ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#ሰውየው ከሰው በር ላይ የሆነ #ነገር ይሰርቃል ትንሽ ቆይቶ ግን ይጸጸታል ተጸጸቶም አልቀረ መምህረ ንሰሐ (የንስሐ አባቱ) ዘንድ ሄዶ አባ #ገመድ ከሰው ደጅ ሰርቄያለው ይቅር ይበሉኝ ብሎ ይናዘዛል አባም የንስሐ ኑዛዜውን ተቀብለው ቀኖና ሰተው #እግዚአብሔር ይፍታህ ብለው ሸኙት ....
በሌላ ጊዜ ሰውየው ተመልሶ #መጣ አባም ምነው መልሰህ በደልክ እንዴ ሲሉ ጠየቁት አባ
ሰውዬውም እየተንተባተበ አይ አባ #የባለፈው ስርቆቴ ነው አላቸው አባም ላለፈውማ ቀኖና ሰጥቼ ንስሐ ገብተሃል #እግዚአብሔርም ምሮሃል ሂድ ብለው መለሱት ሰውየውም #ቅር እየተሰኘ ሄደ ነገር ግን ሄዶ አልቀረም ተመልሦ ለሦስተኛ ጊዜ #መጣ አባም ግራ ተጋብተው አሁንስ ለምን ተመልሰህ መጣህ ሲሉ ጠየቁት ሰውየውም በፍርሃት ድምጽ #የ.... የ.. የየባለፈው #ገመድ አላቸው ያኔ አባ አንድ ነገር #አስተዋሉ ቀና ብለው በፈገግታ ከተመለከቱት በኃላ ልጄ የገመዱ #ጫፍ ላይ ምን ታስሮ #ነበር? ብለው ጠየቁት ሰውየውም አንገቱን አቀርቅሮ በቀስታ በ......በ......#በሬ🐂 #አላቸው::



ስንቶቻችን #በሬ የሚያክል ኃጢያት ሰርተን #የገመድ ንሰሐ ገብተን #ይሆን????????? መልሱን #ልቦና ይመልሰው


" የንሰሐ #ግማሽ
ጽድቅን ሁሉ #ደርማሽ"

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit