሱ
ሲሰግዱላቸው መላእክቱ ለምን አልተቃወሙም? በጣም የሚደንቀው ደግሞ
ቅዱስ ዮሐንስ በሌላም ጊዜ ለመልአኩ መስገዱ ነው፡፡ በራዕ.19፣10 ላይም
ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ፤ እርሱም እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤
ከአንተም ጋር የኢየሱስ ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፡፡
መቼም ትክክል ባይሆንም ዮሐንስ አንድ ጊዜ ተሳሳተ እንበል፤ እንዴት በድጋሚ
ሰገደ? @embtee
‹‹★★ በተጨማሪም ኢየሱስ ሲናገር <እግዚአብሄር # መንፈስ ነው ፣
የሚሰግዱለትም በእውነትና # በመንፈስ ሊሰግዱለት ይገባል> ዮሀ4:24
ብሎናል፡፡
እስቲ ይቺን መልስልኝ ፦ አንተ የምትሰግድላቸው <ቅዱሳን> በዚህ ሰአት
በመንፈስ ናቸው ወይስ በስጋ?
የት አይተሀቸውስ ሰገድክላቸው? ቃሉ በመንፈስ የሚሰገደው ለእግዚአብሔር
እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ስለዚህ መታረም ይገባሀል፡፡›› ልክ ነው እግዚአብሔር
የሚሰገድለት በእውነት እና በመንፈስ ነው በእውነት እና በመንፈስ ይሰገድለታል
ማለት ለእግዚአብሔር የሚቀርበው ስግደት በሰውነት እንቅስቃሴ ብቻ የሚገደብ
ሳይሆን ውስጣዊ እና መንፈሳዊ በሆነ ስሜት የሚቀርብ ነው ሲል ነው ፡፡
ምክንያቱም ለእግዚአብሐየር የምናቀርበው የአምልኮ ስግደት በመንፈሳችን
በውስጠወዊ ስሜታችን አምላካችን ነህ ፈጣሪያችን ነህ የተቤዥከን ነህ ……….
እያልን ከቃላት ከአካል እንቅስቃሴ በላይ በህሊናችን እና በመንፈሳችን ነው
ስግደትን የምናቀርብለት ፡፡ እኛ ከክርስቶስ ጋር ሞተን በትንሳኤው በመነሳት
በሰማያዊው ስፍራ ውስጥ አለን ፡፡አሁን እኛ በጻድቃን ጉባኤ ውስጥ ነን ፡፡ኤፌ2፡
8 ፤ቆላ3፡1-3ክርስትና በሞት የምትቋጭ አይደለችም፡፡ እንደውም እኛ በምድር
ያለነው ክርስቲያኖች በክርስቶስ አካልነታችን ከክርስቶስ ጋር ሞተን በትንሣኤው
በመነሣት በሰማያዊ ሥፍራ ውስጥ አለን ፡፡ አሁን እኛ በጻድቃን ጉባኤ ውስጥ
ነን፡፡ ክርስቶስ በሰጠን ሕይወት ውስጥ ሞት የለም የሥጋ ሞት ከቅዱሳን ነፍሳት
ጋር ያለንን ሕብረት ፍጹም ያደርገዋል እንጂ አያቆራርጠውም፡፡ @embtee
ሕይወታችንም መንፈስ ቅዱስ ከሆነ ቆየ፡፡ ስለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ
“በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን”(ኤፌ.2፡8)
እንዲሁም “እንግዲህ ከተነሣችሁ በክርስቶስ በእግዚብሔር ቀኝ ተቀምጦ
ባለበት በላይ ያለውን እሹ በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም
፡፡ ሞታችኋልና ሕይወታችሁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአልና፡፡
”(2ቆላ.3፡1-3) እንዲሁም “ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ
ደርሳችኋል ወደ ሰማያዊቱ ኢየሩሳሌም በደስታም ወደ ተሰባሰቡት ወደ አእላፋት
መላእክት በሰማያት ወደ ተጻፉ የበኩራት ማኅበር የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ
እግዚአብሔር ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች የአዲስ ኪዳን
መካከለኛ ወደ ሚሆነው ወደ ኢየሱስ ደም ከአቤልም ደም ይለቅ የሚሻለውን
ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል፡፡”(ዕብ.12፡22-24)ይለናል፡፡
ደርሳችኋል ማለት ምን ማለት ነው? አንድ ሥፍራ ነው ያላችሁት ማለቱ
አይደለምን? አንድ ሥፍራ መሆን ብቻ አይደለም “ከእንግዲህ ከቅዱሳን ጋር
ባለአገሮች ናችሁና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና
መጻተኞች አይደላችሁም፡፡”(ኤፌ.2፡19) ይለናል፡፡
ስለዚህ ቤተሰብ ለቤተሰቡ አባል ማሰቡ ተገቢ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ ያለበለዚያ
ከአመነም ሰው ይልቅ የከፋ ነው (1ጢሞ.5፡8) ፡፡በእነዚህ ሁሉ መስረጃዎች እኛ
ከቅዱሳን ሕብረት ውስጥ እንዳለን ተነግሮአል፡፡ እነዚህ ቅዱሳንም
“የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ ከእርሱም ጋር ይህን ሺህ ዓመት
ይነግሣሉ፡፡(ራእ.20፡6) የተባለላቸው ናቸው፡፡ ይህ ሁሉ ማስረጃዎች በዙሪያችን
አሉ፡፡ ስለዚህ በጥምቀት የተመሠረተውን ሕብረትና አንድ ቤተሰብ መሆንን የሥጋ
ሞት አይቆርጠውም እንደውም ይበልጥ ያጠነክረዋል፡፡
አስቀድመን በክርስቶስ የድኅነት ተግባር ሁላችን ክርስቲያኖች አንድ መሆናችንን
እናስታውስ ፡ አይሁድ የለ ፡ ግሪካዊ ፡ አረማዊ የለ አህዛብ ሁላችን በክርስቶስ
አንድ ሆነናል፡፡ በክርስቶስ አምኖ የሞተ ይሁን አሁን በሥጋ ያለ ሁሉ አንድ ሆኗል፡፡
ይህንስ ለሥጋ አዕምሮ እናገራለሁ እንጂ ሞትማ በክርስቶስ ሞቶ የለምን? ነገር
ግን ይህን አሁን አናይም ፡
በክርስቶስ የሞቱ ግን ስለክርስቶስ ህያዋን ናቸው፡፡
እንግዲህ ሁላችን አንድ ከሆን ወዲያ ስለክርስቶስ በፍቅር እንመላለስ ዘንድ
አለንና ፡ ከዚህ አንፃር አማላጅነት ምንድን ነው? ኢምንት መሆኑን አይደለምን?
ነገር ግን ስለክርስቶስ ጸጋወች ሁሉ ክቡራን ናቸው፡፡
ነገር ግን ምስጢሩ እያለ ስለምን በፊደሉ ላይ እስከመቼ ልባችንን አጨልመን
እንጓዛለን? እስከመቼ በሥጋ ስንመላለስ እንኖራለን? ክርስቶስ ለዚህ
ጠርቶናልን? የሥጋ ህይወት ፡ የስጋ ኑሮማ በኦሪት ዘመን ቀረ ፤ በክርስቶስ
ብርሃንነት መንፈሳዊነት ተገለጠች ፡ ሩቅ ሰማይ ቀረበች ፡ የጥል ጨለማ
ተገፈፈች ፡ የሞት አገልግሎት ተሻረች ፡ ምድር ከሰማይ ቀረበች ፡ ቅዱሳን ሁሉ
ከአንድ ማእድ ሊቋደሱ ተጠሩ ፡ ከአንድ አብ ከአንድ ወልድ ከአንድ መንፈስ
ቅዱስ የህይወት ማእድ ሊቋደሱ ፡ በአንድ መሶብ ሊቋደሱ ፡ በአንድ ምስጋና
ሊያወድሱ ፡ በአንድ ፀሃይ ሊያበሩ ፡ ተጠሩ፡፡ እንዲህማ ካልሆነ የክርስቶስ
መምጣት ሃይል በምን ይታወቅ ነበር፡፡
እንግዲህ መራራቅ ወዴት ነው? በክርስቶስ ቅርብ ሆኗን፡፡ እንግዲህ መከፋፈል
ወዴት ነው? በክርስቶስ አንድ ሆኗል ፤ እንግዲህ መጠላላት ወዴት ነው?
በክርስቶስ ተዋዷል ፤ እንግዲህ ባእድነት ወዴት ነው? በክርስቶስ ሁሉ ዘመድ
ሆኗል፡፡ ወይንስ ሞት ወዴት ነው? እርሱም በክርስቶስ ድል ተነስቷል ፤ በምድር
በሥጋ ያሉት ስለክርስቶስ ሰማያውያን ሆነዋል ፡ በነፍስ በሰማይ ያሉት
ስለክርስቶስ ምድራውያን ሆነዋል ፡፡
እንግዲህ በክርስቶስ ሁላችን ሰማያውያን መሆናችን አይደለምን? ሰማያውያን
ከሆንን እኛ አስቀድመው በሥጋ ከተለዩን ጋር ለመገናኘት ምን ይከለክለናል ፤
ወይንስ ሰማይ ሰፊ ነው የሚል አለን? እንኪያስ በክርስቶስ ሁላችን በእርሱ
ግንድነት ቅርንጫፍ ሆነን ተሰርተናል እንላለን ፤ እንግዲህ ቅዱሳን ሁሉ
ቅርንጫፍ ሆነው በአንድ ግንድነት ከተተከሉ ፡ እኔም ለዚህ ክብር ከተጠራሁ ፡
ከቅዱሳን ጋር ዘመድ መሆኔ አይደለምን? ወይንስ ዛፍስ ከውጭ ነው የሚለኝ
አለን? እንኪያስ በክርስቶስ ሁላችን አንድ ቤተሰብ ሆነናል እላለሁኝ ፡ እንግዲህ
የቤተሰቤ አካል ስለእኔ ሊጨነቅ ፡ ስለእኔ ሊያስብ ምን ይከለክለዋል? ወይንስ
እኔ ለቤተሰቤ ችግሬን ለመንገር ምን ይከለክለኛል? ወይንስ በአንድ ቤትም ሰፊ
ነው ፡ መደማመጥ ይቸግራል የሚል አለን? እንኪያስ በክርስቶስ አካልነት ሁላችን
ብልቶች ሆነን ተሰርተናል ብየ እመልስለታለሁ፡፡ እንግዲህ አይን ስለአፍንጫ
አይገደውምን? ይህስ ከአፈር ለተሰራ ሰውነት ይገደዋል ፡ ይህስ ከሆነ በክርስቶስ @embtee
አዲስ ተፈጥሮ ለታደሰ ሰማያዊ አካልማ እንደምን ከዚህ ይበልጥ ግድ አይለው?
እንግዲህ ከዚህ ሰማያዊ ምስጢር ይልቅ አማላጅነትን ለማሳነስ ጥቅስን
ስለመፈለግ ሰው ቢደክም ሥጋዊ መሆኑ አይደለምን? የክርስቶስን ክቡር
የመስቀሉን ስራ ለሚረዳ ግን ከፊደል ይልቅ ምስጢሩን ይረዳል ፡ ከምድራዊው
ይልቅ ሰማያዊውን ፡ ከሥጋዊው ይልቅ መንፈሳዊውን ያስባል ፡፡ስለዚህም
እንዚህ ማስረጃዎች ሁሉ ከቅዱሳን ጋር ቤተሰብ እና ባለሀገሮች እንደሆንን
እንዲሁም በመንፈሳዊ አካል አብረናቸው እንዳለን ስለሚያስረዳ ስግደቱን
በእምነት ሆነን አንድ ቤተሰብ እንደሆንን አምነን በመንፈስ እንደተሰጣቸው ጸጋ
መጠን እናቀርብላቸዋለን ፡፡በመንፈስ የሚሰገድ ለእግዚብሔር ው ሲል ቃሉ
ለቅዱሳን አይሰገድም ማለት ስላልሆነ አንተው ታረም!!
እርግጥ አምልኮ የሚገባው እግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ መፅሐፍ ቅዱስ
ይናገራል ፡፡ ዘፀ20፡5 ስግደት ግን ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት
አድርጋ በሶስት መንገድ ትፈፅማለት ይኸውም አምልኮ የጸጋ እና አክብሮት ነው
የአምልኮ የምንለው ለእግዚአብሔር ለአምላካችን ብቻ የሚቀርብ እርሱ ፈጣሪ
ገዥ መጋቤ እንደሆነ በልባችን አምነን የምናቀርብለት ስግደት ነው ፡፡ ማቴ4፡10
፤ዮሐ4፡24፤መዝ29፡2፤ዕብ1፡6፤ነህ9፡6፤መዝ96፡7፤መዝ118፡24 ፡፡የጸጋ
የምንለው እግዚአብሔር ለቅዱሳኑ ስለሰጣቸው ጸጋ የምናቀርበው ስግደት ነው @embtee
፡፡ይህም ከመፅሐፍ ቅዱስ የተገኘ እንጂ እኛ የፈጠርነው የፈለሰፍነው አይደለም፡፡
ዘኁ22፡31፤ኢያ5፡14፤መሳ13፡20፤2ዜ21፡16፤ሐዋ10፡26፤ራዕ19፡10፤ዮሐ22፡
9፤ሐዋ16፡29፤ራዕ3፡9፡፡የአክብሮት የምንለውም በእድሜ ትልቅ ለሆኑ እና
ለነገስታት የምናቀርበው ስግደት ነው ይሄም መፅሐፍ ቅዱሳዊ ነው፡፡ዘፍ33፡
3፤1ሳሙ20፡41፤ዘፍ33፡3፤ዘፍ23፡፤1ዜና29፡20፡፡መፅሐፍ ቅዱስ
የሚያስተምረን ስግደት ለእግዚአብሔር ብቻ ሳይሆን ለቅዱሳኑ እንዲሁም
በእድሜ ታላላቅ ለሆኑ ጭምር በአክብሮት እንድሰግድ ሲሆን ይህንን መቃወም
መፅሐፍ ቅዱስን አለማመን ብሎም መካድ ነው ፡፡የመፅሐፍ ቅዱስ አማኝ
መፅሐፍ ቅዱስ ላይ የተጻፉትን ሳይጨምር ሳይቀንስ ያምናል ይህንም
ይተገብራል እንጂ እንዱን አምኖ የማይመቸውን ጥሎ አይሔድም ፡፡ተሐድሶ
ለእናንተው!!
‹‹➋ለምን ለፍጡራን አንዘምርም?....
ይህንን ለመመለስም ቢሆን ተራራ መቧጠጥ አያስፈልገንም፡፡ በአጭሩ ዝማሬ @embtee
አምልኮ ነው፡፡ አምልኮ ደግሞ ለእግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡
★የሙሴ እህት ማርያም ስትዘምር <በክብር ከፍ ከፍ ብሏልና ለእግዚአብሔር
ዘምሩ> አለች፡፡ ሌላ በክብር ከፍ ከፍ ያለ የዝማሬ ባለቤት ስለሌለኝ ደስተኛ ነኝ፡፡
★ የህዝቡ አለቃ ሙሴ በምድረበዳ ለህዝቡ ካስተማራቸው ዝማሬ መሀል
አንድም ለፍጡራን የተዘመረ <ኢትዮጵያዊው ፃድቅ ማነው ብዬ ጠየቅኩ> አይነት
መርገም አይገኝም፡፡ ይልቅ ለእግዚአብሔር ብቻ የተዘመሩ ነበሩ፡፡
★ 150 ምእራፎች ያሉት መዝሙረ ዳዊት ምንም እንኳን የተለያዩ ሰዎች ስራ
ቢሆንም አንድም ቦታ ላይ እንደናንተ <ዝማሬዎች>ለአብረሀምና ለይስሀቅ የ
<አማልዱን> ጥያቄ አያቀርቡም፡፡
★በራእየ ዮሀንስ ላይ ያሉት ህዝቦች ሁሉ <ለአምላካችንና ለበጉ ማዳን ነው>
ብለው ዘመሩ እንጂ ለማርያም አልዘመሩም፡፡ ስለዚህ ክርስቲያን ለፍጡር
አይዘምርም፡፡››
ቅዱሳንን በተሰጣጨው ጸጋ በዝማሬ ማመስገን እንዳለብንም ያሳሰበን
እግዚአብሔር አምላካችን ነው ፡፡ዳዊት በገና እየደረደረ በዘመረበት ዝማሬ
በተደጋጋሚ ቅዱሳንን አመስግኗል አዳኝነታቸውን አማላጅነታቸውን በዝማሬ
ተናግሯል ፡፡ሙሴ ከሞተ ብዙ ዘመን ቢሆነውም ዳዊት ግን የሙሴን አማላጅነት
በዝማሬው አውስቷል ‹‹እንዳያጠፋቸው ቍጣውን ይመልስ ዘንድ የተመረጠው
ሙሴ በመቅሠፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፥ ያጠፋቸው ዘንድ ተናገረ››መዝ
105(106)፡23 ሙሴ በእግዚአብሔር ፊትም በምልጃ ቆሞ እንደነበር መፅሐፍ
ቅዱስ ይነግረናል ‹‹አሁን ይህን ኃጢአታቸውን ይቅር በላቸው ያለዚያ ግን
ከጻፍኸው መጽሐፍህ እባክህ ደምስሰኝ አለ›.ዘጸ32፡32 ለቅዱሳን መዘመር
ባይገባ ኖሮ ከሞተ ብዙ ጊዜ ስለሆነው ሙሴ ዳዊት ባልዘመረ ነበር !! ወዳጄ
ዝማሬ ሁሉ አምልኮ አይደለም ፡፡የአምልኮ ዝማሬ አለ የጸጋ ዝማሬ ደግሞ አለ፡፡
ያቀረብካቸው ለእግዚአብሔር ዝማሬ ያቀረቡ ሰዎች እነዚህ ብቻ ሳይሆኑ ብዙ አሉ @embtee
፡፤እነሱ ዝማሬ ለእግዚአብሔር ማቅረባቸው ለቅዱሳኑ የጸጋ ዝማሬ ማቅረብ
አይገባም የሚያሰኝ ሳይሆን እግዚአብሔርን ማመስገን ማወደስ እንደሚገባ
የሚያሳዩ ጥቅሶች ናቸው ፡፡በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለእግዚአብሔር ዝማሬ
እንደሚገባ እና ዝሬን ቀረቡ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ ለቅዱሳኑም ዝማሬን ያቀረቡ
ምስጋናን የሰጡ ሰዎች በብዛት አሉ ፡፡ሩቅ ሳንሔድ አንተ ለአስረጅነት
በተቀስከው በ150 የዳዊት መዝሙር ውስጥ ለቅዱሳኑ ብዙ ዝማሬዎች
ቀርበዋል ፡፡እንደሚታወቀው መቶ ሀምሳው ዳዊት ዝማሬዎች
የተለያ ሰዎች
ዘመሩት ዛማሬ ቢኖሩበትም ጸሐፊው ግን ዳዊት ነው ፡፡የተጻፉትም ዝማሬዎች
በበገና በማሲንቆ……..በተለያዩ የመዝሙር መሳሪያዎች የቀረቡ ዝማሬዎች
ናቸው በነዚህ ዝማሬዎች ውስጥ ለቅዱሳኑ ቀረቡ የተለያዩ ዝማሬዎች አሉ ፡፡
ዳዊት ለቅዱሳኑ እንዲህ እያለ ይዘምር ነበር ‹‹በቅዱሳን ምክር እግዚአብሔር
ክቡር ነው በዙሪያው ባሉት ሁሉ ላይ ታላቅና ግሩም ነው።››መዝ88(89)፡7 ፣
‹‹ጻድቃን ሆይ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ ለቅኖች ምስጋና ይገባል።››መዝ
32(33)፡፤‹‹ ጢአተኞችን ክፋት ይገድላቸዋል ጻድቃንንም የሚጠሉ
ይጸጸታሉ።››መዝ33(34)፡21፤‹‹የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው፥ እግዚአብሔርም
ከሁሉ ያድናቸዋል።›.መዝ33(34)፡19፤‹‹የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃን @embtee
ጆሮቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸውና።››መዝ33(34)፡15፤‹‹ኃጢአተኛ ይበደራል
አይከፍልምም ጻድቅ ግን ይራራል ይሰጣልም።››መዝ36(37)፡21፤‹‹የጻድቅ
መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል››መዝ111፡6 በዳዊት መዝሙር ለቁጥር
በሚያዳግት ሁኔታ ስለጻድቃን ቸርነት መታሰቢያ ……..ተዘምሯል ስለሐጥአንም
ክፋት …..ተዘምሯል እኛም ያዳዊትን መዝሙር አብነት አድርገን ስለጻድቃን
ቸርነት መታሰቢያ ተጋድሎ አማላጅነት እንዘምራለን ስለ ሀጥአን ክፋት
እንናገራለን ፡፡ ባይገርምህ ዳዊት ስለሙሴ አማላጅነት ሳይቀር ዘምሯል
‹‹እንዳያጠፋቸው ቍጣውን ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሠፍት ጊዜ
በፊቱ ባይቆም ኖሮ፥ ያጠፋቸው ዘንድ ተናገረ።››መዝ105(106)፡23 ፤ዘጸ32፡32
እኛም ይህንን አብነት አድርገን እንዘምርላቸዋለን ይህንን መቃወም ቃሉን
መቃወም ነው ፡፡ ‹‹ነገር ግን በጎ ሥራ ለሚያደርጉ ሁሉ ምስጋናና ክብር ሰላምም
ይሆንላቸዋል፥ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው።››ሮሜ2፡
10ስለዚህ ክርስቲያን ቤተሰቦቹ ለሆኑ ለቅዱሳኑ ምስጋናን ዝማሬን ያቀርባል ፡፡
መፅሀፍ ቅዱስ እንደሚል መጓዝ እና ማመን መፅሐፍ ቅዱስ አምናለው ከሚል
ሰው ይጠበቃል ፡፡!!!!!!!
‹‹ነገር ግን አላፍርበትም፤ ያመንሁትን አውቃለሁና››2ጢሞ1፡12
እቀጥላለው
ይቆየን

@embtee @embtee
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የመጋቢት ወር መታሰቢያ በዓል
በሰላም አደረሳችሁ።
የመስቀል ስር ስጦታውን የተቀበለ የተዋሕዶ ልጅ ብቻ ስለ እመቤታችን ደስ
ያላችሁን እየጻፋችሁ አመስግኗት። ፳፩ ፳፩ ፳፩
@embtee @embtee
@embtee @embtee
ዕለት ሠርቅ፡፡ በእምርት ዕለት በዓልነ፡፡ እስመ
ሥርዓቱ ለእስራኤል ውእቱ“
ትርጉም፦ በመባቻ ቀን በታወቀችው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ፤ ለእስራኤል
ሥርዐቱ ነውና÷ የያዕቆብም አምላክ ፍርድ ነውና፡፡
ወይም
መዝ.80÷2 „እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሓተ፡፡ በእንተ ጸላዒ፡፡ ከመ
ትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ፡፡“
ትርጉም፦ ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ፡፡ ስለ ጠላት÷
ጠላትንና ግፈኛን ታጠፋው ዘንድ፡፡
ወንጌል
ዮሐ.12÷1-11 ፋሲካ ከሚውልበት ከስድስተኛው ቀን አስቀድሞ ጌታችን
ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ፡፡(ተጨማሪ
ያንብቡ)
ቅዳሴ
ቅዳሴ ዘጎርጎርዮስ፡፡
ሆሳዕና የዐብይ ጾም ስምንተኛ ሳምንት !!
Posted by:- መንበረ ብርሃን ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሙኒክ ጀርመን
ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሑዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ
የሚጠራው ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መገቢያ ዋዜማ ነው።
ሆሣዕና አስቀድሞ ካለው ረቡዕ ጀምሮ የሚታሰብ ታላቅ የቤተክርስቲያን የበዓል
ቀን እንደሆነ ይታወቃል። ይህን ስም በዚሁ ሰንበትና በዋዜማዎቹ ዕለታት
የሚዘመረው ጾመ ድጓ ‘ሆሣዕና በአርያም’’ ‘ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት’’ ‘ዕለተ
ሆሣዕናሁ አርዓየ… ‘ ወዘተ. በማለት ሆሣዕና የሚለውን ቃል ቅዱስ ያሬድና
ሌሎችም አባቶች በየቦታው እየጠቀሱና እየተዘመረለት በአህያ ውርንጭላ ላይ
ተቀምጦ ኢየሩሳሌም የገባበትን ሁኔታ እየተረከ ስለሚዘምር ይህ ሰንበት
በጌትነትና በክብር በውዳሴና ቅዳሴ ሆሣዕና በአርአያም እየተባለ
በሽማግሌዎችና በሕፃናት አንደበት በድንጋዮችም ልሳን ሳይቀር እየተመሰገነ ወደ
ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በከብር ሲገባ ለሰጣቸው ለተቀደሰ ሰላሙና ፍቅሩ
መታሰቢያ ሆኖ የተሰጠ ነው።
ሆሳእና ለርያም
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ሌላ ቀን እንደ ተራ ሰው ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ይገባ
ነበር፡፡ በዚህ ቀን ግን የአይሁድ ንጉሥ ሆኖ በክብር ገባ፡፡ ከቢታንያ ተነሥቶ ደብረ
ዘይት ሲደርስ ከሐዋርያቱ ሁለቱን በቤተፋጌ ሰው ተቀምጦባት የማያውቅ
ውርንጭላ እንዲያመጡለት ላካቸው፡፡ “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሒዱ
በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርሷ ጋር ታገኛላችሁ፤
ፈትታችሁም አምጡልኝ፡፡ ማንም አንዳች ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ“
አላቸው፡፡ ማቴ.21፡1-17
ወደ ቤተፋጌም ሄደው አህያዪቱን አገኙአት፡፡ ሲፈቱአትም ሳለ ባለቤቶቹ
መጡባቸውና አስቆሟቸው፡፡ እነርሱም ኢየሱስ እንደፈለጋት ነገሩአቸው፡፡
ባለቤቶቹ ይህንን ሲያውቁ ተውአቸው፡፡ ሐዋርያትም የአህያዪቱን ውርንጭላ
ፈትተው ወደ ኢየሱስ ወሰዱ፡፡ አጠገቡም ሲደርሱ ልብሳቸውን በአህያዪቱ
ውርንጭላ ላይ አንጥፈው ኢየሱስን አስቀመጡት፡፡
ለምን ዘንባባ ያዙ ቢባል፤ ዘንባባ እሾሃም ነው ፤አንተም የኃይል የድል ምልክት
አለህ ሲሉ፤በሌላም በኩል ዘንባባ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ አይበላውም
አንተም ባህርይህ አይመረመርም ሲሉ፤አንድም ዘንባባ ረጅም /ልዑል/ ነው
አንተም ባሕርይህ ልዑል ነው ሲሉ ዘንባባ ይዘው ተቀብለውታል፡፡
የተምር ዛፍ ዝንጣፊ ነው ቢሉ፤ ተምር ፍሬው አንድ ነው አንተም ባህርይህ አንድ
ነው ሲሉ፡፡አንድም፤ተምር ልዑል/ረጅም/ ነው አነተም ልዑለ ባህርይ ነህ ሲሉ፡፡
አንድም፤የተምር ፍሬው በእሾህ የተከበበ ነው በቀላሉ መለቀም አይቻልም
፤የአንተም ምስጢር አነተ ካልገለጠከው አይመረመርም ሲሉ ነው፡፡
የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ነው ቢሉ፤ ወይራ ጽኑዕ/ ጠንካራ/ ነው አንተም ጽኑዓ
ባህርይ ነህ ሲሉ፤አንድም ወይራ ለመስዋዕት ይሆናል፤ አንተም መስዋዕት
ትሆናለህ ሲሉ፤አንድም ወይራ ዘይቱ ለመብራት ይሆናል አንተም የዓለም ብርሃን
ነህ ሲሉ ይህንን ይዘው አያመሰገኑ ተቀበሉት፡፡
ልብሳቸውንም ማንጠፋቸው፤ እንኳን አንተ የተቀመጥክባት አህያ እንኳን መሬት
መርገጥ አይገባትም ሲሉ ልብሳቸውን አነጠፉለት፡፡ እነዚያ ያላመኑ አይሁድ
ለተቀመጠባት አህያ ይህንን ያህል ክብር ከሰጡ፤ በድንግልና ጸንሳ ለወለደችው
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምን ያህል ክብር ልናድረግለት ይገባን
ይሆን?፡፡
“የጽዮን ልጅ ሆይ አትፍሪ እነሆ ንጉሥሽ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ
ይመጣል” ዘካ.9፡9 የሚለው የዘካርያስ ትንቢት ተፈጸመ፡፡ ሕዝቡም ኢየሱስ
በመምጣት ላይ እንዳለ ሲያውቅ ሊቀበለው ወጣ፡፡ አንዳንዶች ያልፍበት በነበረ
መንገድ ልብሳቸውን እንዳንዶቹ ደግሞ የዘንባበ ዝንጣፊ ያነጥፉ ነበር፡፡ ከፊትና
በኋላ ያሉት ደግሞ “ሆሳዕና በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሳዕና ለዳዊት
ልጅ” እያሉ በታላቅ ድምፅ ይጮሁ ነበር፡፡ ኢየሱስ በሕዝቡ እልልታና ደስታ ታጅቦ
ሲገባ ተጠንቅቀው ይታዘቡትና ይመለከቱት የነበሩ ፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርቱን
ዝም እንዲያሰኛቸው ተናገሩት፡፡ እርሱም ሕዝቡ ዝም ቢል ድንጋዮች እንደሚጮኹ
አስታወቃቸው፡፡ ኢየሱስ ኢየሩሳሌምን ሲያያት አለቀሰላት፡፡ “አንቺ ኢየሩሳሌም
ለሰላምሽ የሚያስፈልገውን ነገር ምነው አውቀሽ ቢሆን ኖሮ አሁን ግን ይህ ነገር
ከዓይንሽ ተሰውሮብሻል ጠላቶችሽ በዙሪያሽ እንደ አጥር ከብበው በዚህም
በዚያም አንቺን የሚያስጨንቁበት ጊዜ ይመጣል… ምክንያቱም እግዚአብሔር
ሊያድንሽና ሊጐበኝሽ የመጣበትን ጊዜ ባለማወቅሽ ነው” እያለ ረገማት፡፡
መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም የገባው ሰለ ደኅንተቷ
ሊያሳስባት ፈልጐ ነው፡፡ በማያወላዳ መንገድ ንጉሷና መድኃኒቷ እንደሆነ
ገለጸላት፡፡ ወደ ራሷ ተመልሳ ጸጋዋን እንድትቀበል የልቧን ድንዳኔ ትታ እርሱን
እንድትሰማ አስጠነጠቃት፡፡ ግን አልተጠነቀቀችም፡፡ ለጊዜው በክብር
ተቀበለችው፡፡ ከጥቂት ቀን በኋላ ግን ተወችው፤ በመስቀል ላይ ሰቀለችው፡፡
የደኅንነቷን ቀን ማወቅ ተሳናት፡፡ በዚህም ደግሞ ከብዙ ዓመታት በኋላ መዓት
ወረደባት፡፡
ይህ የሚያሳዝን የኢየሩሳሌም ሥራ የእኛም ሥራ ነው፡፡ ኢየሱስን መድኃኒታችንን
መቀበል አንፈልግም ወይም ተቀብለን በኃጢአታችን ከእኛ እንዲርቅ
እናደርገዋለን፡፡ በቅዱስ ቁርባን ወደ እኛ ሲመጣ በደስታ እንቀበለዋለን፡፡ ትንሽ
ቆየት ብለን ደግሞ እናዋርደዋለን፡፡ ከእርሱ ጋር እንጣላለን፡፡ ከኃጢአት ጋር
ጓደኝነት እንይዛለን፡፡ በኃጢአት ስንወድቅ እርሱን እንደገና እንሰቅለዋለን፡፡ ኢየሱስ
እኛን “አቤት በዚህ ቀን ለደኅንነትህ የሚደረገውን ብታውቅ ኖሮ …፣ ይህ ሁሉ
ከዓይንህ ተሰውሮብሃል ማወቅን አልፈለግህም፡፡ ይህን እወቅ ግን አንድ ቀን …”
እያለ አዝኖ ይፈርድብናል፡፡ ይህንን በማሰብ ሲመጣና ሲናገረን እምቢ አንበለው
አናባርረው፡፡ በኋላ እርሱ ቂም ይዞ እምቢ እንዳይለና እንዳያባርረን ደኅንነታችንን
ራሳችን አናጥፋት፡፡
የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ)
ወእንዘ ሰሙን በዓለ ፋሲካ ቀርቡ አርዳኢሁ ለአምላከ ጽድቅ ኀበ ደብረ ዘይት
ሙራደ ዓቀብ ሀገረ እግዚአብሔር ወተቀበልዎ ሕዝብ ብዙኃን አዕሩግ ወሕፃናት
ነሢኦሙ አዕፁቀ በቀልት እንዘ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ተፅዒኖ ዲበ ዕዋል ቦአ
ሀገረ ኢየሩሳሌም በትፍሥሕት ወበሐሴት ይሁቦሙ ኃይለ ወሥልጣነ፡፡…..
ትርጉም: “በፋሲካ በዓል ሰሞን የእውነት አምላክ ደቀ መዛሙርት ወደ ደብረ
ዘይት ቀረቡ፤ በሀገረ እግዚአብሔር (ኢየሩሳሌም) አቀበቱ ላይ ብዙ አረጋውያንና
ሕፃናት የዘንባባ ቅጠል ይዘው ሆሣዕና በአርያም እያሉ ተቀበሉት፣ በአህያ
ውርንጫ ላይ ተጭኖ በፍጹም ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። ለእነዚህ ኃይልና
ሥልጣንን ይሰጣቸዋል።
መልዕክታት
ዕብ.8÷1-ፍጻ. ከተናገርነውም ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው
ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፡፡ እርሱም የመቅደስና
የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፤ እርስዋም በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር
የተተከለች ናት፡፡ (ተጨማሪ ያንብቡ)
1ኛ ጴጥ.1÷13 ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና ነቅታችሁ ኑሩ፤ ኢየሱስ
ክርስቶስም ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ፡፡ (ተጨማሪ
ያንብቡ)
ግብረ ሐዋርያት
የሐዋ.8÷26-ፍጻ. የእግዚአብሔር መልአክም ፊልጶስን ተናገረው፤ እንዲህም
አለው÷ “በቀትር ጊዜ ተነሣና በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ
በሚያወርደው በምድረ በዳው መንገድ ሂድ፡፡” ተነሥቶም ሄደ፡፡” እሆም÷
(ተጨማሪ ያንብቡ)
ምስባክ
መዝ.80÷3 „ንፍሑ ቀርነ በ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሕማማት መስቀል " ተብለው የሚዘከሩት አሥራ ሦስት ሲሆኑ እነዚህም፦
@embtee
1. በብረት ሐብለ መጋፊያና መጋፊያው እስኪጋጠም ድረስ የኋሊት መታሰሩ
2. ከአፍንጫው ደም እስኪውጣ ድረስ 25 ጊዜ በጡጫ መመታቱ
3. 65 ጊዜ ከግንድ ማጋጨታቸው
4. 120 ጊዜ በድንጋይ ፊቱን መመታቱ
5. 365 ጊዜ በሽመል መደብደቡ
6. 80 ጊዜ ጽህሙን መነጨቱ
7. 6666 ጊዜ መገረፉ
8. አክሊለ ሦክ በራሱ ላይ መደፋቱ
9. 136 ጊዜ በምድር ላይ መውደቁ
10. ሳዶር፡ አላዶር፡ ኤዴራ፡ ዳናትና ሮዳስ በሚባሉ 5ቱ ቅንዋተ መስቀል
በችንካር መቸንከሩ
11. መራራ ሐሞትን መጠጣቱ
12. መስቀሉን ተሸክሞ መንገላታቱ
13. በመስቀል መሰቀሉ ናቸው።
@embtee @embtee @embtee
@embtee @embtee @embtee
#መዝሙር
ለምን መዝሙር በግጥም ብቻ እናጠናለን ኑ ከኛ ጋ አብረን ከነ #ዜማው እናጥና እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን {መዝ 150-6}
👇 ይ ቀ ላ ቀ ሉ 👇

@Zemaryan 👈👉 @Zemaryan
@Zemaryan 👈👉 @Zemaryan
@Zemaryan 👈👉 @Zemaryan
@Zemaryan 👈👉 @zemaryan