✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.2K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
Forwarded from Soli G
እንኳን ለአምላካችን ለመድሀኒታችን የሰማይና የምድር ንጉስ ለድንግል
ማርያም ልጅ ለቸሩ መድሀኒአለም አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን
አደረሳቹ አሜን
Forwarded from Deleted Account
Forwarded from Deleted Account
ልጄ ሆይ.. በሁሉ አመስግን !!!
የምስጋና ሕይወትን የሚኖር ሰው ምስጉን ነው የተደረገለትን የማይዘነጋ
አመስጋኝ ነው።
የተደረገለትን በጎ ነገር ሁሉ የማይረሳና ምስጋና የሚያቀርብ የተባረከ ነው ።
ምስጋና ሰውን
ከመላእክት ጋር አንድ የሚያደርገው ሀብት ነው ፣ በልባችንና በአንደበታችን
ለእግዚአብሔርም
ሆነ ለሰው ልጅ ምስጋና ማቅረብ ይገባል ።
ምስጋና ባቀረብን ቁጥር እግዚአብሔርን እናከብራለን እግዚአብሔር ለእኛ
ያለውን ፍቅር
እናደንቃለን ።ለእኛ ያለውን ርህራሄ እናውቃለን ።የተደረገልንን ሁሉ አውቀን እና
ተረድተን
መኖራችን ይገለጣል እግዚአብሔርን ለማመስገን ቦታ ጊዜና ሁኔታን
አንመርጥም..ሁል ግዜ
እናመሰግነዋለን ።
"ሳታቋርጡ ፀልዩ በሁሉ አመስግኑ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ
ወደ
እናንተ ነውና" ፩ ተሰ ፭፥፲፯
ጌታ ሆይ ስላደረክልኝ ስላላደረክልኝም ሁሉ ተመስገን !!!
Forwarded from Deleted Account
ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል ።" መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ
16:7
Forwarded from Deleted Account
Forwarded from Deleted Account
ለምን ነጭ ነጠላ እንለብሳለን?
ከአነበባችሁ በኋላ ለሌሎች ሼር አድርጉ
አንዳንዶች ባለማወቅም ይሁን በቅናት ክርስትና ነጠላ ለብሶ ቤተክርስቲያን
መሄድ አይደለም ሲሉ ይደመጣሉ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ግን
መጽሐፍ ቅዱስን ምክንያት አርጋ ምሥጢሩን ከተግባር ጋር ትገልጻለች ወደ ቤተ
መቅደስ ስንሄድ ነጭ መልበሳችን የተገባ ነው ነጭ ነጠላ ጋቢ አደግድገን
ወይም በትእምርተ መስቀል ለብሰን ቤተመቅደስ ስንቆም የምናስባቸው
ምስጢራት አሉ
ለምን በትእምርተ መስቀል እንለብሳለን ካልን የክርስቶስን መከራ ለማሰብ
ነጠላው ወደ ግራ ቀኝ በትእምርተ መስቀል አምሳል ይጣፋል። በዚህ ጊዜ
ጌታችን በዕለተ አርብ የተቀበላቸው ጸዋትወ መከራ እንዲሁም በቀራንዮ
በምልዕልተ መስቀል መሰቀሉን ያስታውሰናል።ይኸውም የተመሳቀለ ነጠላ
የሚመለከትም ሁሉ የጌታችንን መከራ መስቀል መቀበሉን ያስባል። የምናጣፋው
ነጠላ ነጭ የሆነባቸው የተለያዩ ምክንያቶች አሉ እነዚህ ከታች የተጠቀሱት
ምክንያቶች ሰፊ ትምህርት ቢኖራቸውም እኔ ግን ባጭሩ እንዲህ
አቀረብኩላችሁ፦
፩. የሚጠብቀንን ሰማያዊ ክብር በማሰብ ነጭ እንለብሳለን ".....ቅዱስና
እውነተኛ ጌታ ሆይ እስከመቼ አትፈርድም? ደማችንንስ በምድር ላይ በሚኖሩት
ላይ እስከመቼ ድረስ አትበቀልም አሉ ለእያንዳንዳቸው ነጭ ልብስ
ተሰጣቸው....." /ራዕ.፮፥፱-፲፩/ "ከዚህም በኋላ አየሁ እንሆም አንድ እንኳን
ሊቆጥራቸው የማይችል ከህዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ
ሰዎች ነበሩ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባም የዝንጣፊም በእጆቻቸው ይዘው
በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ" /ራዕ.፯፥፱/
፪.ቅዱሳን መላእክት ከእኛ ጋር መሆናቸውን ማሰብ
".....ማርያም ግን እያለቀሰች ከመቃብር በስተ ውጪቆማ ነበር። ስታለቅስም
ወደ መቃብር ዝቅ ብላ ተመለከተች ሁለት መላእክትም ነጭ ልብስ ለብሰው
የጌታ የኢየሱስ ሥጋ በነበረበት ቦታ አንዱ በራስጌ ሌላው በግርጌ ተቀምጠው
አየች።" /ዮሐ.፳፥፲፩-፲፪/ ታድያ እንደ መላእክት ለብሶ በቤተክርስቲያን ማገልገል
ምኑ ነው የሚያስወቅሰው ያሚያሳፍረው ያኮራል እንጂ!።
፫. ከጌታችን ጋር እንዳለን እናስባለን
".....ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን
ይዞ ወደ ረጅም ተራረ ለብቻቸው አወጣቸው። በፊታቸውም መልኩ ተለወጠ
ፊቱም እንደ ፀሐይ አበራ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ።" /ማቴ.፲፯፥፩-፪/
ስለዚህም ነጠላ መልበስ መንፈሳዊ ትርጉም አለውና ወንዶች ብንሆን በኪዳኑ
በቅዳሴውና በንግሱ ላይ ያለ ነጠላ ከምንሄድ ነጠላ ብንለብስ እህቶቼም
ሥርዓቱን የጠበቀ ነጠላ ለብሰን ከላይ የተጠቀሱትን እያሰብን በቤቱ ብንገኝ
መልካም ነው። << አባቶች የሠሩትን የቀድሞውን የድንበር ምልክት
አታፍልስ>> /ምሳሌ.፳፪፥፳፰/ ሁላችንም ሥርዓተ ቤተክርስትያንን እንድንጠብቅ
ልቦና ይስጠን። እግዚአብሔር ሁላችንንም እንደ ፍላጎታችን ሰይሆን እንደ እርሱ
ፈቃድ እንድንመራ ዓይነ ልቦናችንን ያብራልን! ይህ እራስን መግዛት ለቃሉ
አለመታዘዝ ብዙዎቻችን ጋር ያለ ችግር ነው ይህ የሆነው የእግዚአብሔር ፍቅር
በውስጣችን ሳይኖር የዓለምን ፍቅር እብልጠን ምን ችግር አለው እያልን በእግር
ብቻ በቤቱ መመላለስ ስለለምድን ነው። ትልቁ ችግር ያመጣው ምን ችግር
አለው ነው ለዚህም ማሳያ የፕሮቴስታንት እምነት ያለ ዶግማና ቀኖና በራሳችን
አስተያየት የምንጓዝ ቢሆን ብዙ ድርጅት በሆንን ነበር ግን አንድ ሀሳብ አንድ
እላማ የሚያረገንን ዶግማና ቀኖና ቤተክርስቲያናችን ሰርታልናለች ስለዚህም
ትክክል ያልሆነውን የዓለም ስርአት ስለተለማመድነው እንደ ቤተክርስቲያን
ስርዓት ለመመላለስ ይቸግረናል ከመምህረ ንሰሃችን ጋር በመመካከር፤ በግልና
በማህበራዊ ጸሎቶች በመትጋት፤ አንዱ ለሌላው በመጸለይ፤ ሁል ግዜ ቅዱሳት
መጽሐፍትን በማንበብና ሊያዘናጉን ከሚችሉ ሁኔታዎች በመራቅ ለእግዚአብሔር
ሕግ መገዛት እንችላለን ትእዛዙን ፈጽመን ለመኖር የቅዱሳን አምላክ
እግዚአብሔር ሁላችንንም ይርዳን!!!
Forwarded from Deleted Account
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Deleted Account
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Deleted Account
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Deleted Account
*©በአባቶች ልመና*

በአባቶች ልመና እስኪ ልለምንሽ
እኔማ ግብር የለኝ ለመቆም በፊትሽ
ርሃብሽን አሳስቢ ድንግል ሆይ እባክሽ

ግብሬን አውቀዋለሁ ምንም ምን ጽድቅ የለኝ /፪/
ውኃ ያልጎበኘው አዳፋ ልብስ ነኝ

አዝ,,,,,ጥምሽን

ለብሼ ሲያምርብኝ ጻድቅ እመስላለሁ /፪/
ድንግል ሆይ ታውቂያለሽ ውስጤን ጐስቁያለሁ

አዝ,,,,,ልቅሶሽን

በኃጢአቴ ሳለቅስ ከጧት እስከማታ /፪/
ድንግል ሆይ አትርሽኝ ሁኝልን አለኝታ

አዝ,,,,ስደትሽን

ካጠጣሽው ውሻ ያን ጊዜ ተጠምቶ /፪/
እኔም በምግባሬ አልሻም ከቶ

አዝ,,,,,ኃዘንሽን
Forwarded from Deleted Account
የፀሎት ቦታ አዘገጃጀት

አቅጣጫው ወደ ምስራቅ (ወደ ጸሐይ መውጫ)::
ፀሐይ በሌለበት አገር ኮምፓስ (Compass) ይጠቀሙ::
ስእሎቹ ተባርከው ቅባ ቅዱስ ተቀብተው በፍሬም ተሰርቶ መሆን አለበት::
በቁመት በግንባር ትክክል መሰቀል ያለበት (የመድኃኔዓለም እና የቅድስት ሥላሴ ስእል
(ተባርኮና ቅባ ቅዱስ ተቀብቶ) ከግራ ወደ ቀኝ::
በንብርክክ በግንባር ትክክል መሰቀል ያለበተ (የቅዱስ ሚካኤል ፤ የእመቤታች ድንግል ማርያም፤ የመላኩ ገብርኤል)
(ተባርኮና ቅባ ቅዱስ ተቀብቶ):: ከግራ ወደ ቀኝ::
ከታች መጽሐፍ ቅዱስ፣ቅባ ቅዱስ፣መቁጠሪያ፣ የጸሎት ውሐ፣
ውዳሴ ማርያም ፥ ሰይፈ መለኮት ፥ ሰይፈ ስላሴ፣ አርጋኖን ፣
መልክአ ገብርኤል፣ መልክአ ስላሴ ፥ መልክአ ሚካኤል፣
መልክአ መድሃኔአለም፥ መልከአ ኡራኤል፣ መልክአ ሩፋኤል ፣
መዝሙረ ዳዊት ወዘተ….ከታች ይቀመጣል::

ይላኩልን👇👇👇👇

@yitayal123bot
☝️☝️ሊቀር የማይገባ☝️☝️

👉ታላቅ ንግስ👈

Share share ያድርጉት

👉ከዚ በፊት ለመጣቹ አዲስ ሰው አስከትለው ይምጡ ስለ እመብርሀን

👉ከዚ በፊት መጣቹ ለማታቁ እመብርሀን ምስክሬ ናት ምን ያህል መንፈሶ ደስስ እንደምትሰኘ ታያላቹ እንዳይቀር ምክንያት አያስፈልግም
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ሕዳር ጽዮን!!
(ዉል ዉል አለኝ ደጅሽ፣ ዉል ዉል አለኝ ደጅሽ!!)
“በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀምጠን፡ ጽዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን”
“ዉስተ አፍላገ ባቢሎን ህየ ነበርነ ወበከይነ ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን”
መዝሙር 137-1
ህዳር 21፣ ታቦተ ጽዮን የምትከብርበት ታላቅ ክብረ በኣል
ታላቅ የምስራች ይህን ታላቅ በአል ለማክበር የምትናፍቁና ሀሙስ ቀን በመዋሉ
በስራ ምክንያት ማክበር አንችልም ብላችሁ ለነበረ
የዘንድሮ 2010 ዓ.ም ህዳር ማርያም የምትዉልበት ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ
የመዉሊድ በአል በሙስሊሙ ህብረተሰብ ዘንድ የሚከበርበት ቀን በመሆኑ
እንዲሁም የስራ ቀን እንዳይሆን የጊዜ ቀመር ሰሌዳዉ(ካላንደር) ስለሚዘጋዉ
በዚህ ታላቅ የበረከት ቀን በአዲስ አለም ማርያም ከዋዜማዉ ቀን ጀምሮ ማንም
ሳይቀር በደስታ በረከት የምንሰበስብበት እለት እንዲሆን ሁላችሁም
ተጠርታችኋል ፡፡
ማንም እንዳይቀር!!
ርእሰ አድባረት ወገዳማት ዳግሚት ጽዮን አዲስ አለም ማርያም በምእራብ ሸዋ
ሀገረ ስብከት ስር የምትገኝ ስትሆን ከአዲስ አበባ በአንቦ መስመር አቅጣጫ
42 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ናት፡፡ ደርሶ መልስ ትራንስፖርት 18+ 18
በጥቅሉ 36ብር የሚፈጅ ሲሆን የትራነስፖርት አማራጮች በሰፊዉ የሚገኙ
እንደሆነና ከዋናው አውቶብስ ተራ እና ከአስኮ መናህሪያ ማግኘት የምትችሉ
መሆኑን እያሳሰብኩ ከመኪና መንገድ ወደ ጸበሉ እና ወደ ቤተክርስቲያኒቱ
ለመድረስ የ15 ደቂቃ ብቻ የእግር ጉዞ የሚያስኬድ መሆኑንም ማስታወስ
እወዳለሁ፡፡


Share ማድረግ እንዳይረሳ ስለ እመብርሀን
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን !!!
✝️ የእግዚአብሔር የባሕሪ ቅጽል ስሞች ✝️
ስም፡- በቁሙ ከባህርይ ግብር የሚወጣ እንዲሁም አንዱ ከአንዱ መለያ የሚሆን ቦታና አካላትን ህላዌ ያለው ማናቸውም ሁሉ በየክፍሉና በየአካሉ በየራሱ ቅሉ በየአይነቱና በየመልኩ በየገጹ በየአባቱ በየዘመዱ ተለይቶ የሚጠራበት የሚታወቅበት ማለት ነው፡፡
እግዚአብሔር የተጽውኦ፣ የተቀብኦ ያይደለ የባህርይ ግብር ስም ነው፡፡
እግዚአብሔር በየቋንቋው የተለያዩ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ስሞች አሉት ነገር ግን ሁሉም ባህሪያዊ ስለሆኑ እና እግዚአብሔር በባህርይው አንድ ስለሆነ በአንድነት ፈጥሮ በሚገዛበት በባህሪይው በመጥራት ይተባበራሉ ወይም አንድ ይሆናሉ፡፡
@embtee
የማንኛውንም ቋንቋ ተናጋሪዎች አንድ የሚያደርጋቸው ሁሉም በየቋንቋቸው እግዚአብሔርን ከፍጡራን ለይተው በባህርይው መጥራታቸው ነው፡፡
በእያንዳንዱ ቋንቋ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ስም ትርጉም ብንመረምር የምናገኘው እያንዳንዳቸው እግዚአብሔርን የሚጠሩት በኃያልነት በፈጣሪነት በዘለዓለማዊነት በቸርነትና በሁሉም አድራጊነት መሆኑን ነው፡፡
@embtee
ስለዚህ ይህ መሆን የሚቻለው ለፍጡር ሊሰጡት የማይገባ ቢሰጡትም የማይስማማው ነው፡፡ ይህም በመሆኑ በየቋንቋው ያሉ የእግዚአብሔር ስሞች ባህሪውን ይገልጣሉ፡፡
‹‹ፈጣሪ አምላክ›› በልዩ ልዩ ቋንቋ በልዩ ልዩ ስም እንደሚጠራ ሁሉ በእኛ በኢትዮጵያዊያን ቋንቋ በግእዝም እግዚአብሔር ተብሎ ይጠራል ‹‹ ገባሬ ኩሉ ከከሃሌ ኩሉ ዘሥሉጥ በላእስኩሉ ›› (ሁሉን የፈጠረ፣ ሁሉን ማድረግ የሚችለው፣ በሁሉ ላይ ሥልጣን ያለው ማለት ነው) /ሃይማኖተ አበው መግቢያ /
@embtee
አንድም እግዚአብሔር ማለት አብ ወልድ መንፈስቅዱስ ማለት ነው፡፡ ‹‹ እኔስ እግዚአብሔር አብ ስል አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለቴ ነው›› እንዲል አምላካችን ስሙ ክብር ገናና ቅዱስ የተመሰገ ነው፡፡ ሚ.2፡2፣ ሕዝ 39፡2፣ መዝ 134፡1-3 ፣ ፊል 2፡10 ልንጠራው የሚገባን በጸሎት ጊዜ በምስጋና ጊዜ እና በኃዘናችን ጊዜ ነው፡፡
@embtee
በፍጥረቱ ለፍጥረቱ በቸርነቱ የሚገለጠው እግዚአብሔር ከማንኛውም ሌላ ሁናቴ የተለየና የላቀ በመሆኑ የእርሱን ባህርይ ለመግለጽ አይቻልም ከአስተሳሰባችን እና ከችሎታችን በላይ ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ምሳሌነት ብቁ የሚሆን ምንም ነገር የለም፡፡ ኢሳ 40፡18 በመለኮታዊ ክብሩ ለዘላለም በራሱ የሚኖር ነው፡፡ በመሆኑም የእግዚአብሔርን ባህርይ ለመመርመር አይቻልም፡፡ 1ኛ ቆሮ13-12 ነገር ግን ቅዱሳት መጻሕፍት ከሚገልጡትመገለጫዎቹ በጥቂቱ ለመግለጥ ያህል
@embtee
1. መንፈስ ነው፡- እግዚአብሔር መንፈስ /ረቂቅ ስለሆነ በህዋሳታችን አማካኝነት ልናውቀው አንችልም እግዚአብሔር መንፈስ ነው / ረቂቅ ነው /ሲባል ዝርው/ብትን/ አካል የሌለው ማለት አይደለም ረቂቅ መንፈሳዊ አካል ያለው ነው ለግዙፍ አካል መስፈርት የሚሆኑ እንደመጠን ትልቅነት ክብደት የመሳሰሉት ለእግዚአብሔር አይሆኑም ረቂቅ አምላክ ነውና ዩሐ 14፡1፣ 2ኛቆሮ 3፡17፣ ከውኃ እሳት ይረቃል ከእሳት ነፋስ ይረቃል ከነፋስ መላዕክት ይረቃሉ ከመላዕክት ሀሳባቸው ይረቃል እግዚአብሔር ከመላዕክት ሀሳብም ይረቃል የመላእክት ሀሳብ በእግዚአብሔር ዘንድ እንደተራራ የገዘፈ ነው፡፡
2. ዘላለማዊ ነው፡- እግዚአብሔር በዘመናት የማይቆጠር መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው ዘላለማዊ ነው የጊዜና የዘመናት ፈጣሪ ሉቃ 1፡37 ነውና ለዘመኑ ጥንትና ፈፃሚ የለውም፡፡ መዝ 89፡2፣ መዝ 101፡24-27፣ መዝ 144፡13፣ ኢሳ 44፡6፣ ራዕ 1፡8
3. ሁሉን ቻይ ./ከሃሌ ሁሉ / ነው፡- እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ አምላክ ስለሆነ የሚሳነው ነገር የለም፡፡ ዘፍ 18፡14፣ መዝ 134፡6፣ ኤር 32-17፣ ማቴ 19፡26፣ ሉቃ 1፡37
4. አይለወጥም፡- እግዚአብሔር በውሳኔው የሚጸና ያለውን የሚያደርግ የተናገረውን የሚፈጽም በውሳኔው እንደሰው የማይጸጸት አምላክ ነው፡፡ ተወዳዳሪ የሌለው ፍጹም በመሆኑ ከዚያ የበለጠ ፍጹምነት ሊኖር ስለማይችል የበለጠ ፍጹም በመሆኑ አይለወጥም አሁን ካለው ደግነት መሐሪነት ትክክለኛ ፍርድ ፈራጅነት ቅዱስነት አዋቂነትና ብርታት ኃያልነት አይጨምርም ወይም አይቀንስም፡፡ ፍርዱም በጊዜና በሰዓት ያልተወሰነ በመሆኑ ሀሳቡን መለወጥ እና ውሳኔውን ማሻሻል አያስፈልገውም በኢሳ 38፣ ዮና 3፡10 ላይ እግዚአብሔር ከፈረደባቸው /ከተቆጣ በኃላ/ ይቅር አላቸው ይላል ይህ እንዴት ነው ቢባል ይሆናል ይህ የተለወጠው እግዚአብሔር ሳይሆን ራሳቸው ናቸው ሰዎቹ በንስሐ በተመለሱ ጊዜ ከጥፋት ድነዋል፡፡ እግዚአብሔር የማይለወጥና የማይጸጸት መሆኑን የሚያረጋግጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፣ ዘኁ 23፡19፣ 1ኛ ሳሙ 15፡29፣ ሚል 3፡6፣ ሮሜ 11፡29
@embtee
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ይቆየን !!!
👇👇

@yitayal123bot
የውዳሴ ከንቱ አስከፊነት


✞ እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ፃድቅ አድርገው ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ። አባ እንጦስ ✞



@embtee
@embtee

የአትሮኖሱ ንጉስና የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ ታላቁ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ውዳሴ ከንቱ አስከፊነት ሲያስተምር፦ ☞ ውዳሴን ከንቱን መሻት የገሃነመ እሳት እናት ናት ውዳሴ ከንቱን መሻት እሳቱ ለማይጠፋው ትሉ ለማያንቀላፋው ዓለም መጋቢዋ ናት ሌሎች ክፉ ምግባራት በሞት ይገታሉ ውዳሴ ከንቱ ግን አንድ ሰው ከሞተ በኃላ እንኳን ሊያደርገው የሚችለው የክፉ ክፉ ምግባር ነው በመሆኑም ውዳሴ ከንቱ የገሃነም እሳት እናት ናት እላለው ሌሎች ክፉ ምግባራት ሰው ሲሞት ይቆማሉ ውዳሴ ከንቱ ግን ከሞቱ በኃላ እንኳን የሚቀጥል ነው። ታዲያ ከዚህ የባሰ ምን አለ ልንል እንችላለን? ምን ማለቴ እንደሆነ እነግራችው ዘንድ ትሻላችሁን? እስኪ ወደ መካነ መቃብር ሂዱ ቢያንስ አሁን በአካል ባትሄዱ በዓይነ ህሊናችው ሂዱ ብዙ የብዙ ብዙ ሐውልቶችን አታገኙምን? አዎ! እነዚህ ሰዎች ከመሞታቸው በፊት የሚናዘዙት ሀብታቸው ለድሆች እንዲሰጥ አይደለም፤ ሀብታቸው ብል እንዲበላው ሐውልት እንዲቆምላቸው እንጂ። በቀብር ሥነ-ሥርዓታቸው ላይ ለየት ያለ ትርዒት እንዲፈፀምላቸው ነው የሚናዘዙት እነዚህ ሰዎች በዘመናቸው ድሆችን ሲሳደቡ የነበሩ ናቸው አንዲት ቁራሽ ዳቦ ለድሀ መመፅወት ሲያሳፍራቸው የነበሩ ናቸው የምድር ትላትል ይበሉት ዘንድ መቃብራቸው እንዲያምር ሲናገሩ ግን ምንም ሀፍረት ቢጤ አይሰማቸውም ለሰራተኞቻቸው ደሞዝ ለመጨመር ይንገበገባሉ እንዲሁ በከንቱ ለትላትል ለሚያወጡት ገንዘብ ግን እጅግ ይጨነቃሉ። ወዮ! በአርአያ ስላሴ የተፈጠረውን ሰው ረስቶ ለትላትል ከመጨነቅ በላይ ምን ከንቱነት አለ? ከዚህ የባሰ ክፉ ደዌ ምን አለ?... በማለት እኛ ኦርቶዶክሳውያን ከውዳሴ ከንቱ መጠንቀቅ እንዳለብንና ካልተጠነቀቅን ግን ይቺን አለም ተሰናብተን እንኳን ውዳሴ ከንቱ ተከትሎን እንደሚመጣ ያሳስበናል።

ተወዳጆች በተለይ እኛ ኦርቶድክሳውያን ሁሉ ነገራችን ኦርቶዶክሳዊ መምሰል ነው ያለበት አነጋገራችን፣ አካሄዳችን፣ አለባበሳችን ሁሉ ትህትናን የተሞላ ነው መሆን ያለበት ውዳሴ ከንቱ የነበረንን መልካም ምግባር ሁሉ የሚያሳምም ደግሞም የሚገድል ክፉ ደዌ ነው መጽሐፍ ቅዱሳችን በሰው ዘንድ የከበረ በእግዚአብሄር ዘንድ ግን የተዋረደ ነው እንዲል ውስጣችን በውዳሴ ከንቱ የተሞላ ከሆነ ብንሰብክ፣ ብንዘምር፣ ብንመጸውት፣ ብንጸልይ ስብከታችን፣ ዝማሬያችን፣ ምጽዋትችንና ጸሎታችን በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነው ውዳሴ ከንቱ ካለብን ውስጣችን ንፅህና የለውም ስለዚህ ሰው ንፅህናውን እንዲያጣ የሚያደርገው ዝሙት ወይም ማመንዘር ብቻ ሳይሆን ውዳሴ ከንቱምም ጭምር ነው።

✞ በአንድ ወቅት አባ ጵላን የተባለ ቅዱስ አባት ከእግዚአብሄር ዘንድ ውጣና አስተምር የሚል ትእዛዝ ደርሶት ነበረ እርሱ ግን ዝም ብሎ ተቀመጠ ውጣና አስተምር አላልሁህምን? ብሎ ሲጠይቀው አስተምር ካልከኝስ የትዕቢትን ሰይጣን ከእኔ አርቅልኝ ብሎ ለመነ ሰይጣነ ትዕቢትንም ከላዪ አወጣለት ይህ መንፈሳዊ አባት በማስተማር የሚመጣውን ፆር ፈተና ተረድቶ ስለነበረ አስተምር ሲባል በማስተማሩ ስለሚመጣበት ጉዳይ አጥብቆ ጠየቀ ይህ አባት እንዲያስተምር የታዘዘው በራሱ በፈጣሪ በመሆኑ እንኳን ልቡ በኩራት አልተሞላም በውዳሴ ከንቱም አልታበየም ከራሱ ከፈጣሪ ዘንድ ተልኬ ታዝዤ መጣው እያለ በሰው መካከል ለመኮፈስና ስለሱ ቅድስና ብቻ እንዲወራ አልቸኮለም ትምህርቱንም ሕይወቱንም ሊያበላሽ የሚችለውን መንፈሰ ትዕቢት አርቅልኝ አለ እንጂ።

እኛ ብንሆን ግን እንኳን ልዑለ እግዚአብሔር አምላካችን አዞን ቀርቶ የደብራችን አስተዳዳሪ የሆኑ አንድ አባት ቢያዙን እንኳን መሬት አትንካኝ፣ ከኔ በላይ ማን አዋቂ አለ በማለት ትእቢታችን አፍንጫችን ላይ ደርሶ በውዳሴ ከንቱ ታብየን ለመካሪዎች እንኳን እናስቸግር ነበረ። አንድ ሰው በውዳሴ ከንቱ ተወጥሮና ትዕቢተኛ ሆኖ በትህትናው ዓለምን ስላዳነው አምላክ ማስተማር አይችልም ስለጌታችን በትንቢት "ለአህዛብ ፍርድን ያወጣል አይጮህም ቃሉንም አያነሳም ድምፁንም በሜዳ አያሰማም የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም የሚጤስንም ክር አያጠፋም" ተብሎ በኢሳ 42፥1-4 ላይ ተጽፏል ይህም ጌታችን ሲያስተምር ውዳሴ ከንቱ የማይሰማበት፣ በጭምትነት የሚሄድ፣ ንግግሩ የለዘበ እንደነበረ ያስረዳል ቅዱሳን ሐዋርያትም እንኳን ራሳቸውን ሊሰብኩ ሌሎች ሲያመሰግኗቸው እንኳን ልብሳቸውን ቀድደው "እናንተ ሰዎች ይህንን ስለምን ታደርጋላችው? እኛ ደግሞ እንደ እናንተ የምንሰማ ሰዎች ነን ከዚህም ከንቱ ነገር ሰማይና ምድርን ባሕርንም በእነርሱ ያለውን ሁሉ ወደፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ዘወር ትሉ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን" ይሉ ነበር። ሐዋ 14፥15

✞ ትህትናን ስናስብ ፍፁም ከአይምሯችን የማትጠፋው ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ የሆነች እናታችን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በትንቢት መሲህ እንደሚወለድ ይጠበቅ ስለነበረ መሲህ ክርስቶስን ለምትወልደው ድንግል ባሪያ መሆንን ትመኝ ነበረ ዳሩ ግን ክርስቶስ በማይመረመር ምስጢር በፍፁም ተዋህዶ ማህተመ ድንግልናዋን ሳይለውጥ ከእርሷ እንደሚወለድ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ሲበሰራት "እንደቃልህ ይደረግልኝ እኔ ለእግዚአብሄር ባሪያው ነኝ" አለችው እንጂ አምላክን በመፀነሷ አልታበየችም ታዲያ ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ የሆነችው እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትህትናን ካስተማረችን እኛ ማን ነንና ነው በትእቢት ታውረን በውዳሴ ከንቱ የምንጨማለቀው።

✞ ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ፣ ኢትዮጵያዊው ዮሐንስ አፈወርቅ እየተባለ የሚጠራውና ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ቄርሎስን፣ ዮሐንስ አፈወርቅን ወለደች እየተባለ ሀገራችንን ያስጠራው በ1357 ዓ/ም በወሎ ክፍለ ሀገር በቦረና ወረዳ ሸግላ/ሰግላ በተሰኘ ቦታ ከአባታቸው ሕዝበ ጽዮን እና ከእናታቸው እምነ ጽዮን የተወለደው ታላቁ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በህይወታቸው ፍፁም ትሁት ከውዳሴ ከንቱ የራቁ ታላቅ ሊቅ ነበሩ ታዲያ እኚህ አባት ድንቅ ድንቅ መፅሐፍቶችን ጽፈው እራሳቸውን ዝቅ ካደረጉ ዛሬ እኛ የሰናፍንጭ ቅንጣት ለማታክል እውቀታችን በውዳሴ ከንቱ ስንንገላታ ማየት ያሳፍራል

❖ ስለዚህ ተወዳጆች ጌታችን መድኃኒትችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስከፊ ከሆነው ከውዳሴ ከንቱ ይሰውረን ዘንድ የዘወትር ፀሎታችን ሊሆን ይገባል።


#join 👇👇

@embtee
@embtee

ወስብሃት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር

Inbox ይላኩልን👉👇 @yitayal123bot
በቤተክርስቲያናችን ስርአት መሰረት 7 ጊዜ እንፀልያለን የእነሱም ትርጉም
እንደሚከተለው ቀርቦአል ።ካነበቡ በኃላ ሼር ማድረግዎን እንዳይረሱ።
ጠዋት 12 አንድ ክርስቲያን እግዚአብሔርን አምላክን በፀሎት
የሚያመሰግንበት ምክንያት (ሚስጥር)
1 እግዚአብሔር አምላክ ሌሊቱንና ጨለማውን አሳልፎ ብርሀን እንድናይ
ስላበቃን በዚህ ሰአት እግዚአብሔር አምላካችንን እንድናመሰግን ታዝዝዋል
አንድም በዚህ ሰአት ጌታችን ለክስ ከጲላጦ ፊት ቆሞ የተወቀሰበት ሰአት ስለሆነ
አንድም በዚ ሰአት አባታችን አዳም ያልተፈቀደለትን እፅ በልቶ ከገነት የተባረረበት
ሰአት ስለሆነ ነው አንድ ክርስቲያን ይህን ሁሉ እያሰበ ወደ አምላኩ እንዲፀልይ
ታዝዋል
ሰልቱ ሰአት ከጠዋቱ 3 ሰአት አንድ ክርስቲያን እንዲፀልይ የታዘዘበት
ምክንያት (ሚስጥር)
1 በዚህ ሰአት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብስራተ ገብርኤልን
የሰማችበት ሰአት ስለሆነ ነው አንድም በዚህ ሰአት እመቤታችን ቅድስት ድንግል
ማርያም ጌታችንን የፀነሰችበት ሰአት ስለሆነ ነው አንድም ጌታችን መድሀኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ከ ጲላጦስ ፊት ቀርቦ የተገረፈበት ሰአት ስለሆነ ዮሐ 19 ፥1
ሐዋ ስራ 2፥15 እያንዳንዱ ክርስቲያን ይሔንን የመሳሰሉ ሁሉ እያሰበ
እግዚአብሔር አምላኩን እንዲያመሰግን ታዝዋል
6:00 አንድ ክርስቱያን እኩለ ቀን (ከ ቀኑ 6ሰአት) ሲሆን እንዲፀልይ
የታዘዘበት ምክንያት ወይም (ሚስጥር )
1 ጌታችን በቀራኔዎ አደባባይ በመስቀል ተሰቅሎበታልና አንድም ልብሱን
ተገፎበታል አንድም ሳዶር አላዶር ዳናት ሮዳስ በተባሉ ችንካሮች ተቸንክሮበታል
አንድ ክርስቲያን ይህን ሁሉ እያሰበ በዚህ ሰአት እንዲፀልይ ታዞበታል
ተስአተ ከ ቀኑ 9:00 ሰአት ሲሆን አንድ ክርስቲያን የሚፀልይበት
ምክንያት (ሚስጥር)
1 አይሁዶች ጌታችን መድሀኒታችን ኢየ�ሱስ ክርስቶስን መራራ ሐሞት
አጠጥተውበታል አንድም ቅድስት ነፍሱን ከ ክቡር ስጋው የለየበት ሰአት ነውና
አንድም በመስቀል እንዳለ 7ቱን አፅርሀ መስቀል የተናገረበት ማር 15፥34 ማቴ
27፥50 አንድ በዚህ ሰአት ይህንን እያሰበ እንዲፀልይ ታዝዋል
የሰርክ ሰአት ከቀኑ 11፡00 ሰአት አንድ ክር�ቲያን እንዲፀልይበት
የታዘዘበት ምክንያት ወይም (ሚስጥር)
1 ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ወደ ከርሰ መቃብር የወረደበት ሰአት
ስለሆነ አንድም ቀኑን በሰላም አሳልፎ ወደ ምሽት በሰላም ያደረሰን አምላክ
ምስጋ ስለሚገባው ነው ይህንን የመሳሰሉ ሁሉ ሕዝበ ክርስቲያን እንዲያስቡ
ታዘዋል
6 ከምሽቱ 3 ሰአት በዚህ ሰአት አንድ ክርስቲያን እንዲያመሰግን
የታዘዘበት ምክንያት (ሚስጥር)
1 በዚህ ሰአት እራሱ ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ስርአተ ፀሎት
አሳይቶበታል አንድም በዚህ ሰአት ጌታችንን አይሁድ በይሁዳ ጠቁዋሚነት
ተረበርበው የያዙበት ሰአት ስለሆነ ነው አንድም በዚህ ሰአት አንድ ክርስቲያን
ከመተኛቱ በፊት በሰላም ያዋለንንና ያስመሸንን አምላክ አመስግኖ መተኛት
አለበት ይህን ሁሉ እያሰበ እንዲፀልይ ታዝዋል
መንፈቀ ሌሊት ከሌሊቱ 6ሰአት በዚህ ሰአት አንድ ክርስቲያን
እግዚአብሔር አምላኩን እንዲያመሰግንበት የታዘዘበት ምክንያት (ሚስጥር)
1 በዚህ ሰአት ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተወልዶበታልና ነው
አንድም ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሙስና መቃብርን ድል
አድርጎበታልና(ተነስቶበታል) በመዝሙረ ዳዊት አመሰግንህ ዘንድ በመንፈቀ
ሌሊት እነሳለው ባለው መሰረት ጳውሎስ ሲላስ በእስር ቤት ሆነው ወደ
እግዚአብሔር የፀለዩበት ስለሆነ ነው አንድም የሰው ልጅ የሚመጣበት ጊዜ ማታ
ይሁን መንፈቀ ሌሊት ይሁን ዶሮ ሲጮህም ይሁን ሲነጋም ቢሆን አይታወቅምና
ባለው አምላካዊ ቀል መሰረት በመንፈቀ ሌሊት አንድ ክርስቲያን እንዲፀልይ
ታዝዋል
ወስብሀት ለእግዚአብሔር
ወለ ወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክብር

#join
@embtee
@embtee

Inbox ይላኩልን @yitayal123bot