ግጥምጥሞሽ ወይስ #እግዚአብሔር_መንፈስ_ቅዱስ?
የአንድ ሰካራም መዝሙር
" #የሰዎች ነገር #አይተኛም "
_____
ቀኑ ብሩሃማ ነው ሰሞነ ሕማማት ከገባ ሦስተኛ ቀን ሆኖታል የቀለም ቆጠራ አለ ስለተባለ እንደ ሳምንቱ ወሳኝ ኩነቶቼ ሁሉ ወደ ቀለም ትምህርት ቤት እየገሰገስኩ ነው። አንድ እብድ መሳይ የኔ ቢጤ የፕሮቲስታንት ሰባኪ በሚመስል ሁናቴ ቀኝ እጁን ወደ ላይ ከፍ አድርጎ አንድ በስፋት የሚታወቅ የይልማ ኃይሉን መዝሙር እየቀለጸ በእኔ ተቃራኒ አቅጣጫ ሲመጣ አየሁት ። መዝሙሩና የመዝሙሩ ዜማ :- "የሚጠብቀኝ አይተኛም አያንቀላፋም" የሚል መሆኑን እርግጠኛ ነኝ ግን ሰውየው የመጀመሪያውን የስንኝ አንጓ በራሱ ሆድ ብሶት ቀይሮ እየዘመረው ነበር። እንዲህ በማለት "የሰዎች ነገር አይተኛም (2)× አያንቀላፋም " ........
........ወዲያውኑ መገረም ያዘኝ ። እውነቱን እኮ ነው ጎበዝ ".......የሰዎች ነገር አይተኛም !" የሚጠብቀን ራሱ የማይተኛው የሰዎች ነገር ስለማይተኛ ይመስለኛል። ምናልባት ትክክለኛው ዘማሪ የዚህን የኔ ቢጤ አዘማመር ቢሰማ ኖሮ የሰዎች ነገር አይተኛም በሚለው ቀይሮ በዘመረው ነበር።
ዓለም ብቻ ሳትሆን የሰዎች ነገርም ብዙዎችን ወግታ ጥላለች። ለነገሩ ዓለም የሚለው በዋናነት የሰው ልጆችን አይደለምን? ነው እንጂ። #ምሳ 7÷26
ግን ግን ይህን ሰካራም እንዲህ ብሎ እስኪዘምር ድረስ የወጋው እና #ጽኑ_ሕማማም የሆነበት የሰው ነገር ምን ይሆን ? በእርግጥስ ያሰከረው ጌሾና ብቅል ነውን ወይስ ነገረ ሰብ ???
ስትወፍር ዘረጦ ፣ ስትከሳ ሜንጦ ፣ ብትረዝም ብቅል አውራጅ ፣ ብታጥርም ጉቶ ፣ ስታገኝ ሰላቢ ፣ ስታጣም ችጋራም ፣ ብታነብ ደብተራ ፤ ብትጽፍ መተታም ስትተወው ደንቆሮ ፣ ስትናገር ተናጋሪ ፣ ዝም ብትል ዝጋታም እያሉ የሚወጉ የሕማማት ሁሉ ምንጭ አንደበተ ሕማማት መጨረሻቸው ምን ይሆን ።
ንጹሐ ባህሪ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳ በመዋለ ስብከቱ ሳለ ይህ የሰዎች የነገር ውጋት አግኝታዋለች ፤ እርሱ ግን "ማይመረ ኩሉ " ሁሉን የሚያውቅ እውነተኛ አምላክ ነውና " ዮሐንስ ሳይበላና ሳይጠጣ መጣ፥ እናንተ ግን፦ ጋኔን አለበት አላችሁት። እነሆ የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፥ እናንተም፦ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፥ የቀራጮችና የኃጢአተኞች ወዳጅ አላችሁት። " ብሎ አምርሮ ወቅሷቸል። #ማቴ 11÷18-19 ክርስቶስ እንኳ በሰው አፍ ያለ በደሉ ሲነቀፍ አስተዋልክን ? ብትበላም ባትበላም ትወቀሳለህ ብታውቅም ባታውቅም ትወረፋለህ ቅንም ቅንቅንም ብትሆን ትተቻለህ
እና ወዳጄ ምን አሰብክ ? የሰውን የነገር አፍ ፈርተህ መቆምን መረጥክን? ከቆንጆ ሕልምህስ መንቃት ፈለክን?? አትሞኝ ሕልምን ብታቆምም መንገድህንም ብትገታ ከሰው አፍ አትወጣም ምክንያቱም " #የሰዎች ነገር #አይተኛም አያንቀላፋምም " ሊሰራ ተነስቶ ነበር አቅቶት ተወው ሕልመኛ መስሎን ነበር ለካ እየቃዠ ነበር ይሉሃል። #ሉቃ 14÷30
እንደ ጋሪ ፈረስ ለጥቃቅን የጎንዮሽ ዕይታ ትኩረት ነፍገህ ወደፊት ወዳለችሁ የጽድቅ መንገድ በፈጣሪህ ሕግና ትዕዛዝ መሠረት ያለ መታከት ገስግስ። ውሾች ይጩሁ ግመሎችም ይሂዱ !
ለዚያም ሰካር ዘማሪ #እግዚአብሔር_አምላክ ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን ከሰው የአፍ ፍላጻም በጽኑ ይፈውስልን አሜን!
......" የ ሰዎች ነገር አይተኛም (2) × አያንቀላፋም ".........
አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
ሚያ03/2015 ዓ.ም