ዐውደ ምሕረት
3.66K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
"፤ ለእርስዋ መታሰቢያ እንዲሆን ይነገራል። " ማቴ 2÷13

የቅዱሳን ዝክር በማሰብ በመናገር እና በመተግበር ሊከበር ይችላል::ተዘከሩ ለመኳንንቲክሙ ዘነገረክሙ ቃለ እግዚአብሔር ::የእግዚአብሔርን ቃል የነገሯችሁን ዋኖቻችሁን #አስቡ ዕብ13÷7
አስቡ ማለቱ በዕሊናቸው ስራቸውን እፁብ እፁብ በሉ ማለቱ ነው ወረድ ብሎም በማሰብ ብቻ ሳይሆን እነርሱ በኑሯቸው የሰሩትን እናንተም በማየት በተግባር ተግብራችሁ ምሰሏቸው ይለናል ::የኑሯቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነት ምሰሏቸው" እንዲል ከየት አግኝተን እንምሰላቸው ቢሉ ስለ እነርሱ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን በመጠየቅ ቅዱሳን መጻሕፍት በማገላበ እናገኛቸዋለን::"፤ ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም፥ ወደ ወለደቻችሁም ወደ ሳራ ተመልከቱ፤። " ኢሳ 5÷2 እነ አብርሃምን ከወዴት አግኝተው ይመልከቱ ቢሉ የነ አብርሃምን ታሪክ ጠይቀው መጻሕፍት ጠቅሰው ይወቁ ሲል ነው እንጂ በዘመን ተዳርሰው አይደለም
በቅድስና ሕይወት ከተመላለሱ በዕሊና በማሰብ በአንደበት በመናገር በተግባር ከመዘከር ከሚታወሱ ቅዱሳን መካከል ሰማዕታት አንደኖቹ ናቸው::
ቅድስት አርሴማ አትናስያ የምትባል እናት ነበራት ልጅ በማጣት ለረጅም ዘመን ታዝን
ታለቅስ ነበር በኃላም እግዚአብሔር ልመናዋን ሰማት ይህችን ክብርት ቅድስት
ልጅንም ሰጣት፤ቅድስት አርሴማ ጥር 6 ነው የተወለደችው፤15 ዓመት ሲሆናት
ሊያጋቡአት አሰቡ እርሷ ግን ይህን አልወደደችም፤ በደናግል ገዳም ገብታ
በተጋድሎ መኖር ጀመረች። ከዚህ በኃላ እንዲህ ሆነ ከሃዲው ንጉስ ዲዮቅልጥያኖስ ሊያገባት ወደደ ቅድስት አርሴማ ግን ከደናግሉ ጋር ሸሽታ ወደ አርማንያ ሄደች በዚያም በበርሃ ለጥቂት ቀናት ተቀመጠች በኃላ ላይ ድርጣድስ የሚባል አገር ገዢ በበርሃ እንደሚኖሩ ሰማ ወታደሮችንም ልኮ
አስመጣቸው፤ የቅድስት አርሴማን መልክ በተመለከተ ጊዜ ፈዞ ደንዝዞ ቀረ የፊቷ ውበት እጹብ ድንቅ፤ ግርማዋ የሚያስደነግጥ ልብ የሚያርድ ነበርና፤ስለዚህም ሊያሰቃያት አልደፈረም በእንክብካቤ በሰገነት ላይ አኖራት፤ ሌሎቹን ግን ለጣአት እንዲሰግዱ ገረፋቸው፤ ቅድስት አርሴማ እኔንም አሰቃዩኝ እያለች አምርራ ታለቀስ ነበር። ድርጣድስ ብዙ ጊዜ ሊሸነግላት ሞከረ እርሷ ግን ትዘልፈው ጣኦታቱንም ትረግም ነበር፤ እርሷ ጸንታ ደናግሉን ታጸና ነበር ትመክራቸው ታረጋጋቸው ነበር፤ ድርጣድስ ሽንገላው እንደማያዋጠው
በአወቀ ጊዜ ማሰቃየት ጀመረ፤ በመጨረሻም ከብዙ ስቃይ በኃላ መስከረም
29 ቀን አንገቷን በሰይፍ ተከላ ሰማዕትነትን ተቀበለች:: ይህችን ቅድስት ሰማዕትን ታድያ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዕሊና ታስባታለች በትምህርቷ(በንግግሯ)ታነሳታለች በተግባሯ አርያ ታደርጋታለች::

በወንጌል አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የበዛ ሽቱ የሞላው የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች በማዕድም ተቀምጦ ሳለ በራሱ ላይ አፈሰሰችው።
ደቀ መዛሙርቱም ይህ ጥፋት ምንድነው ሽቶ ተሽጦ ለድሆች በተቸረ ነበር አሉ

እርሱ ግን ድሆችስ ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር አሉ አላቸው: ቀጥሎም :"፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ወንጌል በዓለም ሁሉ በማናቸውም ስፍራ በሚሰበክበት እርስዋ ያደረገችው ደግሞ ለእርስዋ መታሰቢያ እንዲሆን ይነገራል። " (የማቴዎስ ወንጌል 26: 13) ይህች ሴት ዘመኗን ሙሉ ስትዘሙት የነበረች ሴት ነች ተፀፅታ ንስሐ ገብታ ባፈሰሰችሁ እንባና ሽቶ ይህ ቃል ኪዳን ከተሰጣት በክርስቶስ ፍቅር ልቦናቸው ተቃጥሎ እንደ ሴቲቱ ሽቶ ሳይሁን የከበረ ደማቸውን ያፈሰሱ ሰማዕታት ምን ያክል ቃል ኪዳኑ ይጸናላቸው ይሁን?

አዘጋጅ #ተርቢኖስ_ሰብስቤ

ከሰማዕቷ ረድኤት በረከት ይከፈለን አሜን!

📢📢📢📢📢📢📢📢📢
📢 @AwediMeherit 📢
📢 @AwediMeherit 📢
🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤