ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#አደረጃጀት_እናፍጥን

ለመግደል ባንሄድ ለማቃጠል እሳት ባንለኩስ ሊገድሉን የሚመጡትን እሳታቸውን ማጥፋት ተገቢ ነው፡፡ ለዚህም አባቶቻችን ዮዲት ጉዲትን ግራኝን እንዲሁም የካቶሊክ ወራሪን እንዴት እንደገቱት የቀደመው ታሪክ ይነግረናል፡፡ አባቶቻችን ጳጳሳት በኛ ዘመን ደጋግመው እያነቡ እንደ ልጅነታችን የድርሻችንን መወጣት ይጠበቅብናል፡፡ ካልሆነ የተሰዉት ደም ምድር እስክትቀላ ፈሶ፤ የአባቶቻችንም እንባ ምድርን ጎርፍ ሆኖ አጥለቅልቆ የተኛነውን እና ሚናችን ያልተለየውን አይተወንም ይወስደናል፡፡ ደማቸው ከጸባዖት እንባቸው ከምድር ኤሎሄ ኤሎሄ ይላልና ድርሻችንን በምንችለው አቅም እንወጣ፡፡ እግዚአብሔር መሲህውን ከኛ መኃል ያስነሳልናልና ምህረቱን ለመቀበል የተዘጋጀን እንድንሆን በጸሎት የሚተጋ ጸሎቱን በማስተማር የሚተጋ ማስተማሩን ያጠንክር፡፡ ተደራጅተን መከላከል ያለብንና በህብረት የምንቆምበት ጊዜ አሁን ነውና የሃገሪቷ መሪዎች ከየትኛው ወገን እንደሆኑ አጥርተን አበጥረን የምንለይበት፤ እንዲሁም በማን አለብኝነት ከቤተክርስቲያኗ አናት ላይ ጉብ ብለው የሚያሳርዱንን የሚያስቃጥሉንን እስክናወርዳቸው ድርስ በፍጥነት መደራጀት ከኛ ከምዕመናን ይጠበቃል፡፡

#አደረጃጀቱም
#1 በየክፍለ ከተማው የሚገኙ ምዕመናን በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት በየሰበካ ጉባዔው እንዲደራጁ ማድረግ፡
#2 በየትምህርት ቤቱ ኦርቶዶክሳዊያን ክርስቲያኖች እንዲደራጁ ማድረግ፡
#3 በየመስሪያ ቤቱ ያሉ ኦርቶዶክሳዊያን ክርስቲያን ምዕመናን እንዲደራጁ ማድረግ፡
#4 በንግድ አካባቢ የሚገኙ ኦርቶዶክሳዊያን እንዲደራጁ ማድረግ፡
#5 የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ኦርቶዶክሳዊያን እንዲደራጁ ማድረግ፡
#6 ወደ ወረዳ ወደ ቀበሌዎች አደረጃጀቱን በማውረድ በየመንደሩ እንዲደራጁ ማድረግ፡

#ማሳሰቢያ
#1 ይህ ሁሉ የሚሆነው አጽራረ ቤተ ክርስቲያንን ለማስቆም፤ ማውደማቸውን ጀመሩ እንጂ አልጨረሱምና ለመከላከል እንዲረዳን እንጂ የትኛውንም ሰው ለመጉዳት አይደለም፡፡
#2 አጥፊዎችን እኩይ ተግባራቸውን ከምንጩ ለማድረቅና ለመከላከል በመሆኑ ሌሎችን ባለን አብርሃማዊ አቀባበል በሰላም መኖር ዋናው መርህ መሆኑን እያንዳንዳችን በመገንዘብ እንቅስቃሴው እንዳይጠለፍ መጠንቀቅ፡

የተሻለ ሀሳብ ስለሚኖር እንምከር አማራጮችን እንይ፡፡ ባንገድልም ቀባሪ አንሆንም፡፡ ባናሳድድም አሳዳጅ አንሆንም፡፡ ጠላቶቻችን በየወቅቱ እየሞከሩን እየፈተሹን የሚሄዱበትን የትፋት ተግባር ባናስቆም ሰከን እንዲሉ እናደርጋለን፡፡

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit